EthioAfrica news ኢትዮአፍሪካ ዜና

EthioAfrica news ኢትዮአፍሪካ ዜና media outlet

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው። ዘላቂ ሰላምና ልማት ለሀገራችን እንመኛለን።
31/05/2025

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው። ዘላቂ ሰላምና ልማት ለሀገራችን እንመኛለን።

"...ጠ/ሚ አብይ አህመድን መጀመሪያ አከባቢ  ኤርትራ ሄዶ ከተመለሰ በውሃላ የመጀመሪያ ጥያቄ የጠየኩት (ኢሳያስን እንዴት አገኘኸው ?)  የሚለውን ሲሆን ...  አብይ የመለሰልኝ መልስ .....
31/05/2025

"...ጠ/ሚ አብይ አህመድን መጀመሪያ አከባቢ ኤርትራ ሄዶ ከተመለሰ በውሃላ የመጀመሪያ ጥያቄ የጠየኩት (ኢሳያስን እንዴት አገኘኸው ?) የሚለውን ሲሆን ... አብይ የመለሰልኝ መልስ ... (ኢሳያስ ሀገሪቷን ፀሃይ ላይ የታጠለ የደረቀ ቆዳ አስመስሏታል) የሚል አርኪ መልስ ነበር ።

ሌ/ጀነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል

በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የተመዘገቡ ውጤቶች ተሞክሮ የሚሆኑ ናቸው -አቶ ተስፋሁን ጎበዛይለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ከሚገኘው ስልጠና ጎን ለጎን በደቡብ ኢትዮጵያ ክ...
30/05/2025

በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የተመዘገቡ ውጤቶች ተሞክሮ የሚሆኑ ናቸው -አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

ለሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ከሚገኘው ስልጠና ጎን ለጎን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ዘርፍና የደን፣ የፍራፍሬና የመኖ ችግኝ ማባዣ ጣቢያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የመስክ ምልከታ ያደረጉት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ወጣቶች ተደራጅተው በተማሩበት የሙያ ዘርፍ በመሰማራት በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ያስመዘገቡት ውጤት ትልቅ ተሞክሮ የሚገኝበት ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ወጣቶችን በማደራጀትና በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለልማት ስራዎች መሳካት ያበረከተው አስተዋፅኦ የሚደነቅ ነው ሲሉ አንስተዋል።

በለውጡ መንግስት በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን በተለያዩ የኮሚዩኒኬሽን አማራጮች በማስተዋወቅ በድህረ እውነት ዘመን የአጀንዳና የመረጃ የበላይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመልክቷል።

ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዘለፋ ኢትዮጵያ ምላሽ መስጠት አትፈልግም ሲል ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋዎች ምላ...
30/05/2025

ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዘለፋ ኢትዮጵያ ምላሽ መስጠት አትፈልግም ሲል ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋዎች ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቋሙን አሳውቋል።ዛሬ ግንቦት 21 2017 ዓ.ም በወቅታዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረውን ሳምንታዊ መግለጫ፤ በቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በኩል ተሰጥቷል።

ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሁልጊዜም የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እንደምትሰራ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራን የነፃነት ቀን ግንቦት 16 ባከበሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል።ይህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ያስቆጣ ሲሆን፤ የተለያዩ ሀሳቦችም እየተሰነዘሩበት ቆይተዋል።

ይህንን በተመለከት ጥያቄ የቀረበለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በቃል አቀባዩ በኩል ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤ ቃል አቀባዩ “ኢትይዮጵያ ለሚሰነዘሩባት ዘለፋዋች ምላሽ የምስጠት ፍላጎት የላትም” ብለዋል።ኢትዮጵያ የተረጋጋ አካሄድን የምተከተል ሀገር መሆኗን የገለጹት አምባሳደር ነብያት፤ “ከዚህ ቀደምም ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት በመሪዎቹ ደረጃ ተገቢ ያልሆኑ ክሶችና ዘለፋዎች ደርሶባት ያውቃል” ሲሉ ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ግን እንደዚህ ያለ እንካ ሰላምትያ ዉስጥ ሳተገባ በሰከነ ዲፕሎማሲ መንገድ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የምትቀጥል ነው የሚሆነው” ብለዋል።

16/05/2025
ክቡሩ የህክምና ሞያ እና የፖለቲካ አክራሪነት የተምታታበት ሁሉ የሞያ ፍቃዱ በአስቸኳይ ይሰረዛል!መንግስት የጤና ባለሙያዎችን የኢኮኖሚ ጥያቄ እውቅና ሰጥቶ የሀገር አቅም በፈቀደ መሰረት ችግሩ...
14/05/2025

ክቡሩ የህክምና ሞያ እና የፖለቲካ አክራሪነት የተምታታበት ሁሉ የሞያ ፍቃዱ በአስቸኳይ ይሰረዛል!

መንግስት የጤና ባለሙያዎችን የኢኮኖሚ ጥያቄ እውቅና ሰጥቶ የሀገር አቅም በፈቀደ መሰረት ችግሩን ለመፍታት እየሰራ ባለበት ከሙያ ስነምግባር ፍጹም ባፈነገጠ መልኩ መንግስትን እጅ ጠምዘዘን የፖለቲካ ግብ እናሳካለን ላሉ ጽንፈኛ ሃይሎች መጠቀሚያ በመሆን የገቡትን የከበረ ቃልኪዳን በማፍረስ ከሞራልም ከስነምግባርም ያፈነገጠ ተግባር የፈጸሙ የጤና ባለሞያዎች ፍቃድ ከነገ ጀመሮ ይሰረዛል። በዚህም ነገ ጠዋት 2 ሰአት ላይ በስራ ገበታቸው ተገኝተው ተገቢውን ግዴታቸውን ባልተወጡ እና በህሙማን ላይ ጉዳት ያደረሱ የጤና ባለሙያዎች የሞያ ፍቃድ ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰረዝ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ!

ምክር ቤቱ አራት ስምምነቶችን አጸደቀ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት የስምምነት አዋጆችን ...
13/05/2025

ምክር ቤቱ አራት ስምምነቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት የስምምነት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።

በቀዳሚነት የጸደቀው ለአካባቢ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መንግስት መካከል የተደረገው የ11 ሚሊየን 500 ሺህ ዩሮ የብድር ስምምነት ነው።

ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር ያደረገው የ50 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ጸድቋል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በኦስትሪያ መንግስት መካከል የተፈረመው የትራንስፖርት ስምምነት ጸድቋል።

ጀዋር እና የጤና ባለሙያዎቹ ምን እና ምን ናቸው? ጃዋር የሞት ነጋዴ ነው ፣ የጤና ባለሙያዎች ህይወት አድን ናቸው!ጀዋር ደም አፍሳሽ ነው ፣ የጤና ባለሙያዎች እየፈሰስ ያለን ደም የሚያቆሙ ...
09/05/2025

ጀዋር እና የጤና ባለሙያዎቹ ምን እና ምን ናቸው?

ጃዋር የሞት ነጋዴ ነው ፣ የጤና ባለሙያዎች ህይወት አድን ናቸው!

ጀዋር ደም አፍሳሽ ነው ፣ የጤና ባለሙያዎች እየፈሰስ ያለን ደም የሚያቆሙ ናቸው!

የቄሳርን ለቄሳር መተው አይሻልም? ጀዋር የነካው በሙሉ ሞት ጀዋር የነካው በሙሉ ጠፊ መሆኑ ይታወቃል። አሁንም ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተገናኘ በጣም የሚረብሽ መረጃ እየደረሰን ነው :: የሙያተኞቹን ጥያቄ ለራሱ ርካሽ ፖለቲካ እየተጠቀመበት የሚገኘው ጀዋር እና ቡድኑ እንቅስቃሴውን ከሰላማዊ ጥያቄ ወደ ሁከት እና ብጥብጥ ለመቀየር ስትራቴጂ ነድፎ እየሰራ መሆኑን ከውስጥ ታማኝ መረጃ ማግኘት ተችሏል ። እቅዱም የተለመደው የደም ንግድ ነው ። ከባለሙያዎቹ የተወሰኑትን በመግድል በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁከት እና ብጥብጥ በመፍጠር ኢትዮጵያ እንድትወድቅ ማድረግ! የሚያሳዝነው ታዲያ ጥቂት የጤና ባለሙያዎች በገንዘብ ተገዝተው ከሙያ ስነምግባር ባፈነገጠ መልኩ ለዚሁ ሴራ መስማማታቸው ነው :: አብዛኞቹ የጤና ባለሙያዎች ግን ንፁህ የኢኮኖሚ ጥያቄን ይዘው ባለማወቅ ለዚህ ቡድን መጠቀሚያ መሆናቸው ነው።

አሁንም አልረፈደም ! እናስተውል!

መንግስት የጤና ባለሙያዎችን የኢኮኖሚ ጥያቄ ባልካደበት ሁኔታ ይልቁንም ጥያቄውን እውቅና ሰጥቶ ችግሩን በተቻለ መጠን ለመቅረፍ እየሰራ ባለበት ሁኔታ ጥያቄውን በኢትዮጵያ ጠላቶቹ እንዲጠለፍ ለምን ፈቀዱ?

የጤና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የግብርና ባለሙያዎች ሁሉም የኢኮኖሚ ጥያቄ አለው! ጥያቂውን ታዲያ ሀገር በማፍረስ በሁከት በብጥብጥ ነው ማቅረብ ያለበት? ለጠላት ለፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች መጠቀሚያ በመሆን? በፍፁም!

የግብፅ እና የሻቢያ  sub-contractor ጃ-war ቅዱሱ ሙያ ውስጥ ምን ያደርጋል?ጃዋር ቸግሮታል! Political entrepreneur ነው! የፖለቲካ ንግድ ቀዝቅዝበታል። ለዚህም ከ አ...
08/05/2025

የግብፅ እና የሻቢያ sub-contractor ጃ-war ቅዱሱ ሙያ ውስጥ ምን ያደርጋል?

ጃዋር ቸግሮታል! Political entrepreneur ነው! የፖለቲካ ንግድ ቀዝቅዝበታል። ለዚህም ከ አስሪዎቹ ግብፅ እና ሻቢያ አዲስ ፕሮጀክት ቀርፀዋል:: በኢትዮጵያ የሰራተኛ አመፅ እና ብጥብጥ ማስነሳት የሚል :: ለዚህም ባለፉት ወራት ጥናት ሲያደርጉ ቆይተዋል:: ይህም ጥናት በአሰሪዎቹ አዋጭ ተብሏል። እንደ አፈፃፀምም በደሞዝ ጥያቂ ስም አመፅ ማነሳሳት እና የተወሰኑ ሀኪሞችን መግደል የሚለው ተመላክቷል።

ሁሉም የጤና ባለሙያዎች ሊያውቁት የሚገባ የኢኮኖሚ ጥያቄ የሁሉም ነው! ጥያቄው መቅረብ ያለበትም በሰላማዊ መንገድ ነው! ጥያቄያቸው ለጠላት ፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳይሆን ጥንቃቄ መደረግ አለበት!

የፖለቲካ ቁማሩ ተጋለጠየጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ ጃዋር መሐመድ ከርካቶች ጋር በርካታ የስልክ ልውውጦች እና የዙም እንዲሁም የዋትስአፕ ስብሰባዎችን እያደረገ ነው። ሁሉም መረ...
08/05/2025

የፖለቲካ ቁማሩ ተጋለጠ

የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ ጃዋር መሐመድ ከርካቶች ጋር በርካታ የስልክ ልውውጦች እና የዙም እንዲሁም የዋትስአፕ ስብሰባዎችን እያደረገ ነው። ሁሉም መረጃ እጃችን ገብቷል። ጃዋር ይህን እድል መጠቀም አለብኝ በሚል በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ከሚገኙ ተቃዋሚዎች ጋር መክሯል። በምክክራቸውም "የሀኪሞች እንቅስቃሴ ብዙም ጠቃሚ ስላልሆነ ከፍ ወዳለ ህዝባዊ አመፅ መቀየር አለብን" የሚል አጀንዳን አንስቷል። ጃዋር ባደረጋቸው ስብሰባዎች "ተቃውሞው በዋናነት ከኦሮሚያ እና ከአማራ መመራት አለበት ብሏ"። በሱ እቅድ መሰረት የሀኪሞችን ጥያቄ ወደ ህዝባዊ አመፅ ከፍ በማድረግ በታጣቂዎችም እንዲደገፍ እናደርጋለን ብሏል። ለዚህ እቅድ "አቀጣጣይ ነዳጅ ያስፈልጋል" ብሏል። ጃዋር መሐመድ ለዚህ አቀጣጣይ ነዳጅ ብሎ ያቀረበው ሀሳብ "ከታዋቂ ሀኪሞች መስዋዕት" ማድረግ የሚል ነው። ይህም በተጠኑ አባቶርቤ የተባለውን ገዳይ ቡድን መጠቀም ነው። ሀኪሞቹ በብሔር ኦሮሞ እና አማራ መሆን እንዳለባቸውም ጃዋር እና መሰሎቹ ተስማምተዋል። ከኦሮሞ እና ከአማራ ሀኪሞች ከተገደሉ በሁለቱ ክልሎች እሳት ይቀጣጠላል ብለው ተስማምተዋል።

እናም የሀኪሞች ጥያቄን ታዝሎ ስልጣን ለመቆናጠጥ የሚደረጉ ሴራዎች አሁንም ደም ለማፍሰስ ዝግጅቱ ደርቷል። የጤና ባለሙያዎች ጥያቄያቸውን ከጠላፊዎች መጠበቅ አለባቸው። ከፍተኛውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። እራሳቸውን ካልተገባ እንቅስቃሴ ማቀብ አለባቸው። መንግስት ጥያቄያቸውን ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን እየገለፀ ነው። ለፖለቲካ ነጋዴዎች ሲባል ውድ ሀኪሞቻችን እንዲገደሉ አንፈልግም።

ህጉ ምን ይላል?የጤና ባለሞያ ሆኖ አመፅ እና አድማ ማነሳሳት ከሞራል እን ከህሊና በተጨማሪ በህግም ወንጀል መሆኑን ያውቁ ይሆን? አንዴ ደመወዝ ካልተጨመረኝ ብሎ ስራ ካላቆምኩ የሚል ባለሞያስ...
08/05/2025

ህጉ ምን ይላል?
የጤና ባለሞያ ሆኖ አመፅ እና አድማ ማነሳሳት ከሞራል እን ከህሊና በተጨማሪ በህግም ወንጀል መሆኑን ያውቁ ይሆን?

አንዴ ደመወዝ ካልተጨመረኝ ብሎ ስራ ካላቆምኩ የሚል ባለሞያስ እንዴት በጤና ጉዳይ ይታመን ይሆን?

07/05/2025

Address

Mekelle

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioAfrica news ኢትዮአፍሪካ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share