
12/07/2025
ሐምሌ 5
ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
የዮና ልጅ ስምዖን ጴጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው።
በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ አድጐ፣ ሚስት አግብቶ ዕድሜው ሃምሳ ስድስት ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ፣ በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል።
(ማቴ. ፲፮፥፲፯ ፣ ዮሐ. ፳፩፥፲፭)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሠራው ስሕተት ንስሐ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የእርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል።
በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል። አሕዛብ ግብራቸው የከፋ ነውና በኔሮን ዘመነ መንግስት በ88 አመቱ አካባቢ ሰማዕት ሁኗል።
የቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከታቸው ትድረሰን