
18/03/2025
ሙሉ ተሳፋሪ ህዝብ በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው ተወስደዋል ሚዲያው ግን ይህንን ሲዘግብ አላየንም የህገሪቱ ሚዲያወች የሰላማዊ ተጓዦችን መታፈን ካልዘገቡ ምን ይሆን ስራቸው ??
በዛሬው ዕለት በ08/07/2017 በኦሮሚያ ክልል ከፍቸ እና ጎሀፂዮን መሀከል በምስሉ የሚታየው የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪወች አሊደሮ የሚባል ልዩ ቦታ ላይ በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው ተወስደዋል :: የሀገሪቱ ሚዲያወች ግን ይህንን ትልቅ ግፍ እና በደል ከመዘገብ ተቆጥበዋል::
ሚዲያዎች በማይናማር ታግተው ስለሚገኙ ዜጎች ዘገባን ይዘው ወጣዋል መልካም ነው :: ሀገራቸው ከመቀመጫ ከተማቸው በ140 ኪሎ ሜትር እርቀት ስለታፈኑ ሰላማዊ ዜጎች ግን ትንፍሽ አላሉም ምክንያታቸው ምንድን ነው??
አንድ ሙሉ አውቶብስ ተሳፋሪ ታፍኖ ሲወሰድ ምንም አለማለት እንደ ሀገር ትልቅ ውድቀት ነው :: ዜጎች በዚህ መልኩ ታፍነው ሲወሰዱ የሚዲያው ዝምታ እንድምታ ምንድን ነው ? ?????
በሀገር ውስጥ እየተፈፀመ ስላለ እገታ የሹፌር ተሳፋሪ ግድያ እንዳይዘግቡ የሚያግድ አይተው እንዲያልፉ የሚፈቅድ የሚዲያ ፖሊሲ አለ እንዴ ሳናውቀው ??