
25/08/2024
የነሐሴ 19 ቀን 2016 የዓለም ዜና
በየመን የባሕር ዳርቻ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በመስቸሟ ቢያንስ 13 ሰዎች ሲሞቱ 14ቱ እስከአሁን ደብዛቸው አልተገኘም።
ጀልባዋ 25 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና 2 የመናውያን የጀልባዋ ቀዛፊዎች አሳፍራ ከጅቡቲ የተነሳች ሲሆን በየመን የባሕር ዳርቻ እስከአሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መስጠሟ አለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ IMO አስታውቋል።
ሂዝቦላህ ከ320 ሚሳይሎችን በእስራኤል ላይ ማዝነቡን አስታወቀ። እስራኤል በበኩሏ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ናቸው ባለቻቸው በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ ኢላማዎች ላይ መጠነሰፊ የአየር ጥቃት መፈጸሟን የሐገሪቱ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል። በጥቃቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ ሮኬት ማስወንጨፊያዎች መውደማቸውንም አክሏል።
በፓኪስታን በደረሱ 2 የተለያዩ የአውቶብስ መገልበጥ አደጋዎች 44 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከሞቱት 12ቱ ለሐይማኖታዊ ሥነ-ስርዓት ሲጓዙ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
ሩስያ ለዛሬ አጥቢያ ሌሊት በሰሜንና ምዕራብ ዩክሬይን በፈጸመችው የድሮንና የሚሳይል በርካታ ጥቃቶች ቢያንስ 1 ሰው ሲሞት 29 ሰዎች መጎዳታቸውን የዩክሬይን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ፖለቲካኢትዮጵያየነሐሴ 19 ቀን 2016 የዓለም ዜናTo play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoፖለቲካኢትዮጵያYohannes Gebreegziabher19 ነሐሴ 2016እሑድ፣ ነሐሴ 19 2016https://p.dw.com/p/...