01/02/2023
24/05/2015 T.C
አዲስ ሃይል ፈላጊ ደንበኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
*************
ውድ ደንበኛችን አዲስ ቆጣሪ ለማግኘት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ሲመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን፡፡
"ለነጠላ ፌዝ ቆጣሪ አዲስ ኃይል ጠያቂዎች "
• የአመልካቹ የቀበሌ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፣
• አንድ ጉርድ ፎቶ /3በ4/፣
• የኪራይ ቤት ከሆነ ከባለቤቱ የተሰጠ የስምምነት ደብዳቤ፣
• ለኃይል ማሻሻያ ወይም ለተጨማሪ ቆጣሪ ከሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የመጨረሻ ክፍያ ደረሰኝ፣
• ጥያቄው ለሽርክና ማህበር ከሆነ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሽርክና ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ፤
"ለሶስት ፌዝ እና ለከፍተኛ ኃይል ጠያቂዎች"
• የሃይል ጥያቄው ከ14 ኪሎ ዋት እና በላይ ከሆነ ከላይ ለነጠላ ፌዝ አገልግሎት ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ነክ ሥራዎች ፈቃድ ባለው ተቋራጭ የተሰራ የኤሌክትሪክ ዲዛይን ፕላን፣
• ክፍያዎች (በየጊዜው የሚደረገው የዋጋ ክለሳ እንደተጠበቀ ሆኖ አገልግልቱን ለመስጠት ለሚከናወኑ የኢንስፔክሽን እና ለማስገመቻ ፣
• ለባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ 300 ብር፣
• ከ24 ኪሎ ዋት እስከ 120 ኪሎ ዋት 500 ብር፣
• ከ121 ኪሎ ዋት እስከ 1 ሜጋ ዋት 5000 ብር፣
• ከ 1 ሜጋ ዋት በላይ 10 ሺህ ብር ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት