Nigat ንጋት Tube

Nigat ንጋት Tube አዲስ እና ሚገራርም የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ እንዲደርሶ Nigat ንጋት Tubeን ይከተሉ Follow Like Share

23/08/2025

በጥገና ሥራ ምክንያት የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው የክልሉ አካባቢዎች

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ፣ሚዛን አማንና ቴፒ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል ከማከፋፈያ ጣቢያዎቹ የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያገኙ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

በዚህ መሰረት በቀን 18/12/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 12፡00 ሰዓት ድረስ (በቦንጋ፣ ጊንቦ፣ ጎጀብ፣ ጌሻ፣ ጢሎ፣ ጨታ፣ አዲያ፣ ጭሪ፣ ውሽውሽ፣ ሚዛን፣ ቴፒ) ኤሌክትሪክ እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል።
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ክቡራን ደንበኞች የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያስታውቃል።

መልካም ዜና ለኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በሙሉ‼️➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ኢትዮ ቴሌኮም ለ3 ቀናት የሚቆይ 1 ጂቢ ነፃ ኢንተርኔት አበረከተ።ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የተለያዩ የምስጋና ስጦታዎችን አበረ...
24/07/2025

መልካም ዜና ለኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በሙሉ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ኢትዮ ቴሌኮም ለ3 ቀናት የሚቆይ 1 ጂቢ ነፃ ኢንተርኔት አበረከተ።

ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የተለያዩ የምስጋና ስጦታዎችን አበረከተ።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ የምስጋና ስጦታዎችን ለደንበኞቹ አበርክቷል።

በዚህ መሰረትም ለ3 ቀናት የሚያገለግል 1 ጂቢ የኢንተርኔት፣ በየቀኑ የ5 ደቂቃ የድምጽ እና በየቀኑ 8 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ስጦታን ለደንበኞቹ አበርክቷል፡፡

እንዲሁም የ10 ደቂቃ ዓለም አቀፍ ጥሪ የምስጋና ስጦታን ለደንበኞቹ ማበርከቱ ነው የተመላከተው፡፡

ስጦታዎቹን ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ድረስ መጠቀም እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተከትሎ ነው ለደንበኞቹ የምስጋና ስጦታ ያበረከተው፡፡

09/01/2025
አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡ በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid...
09/01/2025

አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡ በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid Belt) ፈጥረው ጸሐይን ይዞራሉ፡፡

እነዚህ የሰማይ አካላት ግዙፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹም በመቶ ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ዲያሜትር ያላቸው ናቸው፡፡ በአንፃሩ ሜትሮይትስ (Meteorites) ወደ ምድር ከባቢ አየር የገቡ የአስትሮይዶች ወይም ኮሜት ቁርጥራጮች ናቸው። በሌሊት ሰማይ ላይ የምናያቸው የብርሀን ጅራቶች ሜትሮይድ (Meteoroid)፣ ትንሽ የጠፈር አለት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገባና ሲቃጠል የሚፈጠር ነው።

የሜትዮር ሻወር (Meteor Shower) አስደናቂ የብርሃን ትዕይንት በሰማይ ላይ የሚፈጥሩ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ሜትሮይዶች ጥቃቅን እና መሬት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የሚጠፉ ናቸው።

በመጠን የገዘፉ እና ጠንካራ የሆኑት አለቶች ከእሳታማው መተላለፊያ እና የመሬት ከባቢ አየር ተርፈው መሬት ላይ ይደርሳሉ።

Meteorites ከተለመዱት የምድር አለቶች የሚጋሩት ነገር ቢኖርም በራሳቸው ደግሞ የተለየ ስሪት እና አወቃቀር ያላቸው በመሆኑ በአይን በማየት ብቻ ለመለየት አዳጋች ይሆናል፡፡ የመስኩ ተመራማሪዎች የሜትሮይትን ስብጥር ለመተንተን የረቀቁ ቴክኒኮችን እና የሳይንስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ። ይህም የማዕድን ይዘቱን ለመመርመር ከምድር ውጭ ያሉ ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን መለየት እና የተረጋጋ የአይሶቶፖች ምጥጥንን (isotope ratio) መለካትን ጭምር ያካትታል። እነዚህ ትንታኔዎች የሜትሮይትን አመጣጥ እና ስለ መነሻ ምንጫቸው አስመልክቶ ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳሉ።

ሜትሮይት በምድር ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ እና ጉዳት በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ በየዓመቱ ወደ ምድር ገጽ የሚወርዱትም በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኛው አካላቸው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ሲያልፍ ተቃጥሎ ስለሚያልቅ፤ የሚያደርሱት ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉልህ የሆነ ውድመት ሊያስከትሉ የሚችሉት በሚሊዮን አንዳንዴም በሺህ ዓመታት የሚከሰቱት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ አኳያ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቴሌስኮፖችን በመጠቀም ካለማቋረጥ እንቅስቃሴያቸውን በንቃት በመከታተል ከፍተኛ ጉዳት ለያመጡ የሚችሉትን አስቀድሞ በመለየት የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ።

Follow Nigat ንጋት Tube

ምንጭ፡ Space science and geo-spatial institute

ገበያ ላይ የማይገኘውና ፡  አትሌቶቻችንን ጨምሮ ፡ ለሁሉም ተሳታፊዎች  ሰምሰንግ የሰጣቸው ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ስልክ ።ሰሞኑን ሲካሄድ በሰነበተው የፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ ካየናቸው ለ...
13/08/2024

ገበያ ላይ የማይገኘውና ፡ አትሌቶቻችንን ጨምሮ ፡ ለሁሉም ተሳታፊዎች ሰምሰንግ የሰጣቸው ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ስልክ ።

ሰሞኑን ሲካሄድ በሰነበተው የፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይ ካየናቸው ለየት ያሉ ነገሮች መሀል ፡ አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች ፡ ሜዳልያ አሰጣጥ ስነስርአት ላይ ፡ በትንሽ ስልክ ሰልፊ ሲነሱ አይተናል ።

Galaxy Z Flip6 Olympic Edition ይባላል ። ይህ ስልክ ዝም ብሎ ስልክ አይደለም ። የፓሪሱን ኦሎምፒክ የክብር ስፖንሰር በሆነው ሰምሰንግ ኩባንያ ለዚህ ኦሎምፒክ ሲባል ብቻ የተሰራ ፡ 50 ሜጋ ፒክስል የፎቶ ጥራትና በውስጡ የተለያዩ ፊውቸሮችን የያዘ ስልክ ሲሆን ፡ ሌላ ጊዜ ለገበያ እንደሚቀርቡት በሚሊየን የሚቆጠር ስልክ አልተመረተም ፡ በፓሪስ ኦሎምፒክ በሚሳተፉ አትሌቶች ቁጥር 17 ሺህ ስልኮችን ብቻ ነው የሰራው ።

እናም በፓሪሱ ኦሎምፒክ ተካፍለው ፡ ላሸነፉትም ሆነ ባጠቃላይ ለተሳተፉ አትሌቶች የተሰጠውን ፡ ይህን ስልክ ሲከፍቱት ፡ እንኳን ወደ ፓሪስ በደህና መጡ የሚል ቴክስት ይቀበላቸዋል ።

ከዚያም በስልኩ መጠቀም ሲጀምሩ ፡ በፓሪስ በሚቆዩበት ቀናት ሁሉ ወደፈለጉበት ቦታ በነጻ መደወል ፡ ቴክስት ማድረግና ፡ ኢንተርኔት መጠቀም የሚችሉበት ነጻ ፓኬጅ መጠቀም ይችላሉ ።

ይህ ብቻ አይደለም ፡ ይህን ስልክ ይዘው ፡ ወደየትኛውም የፓሪስ አካባቢዎች ሲጓዙ ፡ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስልኩን በማሳየት በነጻ መጓዝ ያስችላቸዋል ።

በዚህ ወቅትም ለስላሳ መጠጦችንና ጭማቂ መጠጣት ካማራቸው ፡ ከነሱ የሚጠበቀው ለስላሳ ወደሚሸጠው ማሽን ጠጋ ብለው የስልኩን QR code ማስነበብ ብቻ ነው ።

Galaxy Z Flip6 ስልክ. .. 8 GB Ram እና 256 GB ስቶሬጅ ያለውና ፡ ያለ ቻርጀር ገመድ በ15 ዋት ስፒድ ቻርጅ መደረግ የሚችል ሲሆን ፡ አንዴ ቻርጅ ከተደረገ ለ68 ሰአታት ሙዚቃ ወይም ለ23 ሰአታት ቪዲዮ ማየት ያስችላል ።

እንዲሁም የዚህ ስልክ መያዣው ቤርሉቲ በሚባል የቅንጦት እቃዎችን በሚያመርት ካምፓኒ ፡ ቬንዚያ ከሚባል ሌዘር የተሰራ ነው ። የሴኪውሪቲ ፊውቸሩ ፡ የአትሌቶችን ፕራይቬሲ እንዲጠብቅ ተደርጎ የተመረተ ነው ።

ባጠቃላይ ይህ ሰምሰንግ ለፓሪሱ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎች ብቻ የሰራው ታጣፊ ስልክ እጅግ ዘመናዊ ሲሆን በገበያ ላይ ያልዋለ ለአትሌቶች ብቻ የተሰጠ መሆኑ ዋጋውን እጅግ አስወድዶታል ። እና በአንዳንድ የኦንላይን ገበያዎች ስልኩን ከሚሸጡ አትሌቶች የተገኙ ውስን ስልኮች ፡ በተለይ ምንም ያልተከፈተ ከሆነ ፡ ከአምስት ሺህ ዶላር በላይ ማለት በኛ ወደስድስት መቶ ሺህ በሚገመት ዋጋ እየተሸጠ ነው ።
✍️ዋሲሁን ተስፋዬ

20/06/2024

የጤና ሚኒስቴር ከክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭ እና ቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፋይናንስ ስርዓት ለመከታተል የሚያስችል ዲጂታላይዝድ አሰራር ለመተግበር ባዘጋጀው መነሻ ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት አካሂዷል።
________________

በጤና ሚኒስቴር የሚኒስቴር ፅ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ሩት ንጋቱ የጤናውን ዘርፍ ሀብት አጠቃቀም ወጥና ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር እንደሚያስፈልግ ተናግሮ የተሻሻለው የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ የጤና ፋይናንሲንግ ማጎልበት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ እንዲሁም የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ወቅቱን የጠበቀ ውሳኔ ለማስተላለፍ ያለውን ሚና ገልፀው፤ በዚህ የጤና ፋይናንስ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ላይ ቴክኒካል ድጋፍ ያደረጉትን CHAI እና ቢልና ሚልንዳ ጌትስን በጤና ሚኒስቴር ስም አመስግነዋል።

በክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭ ካንትሪ የዳይሬክተር ዶ/ር ራሔል በለጠ እንደተናገሩት ጤና ሚኒስቴር ከትሬዠሪ የሚመደብለትን መደበኛ በጀትና ከለጋሽ ድርጅቶች የሚያገኛቸውን ሀብቶች ለመከታተል የሚያስችለው አሰራር ስለሆነ ወቅቱን የጠበቀ የአፈፃፀም ሪፖርት ለማቅረብ ከማስቻሉም በላይ ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለማስተላለፍ እንደሚያበቃ ተናግረዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር የIFMIS እና IBEX ፕሮጀክቶች ኃላፊ አቶ መኮንን ገዳ በዙም ውይይት በመሳተፍ ገንዘብ ሚኒስቴር በአገሪቷ ያሉትን የፋይናንስ ስርዓቶች የሚመራ አካል እንደመሆኑ የዘመነ የፋይናንስ ስርዓት ኢኒሼቲቮች የሚተገብሩ ተቋማትን እንደሚያበረታታ እንዲሁም በባለቤትነት በመገምገም አቅጣጫ እንደሚሰጥም ገልፀዋል። አቶ መኮንን አክለውም የጤና ፋይናንስ ፍኖተ ካርታው ረቂቅ ላይ አስቀድመው ውይይት እንደተደረገበት ጠቅሰው፣ አገር አቀፍ ጥናታዊ ውጤት ሪፖርቱን ለገንዘብ ሚኒስቴር መላክ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭ የሩዋንዳ ተጠሪና የግሎባል ዲጂታል ጤና ቴክኒካል አማካሪ ቡቶሎንኮሲ ሞዮ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጠቀሜታን ከአለም አቀፍ እስከ አሁጉራችን ያለውን ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማመሳከር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በአለም ባንክ የጤና ኦፕሬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ባለሞያ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ጤና ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ለመንግስት የመደበኛ በጀትና ከለጋሽ ድርጅቶች የሚያገኛቸውን ሀብቶች ፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች የሚመጣውን የአፈፃፀም ሪፖርት ሂደት ገልፀው አሁን የሚተገበረው ዲጂታላይዝድ የጤና ስርዓት ፍኖተ ካርታ ክልሎች የሚያከናውኑትን በእጅ ፅሁፍ የሚመዘገበውን መረጃ አያያዝ ሙሉ ለሙሉ ካላስቀረ በአንድ ቋት የሀብት ፍሰቱን ለመከታተል እርስ በርሱ ተመጋጋቢ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዚህ አውደ ጥናት ውይይት ላይ የለጋሽ ድርጅቶች ተወካይ፣ የክልል ጤና ቢሮ እና የፌደራል ሆስፒታሎች የዲጂታል ጤና የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው አገር አቀፍ የጤና ፋይናንስ ሃብት አመዳደብና አጠቃቀምን ለማዘመን በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ላይ በመወያየት የጤና ዘርፍ የፋይናንስ የሃብት አመዳደብና አጠቃቀም ወጥና ዘመናዊ (Digitalizing Health Resource Tracking) በጤናው ዘርፍ ያለውን የጤና ፋይናንስ የሃብት አሰባሰብ፥ አመዳደብና አጠቃቀምን ማዘመን ወይም ዲጅታላይዝ ማድረግና በሚተገበረው የዲጅታል መረጃ ስርዓት የመረጃ ልውውጡ በሁሉም ደረጃ የሚናበብና የሚመጋገብ እንዲሆን ወቅቱን የጠበቀና ጥራት ያለው የጤና ፋይናንስ መረጃ እንዲኖር ለውሳኔ የሚረዱ መነሻ ሀሳቦች በግብአትነት ተሰተዋል።

Website: moh.gov.et
Facebook: Minis

20/12/2023
20/12/2023
20/12/2023

Address

Mizan Teferi

Telephone

+251904077122

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigat ንጋት Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category