01/10/2024
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቀድሞውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዷለም አድማሴን የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ አድርጎ መሾሙ ታውቋል።
ዶ/ር አንዷለም ከዚህ በፊት በግዙፉ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚነት እንዲሁም በደቡብ ሱዳን ውስጥ ከሌሎች ግለሰቦች ጋር ባቋቋሙት አዲስ የቴሌኮም ኩባንያ በኃፊነት በመሥራት ላይ ነበሩ ተብሏል።
ሳፋሪኮም ኩባንያ አዲሱ የሾማቸው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ በቴሌኮምኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያካበቱትን ልምድ በመጠቀም የኩባንያውን ስኬታማነት ያስቀጥላሉ መባሉን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቦታል።