Sitot Adem Yimam - ስጦት አደም ይማም

Sitot Adem Yimam - ስጦት አደም ይማም እውነት፣ እውቀት እና ሰባዊነት ...መርሆቻችን ናቸው።
(1)

የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የፈተና ውጤታችሁን ከሚከተሉት አማራጮች በአንዱ ይዩ።ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et/ ቴሌግራም፡ https://t.me/EAE...
15/09/2025

የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የፈተና ውጤታችሁን ከሚከተሉት አማራጮች በአንዱ ይዩ።

ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EAESbot
አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡ 6284

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

13/09/2025

መስከረም 03፣2018ዓም
ልዩ የስኮላርሺፕ እድል ለመምህራን ትምህርት!

አንጋፋው እና ስመጥሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን የትምህርት ጥራት እና ተገቢነት ለማረጋገጥ የሚሰራውን ስራ ለመደገፍ እንደ ወትሮው ሀገራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል። ከዚሁ ጋር በተያየዘ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ልዩ የስኮላርሽፕ እድል አዘጋጅቷል።

የስኮላርሺፑ ተጠቃሚ ሁሉንም መመዘኛ ያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና በብቃት ያለፉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የዚህ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎች

- በተፈጥሮ እና ኮምፕዩቴሽናል ሳይንስ የትምህርት መስክ በፊዚክስ ፣ በኬምስትሪ ፣ በባዮሎጂ እና በሂሳብ እንዲሁም
- በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ፤ በእንግሊዘኛ ፣ በኢኮኖሚክስ ፣ በታሪክ፣ በጂኦግራፊ እና በሌሎችም የመምህርነት ትምህርት የሚከታተሉ ይሆናሉ።

የዚህ ስኮላርሽፕ ተጠቃሚዎች

- ሙሉ ነፃ የትምህርት እድል
- መጠነኛ የኪስ ገንዘብ
- ከአጋር ተቋማት ጋር በሚኖር ትብብር ተጨማሪ የስልጠና እድሎችን የሚያገኙ ይሆናል።

በመሆኑም የዚህ ልዩ እድል ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉና ከምርቃት በኋላ በመምህርነት ለማገልገል የምትሹ ሁሉ ከቅበላ በኋላ ዉል ፈርማችሁ ትምህርታችሁን መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

#አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣የተፅዕኖ ፈጣሪዎች ቤት
# አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ : ህልሞን ያሳኩ

10/09/2025

ለገፃችን ቤተሰብ ይሁኑ!

22/04/2025

ማስታዎቂያ

ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ https://exam.ethernet.edu.et የሚለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑ እንገልጻለን።

12/04/2025

ስምንቱ የሥነምግባር እና ውጤታማ አገልግሎት መርሆዎች :-
1.ትሕትና (Humility)፦
የራስን ጥንካሬ እና ውስንነት ማወቅ፣ ሌሎችን ማዳመጥ፣ ክፍት አዕምሮ መያዝ እና ከሌሎች ለመማር ዝግጁ መሆን።
2.አክብሮት እና ማካተት (Respect and Inclusion)፦
የሌሎችን ክብር መጠበቅ፣ ልዩነቶችን እንደ ሀብት መቁጠር፣ አድልዎ እና ጭፍን ጥላቻን መቃወም።
3.የመተባበር መርህ (Reciprocity)፦
ከአጋሮች ጋር በጋራ መስራት፣ የእውቀት እና የሀብት ልውውጥ ማድረግ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ።
4.ዝግጅት (Preparation)፦
የአገልግሎቱን ማህበራዊ፣ ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ መረዳት፣ ስለ አጋሮች እና ማህበረሰቦች መረጃ መሰብሰብ።
5.ደህንነት (Safety / Well-being)፦
የተሳታፊዎችን አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነት ማስጠበቅ፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ።
6.ተጠያቂነት (Accountability)፦
ለተግባራት እና ለገቡ ቃሎች ኃላፊነት መውሰድ፣ ግልጽነት እና መተማመንን መገንባት።
7.ግምገማ (Evaluation)፦
የአገልግሎቱን ተፅዕኖ መገምገም፣ ግብረመልስ መሰብሰብ እና ለቀጣይ መሻሻል መጠቀም።
8.ትምህርት እና ነፀብራቅ (Learning and Reflection)፦
ከተሞክሮ መማር፣ ባገኙት እውቀት ላይ ማሰላሰል እና የግል እድገትን ማረጋገጥ።

12/04/2025

Address

Masha

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sitot Adem Yimam - ስጦት አደም ይማም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share