Organic Tigray

Organic Tigray ትግራይ የኢትዮጲያ ሀገረ መንግስት መነሻ ማዕከል ናት። የህወሓትን ቆሻሻ ታሪክ አድሰን ከኢትዮጲያዊ ወንድሞቻችን ጋር ኢትዮጲያን ከፍ እናደርጋለን።

Dawit Kebede ንኢትዮ ፎረም ልኢኹ ዝተጋውሐሉ ፅሑፍ ዘስፈሮ ሓበሬታ መረጋገፂ ስኢነሉ እምበር : ብዛዕባ   ከምዚ ኣላ ክፅሕፍ ወጢነ ነይረ:-=> ከም ፀብፃብ ዳዊት : ሀ) ወዲ ወረደ ...
28/07/2025

Dawit Kebede ንኢትዮ ፎረም ልኢኹ ዝተጋውሐሉ ፅሑፍ ዘስፈሮ ሓበሬታ መረጋገፂ ስኢነሉ እምበር : ብዛዕባ ከምዚ ኣላ ክፅሕፍ ወጢነ ነይረ:-

=> ከም ፀብፃብ ዳዊት :

ሀ) ወዲ ወረደ ንህወሓት ከየማኸረ ንኣለም ገብረዋህድ መንግስታዊ ሹመት ሂብዎ።

ለ) ፖለቲካዊ ሹመቱ ሓያል እዩ። ማሓውራት ወረዳን ጣብያታትን ዝከታተል። እኒ ክቆፃፀሩ ፈቲኖም ዝፈሸለቶም።

ሐ) ወዲ ወረደ ስልጣኑ ንብሄራዊ ሓርነት ከይኾነስ ከምቲ ቕድሚኡ ዝነበረ ግምት ስልጣን ህወሓት ከመዓሪ ተኾይኑ ክጥቀመሉ ዝእምት : ኣለም ንመሪሕነት ህወሓት ንምንስፋፍ ideal ሰብ እዩ። ተሞክሮን ነባር ኔትወርክን ስለዘለዎ።

መ) ግና ህወሓት ሹመት ኣለም ብፖሊት ቢሮ ዘይትሓረየን ዘይፀደቐን ስለዝኾነ : ንወዲ ወረደ ካብ ተግባርኻ ተቖጠብ ኢላቶ። ሹመት ኣለም ተሰሪዙ።

=> እዙይ ማለት:-

ሀ):- ፖለቲካዊ ሂወት ኣለም ገብረዋህድ ኣብቂዑ ማለት እዩ። ህወሓት ኣብዘይትፈልጦን ኣብዘይመደበቶን ዕማም ውዒሉ። ዳርጋ ንመፈንቅላ ስልጣን ኣድብዩ (Conspire ገይሩ) ማለት እዩ።

ለ):- ኣለም ንወዲ ወረደ እውን ተመላሊእዎ ክኾን ይኽእል። ወዲ ወረደ ብጎኒ ንኣለም ክሾም ምንቅስቓሱ ብህወሓት ኣብ ጥርጣረ ክኣቲ ይገብሮ። ቓልሲ ብሄራዊ ሓርነት ክመርሕ ከይኾነ ከምቶም ቐዳሞት ግምት ኣብ ስልጣን ህወሓት ከነፃፅር እዩ ድልየቱ ኢላ ንክትጥርጥሮ መገዲ ይኸፍት።

23/07/2025
"ፕሬዝደንቱ በአስቸኳይ ስልጣን ይልቀቁ"ሳልሳይወያነ
23/07/2025

"ፕሬዝደንቱ በአስቸኳይ ስልጣን ይልቀቁ"ሳልሳይወያነ

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ሕዝብ ጋር በቀጥታ መነጋገር እንዳለበት ተገለጸ+++++++++++++++++  |የትግራይ ሕዝብ ጦርነት አክሳሪ እንደሆነ ከበቂ በላይ ስለተማረ የፌዴራል መንግሥት ከ...
23/07/2025

የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ሕዝብ ጋር በቀጥታ መነጋገር እንዳለበት ተገለጸ
+++++++++++++++++

|የትግራይ ሕዝብ ጦርነት አክሳሪ እንደሆነ ከበቂ በላይ ስለተማረ የፌዴራል መንግሥት ከትግራይ ሕዝብ ጋር በቀጥታ ተገናኝቶ በመነጋገር ያሉትን ችግሮች ሊፈታ ይገባል ሲሉ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የመቐለ ከተማ ነዋሪና የመንግሥት ሠራተኛ የሆነችው ወጣት በረከት ተዓረ ለኢፕድ እንደገለፀችው፤ አሁን እንደ ሕዝብ ያለንበት ሁኔታ በአጭሩ ስገልፀው ‹‹እባብን ያየ በልጥ በረየ›› የሚለውን አባባል ያስታውሰኛል፤ ቀደም ሲል ያሳለፍነው የመከራና የስቃይ ጦርነት፣ ያንን ተከትሎ የመጣው የኑሮ መመሰቃቀል ሲደመር አሁን የክልሉ መሪዎች እየፈጠሩት ያለው ሁከት በፍራቻና ሰቀቀን ውስጥ አስገብቶናል።

የፌዴራል መንግሥት ከእኛ ከተበዳዮችና ሰላም ፈላጊዎች ጋር በቀጥታ ተገናኝቶ ችግሮቻችንን ሊሰማን ይገባል ያለችው በረከት፤ ከሴቶች፣ ከወጣቶችና የመንግሥት ሠራተኞች ጋር በቀጥታ መገናኘት ሲገባው በሶስተኛ ወገን ተመካከሩ ተስማሙ እያለ እስከ አሁን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳናገኝ ብዙ ጊዜ እየፈጀብን ነው፤ ይህም ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ እያመራ መሆኑንና ሕዝቡም ፍርሃት ውስጥ እንደገባ ተናግራለች።

በክልሉ ከነገ ዛሬ ጦርነት ይጀመራል በሚል ስጋት አሁንም ከፍርሃት የመነጨ የሰላም እጦት መኖሩን ጠቁማ፤ የመንግሥት ሠራተኛው በሁለንተናው እየተጎዳና ልጆቹን በሰላም እንዳያስተምር የኑሮ ውድነትና የትምህርት ቤት ክፍያ ተደማምሮ አሁን ላይ የክልሉ መሪዎች በሚፈጥሩት አስፈሪ መግለጫ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ጭንቅ ውስጥ ገብተናል፤ በዚህም ምክንያት እንደ ሕዝብ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን......https://press.et/?p=156200

የወዲ ወረደ ጭምብል ተገልጧል ፤ እያምታታ መቀጠል አይችልም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተሾመው ታደሰ ወረደ ለህዝብ የገባውን ቃል ፣ እራሱ የፈረመውን ስምምነት በመጣስ ላይ ይገ...
23/07/2025

የወዲ ወረደ ጭምብል ተገልጧል ፤ እያምታታ መቀጠል አይችልም

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተሾመው ታደሰ ወረደ ለህዝብ የገባውን ቃል ፣ እራሱ የፈረመውን ስምምነት በመጣስ ላይ ይገኛል:: ታደሰ ወረደ ህዝብ እና መንግስት የሰጠውን አደራ ረስቶ ትግራይን ወደተሻለ ሰላም እና መረጋጋት እመልሳለሁ ፣ ዳግም ግጭት እንዳይቀሰቀስ እሰራለሁ ብሎ የገባውን ቃል ቀርጥፎ በልቶ አሁን ላይ የኋላቀሩን ቡድን ፍላጎት በማስፈፅም ላይ ተጠምዷል:: ሁለት ቦታ እየረገጠ እና የማይጨበጥ አቋም እያንፀባረቀ ለኋላቀሩ ቡድን ሽፋን እየሰጠ የነበረው ታደሰ ወረደ አሁን ፊትለፊት ወጥቶ ግጭትን የሚቀሰቅሱ ንግግሮችን ከማድረግ ጀምሮ ታጣቂዎችን ወደ ማሰማራት ገብቷል::
ፍላጎቱ የትግራይ ህዝብ ጥያቄን በኃይል ማስመለስ ከሆነ ቀድሞውኑ ከፌዴራል መንግስቱ የሚሰጥን ስልጣ ለማግኘት ያን ያክል ደጅ መጥናት ባላስፈለገው ነበር፡፡ የሱ እውነተኛ ፍላጎት ስልጣን መያዝ ከዚያም በግጭት መሃል ተጠያቂነት ስለማይኖር አምስትም አስርም ዓመት ቢሆን በስልጣን ሊያቆየው የሚችለውን ጦርነት መቀስቀስ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ይህ ሰው ጥያቄያችንን የሚፈታው በጦርነት ከሆነ ከፌዴራል መንግስት ህጋዊ ሹመትን መቀበል ለምን አስፈለገው?

ታደሰ ወረደ ከሰፊው ህዝብ ጎን ከማቆም ይልቅ ወደኋላቀሩ ጥቅመኛ ቡድን በማድላት ህዝብን ወደ ሌላ መከራ እና እልቂት እየወሰደ ከሚገኘው ሰሞነኛ እንቅስቃሴው ቆም ብሎ ቢመለስ ለእሱም ሆነ እመራዋለሁ ብሎ በአደራ ለተቀበለው ህዝብ የተሻለ ነው:: ያ አይሆንም ካለ እና ጥቅመኛውን ጠባብ ቡድን ከመረጠ ደግሞ ስልጣኑን ለትግራይ የህዝብ ልጆች በአስቸኳይ ማስረክብ አለበት። እያምታታ የሚቀጥልበት እዚህም እዛም እያረገጠ የሚያጭበረብርበት ጊዜው አብቅቷል።

አሁን በትግራይ ጨለምተኛው የሆነው ብሔርተኛ በአደባባይ እርቃኑን የሚያሳዩን የራስ ኣሉላ አባነጋ ልጆች የተጫነባቸውን የዘር ፖለቲክ  አቧራ፣ እያራገፉ አንገታቸውን ቀና እያደረጉ ነውና ሁሉም ...
21/07/2025

አሁን በትግራይ ጨለምተኛው የሆነው ብሔርተኛ በአደባባይ እርቃኑን የሚያሳዩን የራስ ኣሉላ አባነጋ ልጆች የተጫነባቸውን የዘር ፖለቲክ አቧራ፣ እያራገፉ አንገታቸውን ቀና እያደረጉ ነውና ሁሉም ኢትዮጵያዊ አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ሊላቸው ይገባል። ለዛሬ ኢትዮጵያ ጠል ለሆነው ዶክተር ገብረመድህን በትግርኛ እና በአማርኛ መልስ ከሱጡት መምህር ክብሮም በእራሱ ፌስቡክ ፖስት ያደረገውን አንብቡት።

"Zingo Parlor
#አድርሱልኝ 🙄☝️👏
እባካችሁ ይህንን ጽሑፍ ሼር በማድረግ ለዶክተር ገብረመድህን አድርሱልኝ!



ያነሱትን ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ይህንን መከራከሪያ ነጥብ በክብር አቀርብልዎታለሁ።

"ኢትዮጵያ ስረ-መሰረታዊ (primordial)፣ ሃይማኖታዊ (sacral) እንዲሁም ፖለቲካዊ ዝንባሌ ስለሌላት ሀገራዊ መነሻ የላትም" የሚለው ትርክትዎ፣ ለዘመናት የቆዩ እውነታዎችን የሚፃረር ነው። እነዚህ ሶስት መሰረቶች በኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት እንደዳበሩ በሰፊው እንመልከታቸው፦

✍️1. ሰፋ ያለ የስረ-መሰረታዊ ማንነት ግንዛቤ (Expanded Primordial Identity)፦
ይህ ማንነት የህዝቦችን የጋራ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና መነሻን ይመለከታል። በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌ፣ አፋር ወዘተ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት በአንድ ጂኦግራፊያዊ አካባቢ አብረው ኖረዋል። ይህ አብሮ መኖር ደግሞ፡-

በንግድ ትስስር፦ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝቦች በረጅም የንግድ መስመሮች ተገናኝተውና ተሳስረዋል (ለምሳሌ፡ ከዓዱሊስ ወደብ ወደ ውስጥ አገር የነበረው የንግድ መስመር)።

በጦርነትና በሰላም፦ በመካከላቸው ጦርነቶች እንደነበሩ እውነት ቢሆንም፣ ይህ ጦርነት በራሱ የጋራ ፖለቲካዊ ምህዳር እንደነበረ አመላካች ነው። ከጦርነት በኋላ የሚመጡ ስምምነቶችና የጋብቻ ትስስሮች ደግሞ ማህበራዊ ውህደቱን አጠናክረውታል።

በጋብቻ መተሳሰር (Intermarriage)፦ ለዘመናት የቆየው የጋብቻ ትስስር፣ ግልጽ የሆነ "ይህ የእኔ ብቻ ነው" የሚል መስመር እንዳይኖር አድርጎታል። ይህም ጠንካራ የዘረ-መል (genetic) እና ማህበራዊ ቅይጥ ፈጥሯል።

✍️2. ሰፋ ያለ የሃይማኖታዊ ማንነት ግንዛቤ (Expanded Sacral Identity)፦
ኢትዮጵያ የታላላቅ የዓለም ሃይማኖቶች ማዕከል ናት።

ክርስትና፦ ከአክሱም የሚነሳው ጥንታዊ ክርስትና በመላው ሰሜንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ የጋራ መንፈሳዊ ማንነትን ፈጥሯል። አክሱም ጽዮን ለመላው የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ማዕከል ናት። የትግራይ ገዳማት (እንደ ደብረ ዳሞ)፣ የጣና ገዳማት እንዲሁም ላሊበላ፣ ሁሉም እንደ ሰንሰለት የተያያዙ አንድ ትልቅ መንፈሳዊ ገጽታን ይፈጥራሉ።

እስልምና፦ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሙስሊሞች መጠጊያ (ሂጅራ) መሆኗ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ሀረር ያለች አራተኛዋ የእስልምና ቅዱስ ከተማ እንዲሁም የአል-ነጃሺ ቅዱስ መካነ መቃብር በትግራይ ውስጥ መኖራቸው、 ጥልቅ ታሪካዊ የእስልምና ማንነት እንዳላት ያረጋግጣል።

ባህላዊ እምነቶች፦ እንደ ዋቄፈና እና ሌሎች ያሉ ባህላዊ እምነቶችም የዚህ ሀብታም ማንነት አካል ናቸው።

✍️3. ሰፋ ያለ የፖለቲካዊ ዝንባሌ ግንዛቤ (Expanded Political Orientation)፦
ኢትዮጵያ፣ ከጥንታዊው የአክሱም ስርወ-መንግስት ጀምሮ፣ በዛግዌና በሰለሞናዊያን ስርወ-መንግስታት የቀጠለ፣ ያልተቋረጠ ፖለቲካዊ ታሪክ አላት። "ንጉሰ ነገስት" የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ በራሱ፣ በአንድ ፖለቲካዊ ጥላ ስር የተሰባሰቡ በርካታ ንጉሶችና ህዝቦች እንደነበሩ ያሳያል። አፄ ዮሐንስ አራተኛ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመከላከል መውደቃቸው፣ የጋራ ፖለቲካዊ እጣ ፈንታን የሚገልጽ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።



ክቡር ዶክተር፣ እስኪ ሌሎች ሀገራትን እንመልከት። እንደ ታላቋ ብሪታንያ (እንግሊዝ፣ ስኮትላንድ፣ ዌልስ፣ ሰሜን አየርላንድ) ወይም ስፔን (ካስቲላውያን፣ ካታላናውያን፣ ባስካውያን) ያሉ የኢምፓየር ታሪክ የነበራቸው ሀገራት፣ በኢትዮጵያ ካለው የበለጠ ረጅም የጦርነትና የመለያየት ታሪክ ነበራቸው። ማህበራዊ ውህደታቸው ከእኛ በባሰበት ወቅትም ነበር።

ነገር ግን፣ ችግሮቻቸውን የፈቱበት መንገድ "የጋራ መነሻ የለንም" ብለው ታሪክን በመካድ አይደለም። ይልቁንስ፦

#በህገ-መንግስታዊ_ዴሞክራሲ (Constitutional Democracy)፣

(Rule of Law)፣

በጋራ ዘረኝነትንና መለያየትን በመዋጋት፣

እንዲሁም ለሁሉም ዜጋ እኩል እድልና ውክልናን በሚያረጋግጥ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ነው።



ከላይ የተጠቀሱት ስረ-መሰረታዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ መሰረቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትስስር (strong social and political fabrics) ፈጥረዋል።

#ስለዚህ ጥያቄዬ ይህ ነው፦

እንደ አሜሪካ (በጦርነት የተመሰረተች)፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ስፔን፣ ህንድ፣ ናይጄሪያ ያሉ ሀገራት ከእኛ የከፋ ታሪካዊ ችግሮቻቸውን በዴሞክራሲና በህግ የበላይነት መፍታት ከቻሉ፣ እኛ ለምንድን ነው እውነተኛውን መፍትሄ ትተን የቆየውን ታሪካዊ ትስስራችንን "መነሻ የለውም" በማለት የምናፈርሰው? ችግራችን የሀገር መነሻ ማጣት ነው ወይስ ይህንን የቆየ ታሪካዊ እውነትና ብዝሃነት በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና በህግ የበላይነት ማስተዳደር ያቃተው የከሸፈ ፖለቲካዊ አመራር?

በፍጹም አንድ ብሄር፣ አንድ ማንነት፣ አንድ ሃይማኖት መኖር ሀገር ለመሆን ያስችላል ወይ!?

ከነዚያ "የሸዋ ጨፍጫፊዎች" ብለን ከምንላቸው በላይ እኛ እርስ በእርሳችን እየተጨፋጨፍን አይደለም ወይ!?

በእውነቱ፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሰረታቸው አክሱም እስከሆነ ድረስ、 ስለ ራስ ሀጎስ፣ አሉላ、 ደብረጽዮንና ጌታቸው የሚነሱ የርስ በርስ ግጭቶችንና ጉዳቶችን መመርመር ከማዶ ስላሉት የሸዋና የጎንደር ጉዳይ ከማውራት አይቀድምም ነበር?

ወይስ እንደ ህወሓት ስህተት፣ የህዝብን ጥቅም ወደጎን ብሎ ችግሮችን ሁሉ በውጭ ኃይሎች የማላከክ (too much externalization style) ፖለቲካዊ አካሄድ ስለሚያዋጣ ነው!?

ደህና ሁኑ፣ መልካሙን ሁሉ ለሁላችንም!
መምህር ክብሮም ከአዲስ አበባ

በ1967 ከ50 ዓመት በፊት ህወሓት  ተሓህት እያለ " የመጀመሪያ ጠላታችን አማራ ነው"።በ2017 ከ50  ዓመት በኃላ በህወሓት ስር ያደገ ባህላዊ ዶክተር ገብረመድህን እሱን የመሰሉ ተንጣዮች...
20/07/2025

በ1967 ከ50 ዓመት በፊት ህወሓት ተሓህት እያለ " የመጀመሪያ ጠላታችን አማራ ነው"።

በ2017 ከ50 ዓመት በኃላ በህወሓት ስር ያደገ ባህላዊ ዶክተር ገብረመድህን እሱን የመሰሉ ተንጣዮች "ኢትዮጵያ ቋሚ ጠላቴ ናት" እያለን ነው እኔ መንግሥት ብሆን የመጀመሪያ ስራየ ይህንን ሰው ለያዘው የመንግስት ስራ ማባረር ነበር በተጨማሪም ይህንን የለጠፈች መድህን የተባለች የህወሓት ካድሬ የጋዘጠኝነትዋን ፍቃድ እቀማት ነበር። ምክንያቱም መንግስትን መቃወም መብታችሁ ነው ኢትዮጵያ ከአያቶቻችን ጀምሮ እስከራሴው ድረስ የህይወት እና የአካል መስዋዕትነት የከፈልንባት ስለሆነ በእንደዚህ ዓይነቶች ጋጦጥ ብሔርተኞች ስትሰደን ያመኛል።

የሀዘን መግለጫ!የቀድሞ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ዋልታ ፓሊስ እና መቀሌ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ እንዲሁም ታዳጊዎችን በማብቃት የሚታወቀው ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ ህይወት ማለፉን ክለቡ አስታ...
19/07/2025

የሀዘን መግለጫ!

የቀድሞ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ዋልታ ፓሊስ እና መቀሌ 70 እንደርታ ምክትል አሰልጣኝ እንዲሁም ታዳጊዎችን በማብቃት የሚታወቀው ኮማንደር ዮሐንስ ሲሳይ ህይወት ማለፉን ክለቡ አስታውቋል ።
ለመላው ቤተሰቡ፣ የመቀሌ 70 እንደርታ የቡድን አባላት እና ለወዳጅ ዘመዶቹ ዳጉ ስፖርት መፅናናትን ይመኛል።

Address

Mekelle

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Organic Tigray posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Organic Tigray:

Share