18/09/2025
በጀት ለውድመት ውጤት ያስመዘገበው የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ የዲላ ከተማ ትምህርት መምሪያ ይፍረሱ።።።ተቋሙ ለግል ይሰጥ።።።
የጌዴኦ ዞን 2017 የትምህርት ዘመን ካስፈተናቸው ውስጥ 5745 ተማሪዎች መካከል 280 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ማግኘታቸውን በወጣው መረጃ መነሻ ተመልክተናል።
ይሁን እንጂ ያለፉት አብዛኛውን ተማሪዎች የዲላ ዶንቦስኮና ይርጋጨፌ ዩኒየን አካዳሚ ተማሪዎች ናቸው።
ዞኑ አጠቃላይ ካሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ካሳለፋቸው 280 ተማሪዎች ውስጥ 112 ተማሪዎች የይርጋጨፌ ዩኒየንና የዶንቦስኮ ተማሪዎች ናቸው ።
አጠቃላይ ከዲላ ውጪ የጌዴኦ ዞን ቢሊየን ብር በጀት አውጥቶ የትምህርት ስራ ሰርቻለሁ ብሎ አጠቃላይ ለመምህራንና ለትምህርት ጽ/ቤት ሰራተኞች በአበልና በደሞዝ የከፈለው ገንዘብ 150 ሚሊየን ብር ያልፋል ነገር ግን አጠቃላይ በዘንድሮ ከዲላ ውጪ ያሳለፋቸው ተማሪዎች ቁጥር 68 ብቻ ነው 112 ተማሪዎች በግል ትምህርት ቤት ይርጋጨፌና ዶንቦስኮ ተማሪዎች ናቸው።
ይህ ሁሉ በጀት ከመንግስት ቋት ወጥቶ ለእነዚህ ለግል ተቋም ቢሰጥ ኖሮ በሺዎች ማሳለፍ እንችል ነበረ። ትምህርቱን በጀት ለመቀራመት በሚል ብቻ ፖለቲካ አድርገው በዘር በጎሣ ሰንሰለት ያለ ብቃት አመራር የትምህርት ቤት ባለሙያ ይመደብና ትውልድ ይሞታል ነጌ ለማኝ ትውልድ ማፍሪያ ተቋም አድርገዋል ብቻ ትግሌ ትምህርት ከፖለቲካ ነፃ ይሁን በእውቀትና በባለሙያ ይመራ በዘር በጎሣ በዘመድ አዝማድ በጀት ያለበትን ቦታ ተቆናጥጠው ስራ እንዳይሰራ መምህራኑ በነፃነት እንዳይሰራ ሀሉንም ነገር ፖለተካ አድርገው ትውልድ የሚገድሉ ይነሱ ዘማች ክፍሌ ቀድሞ ይነሳ