10/06/2026
ዳሸን ባንክ ለክቡር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ልዩ ዕውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡
---------------------------------------------------------------------
ባንኩ ሽልማቱን ለክቡር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ያበረከተው፤ ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ገናና ተቋም እንዲሆን ስያሜ ከመስጠት ጀምሮ፣ የባንኩ ምስረታ ዕውን እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ በማድረጋቸው ነው፡፡
ክቡር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በመሰማራት ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ሰው-ተኮር በጎ አድራጎቶች ላይ በፈር ቀዳጅነት በመሳተፍ ለሀገር ዕድገት አቻ የሌለው ሚና እያበረከቱ የሚገኙ ባለሀብት ናቸው፡፡
ዳሸን ባንክ እውቅናውን የሰጠው 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ የማጠቃለያ ፕሮግራም ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
MIDROC Investment Group ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
የሀገር ሀብት!