
28/09/2025
በአፋር በትራፊክ አደጋ የ4 ሰው ሕይወት አለፈ
*******
በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን ገለኣሉ ወረዳ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ እና ስታስቲክስ ዲቪዠን ዋና ሳጅን ሰዒድ አህመድ ተናግረዋል።
በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች በገዋኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑም ታውቋል።
ዋና ሳጅኑ ከሰመራ እስከ አዋሽ ባለው መንገድ የሚተላለፉ ማንኛውም አሽከርካሪዎች በየመንገዱ እንስሳት፣ ሕዝብ የሚንቀሳቀስባቸው ከተሞች እና ኩርባ መንገዶች ስለሚገኙ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲያሽከረክሩ አሳስበዋል ።