Gesuba times

Gesuba times Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gesuba times, Media/News Company, Wolayita, Sodo.

"ውሾች ይጮኻሉ፣ ግመሎች ይራመዳሉ" እያሉ የሚሳለቁብንን ሰዎች ስመለከት... እነዚህ "ውሾች" የሚሏቸው የዋሁንና ታጋሹን ህዝባችንን ይሆን?የሚል ጥያቄ አነሳብኝ✍️አንድ እውነት አለ... ዛሬ...
05/07/2026

"ውሾች ይጮኻሉ፣ ግመሎች ይራመዳሉ" እያሉ የሚሳለቁብንን ሰዎች ስመለከት... እነዚህ "ውሾች" የሚሏቸው የዋሁንና ታጋሹን ህዝባችንን ይሆን?የሚል ጥያቄ አነሳብኝ✍️

አንድ እውነት አለ... ዛሬ ህዝብ ዝም ያለው ስለተመቸው ወይም ስለማያውቅ አይደለም። በፍርሃት፣ በቁጭት እና "ከዛሬ ነገ ይሻላል" በሚል ተስፋ ውስጥ ሆኖ ነገሮችን በትዕግስት እያየ ነው። ዝምታ ሰላም ማለት አይደለም፤ የንቀትና የበደል ጽዋ ሲሞላ ግን የዝምታው ፍንዳታ ያስፈራል። ዝምታውን ፍሩት!

ለወላይታ መብት መታገል ዛሬ ሳይሆን ትላንት ነበረበት! ካልታገለን፣ የራሳችንን መብትና ክብር ካላስከበርንማ የሌሎች ባሪያ መሆናችን እኮ የሩቅ አይሆንም። የባርነት ስሜት ምን ያህል ተስፋ አስቆራጭና አንገት አስደፊ እንደሆነ ያየውና የቀመሰው ብቻ ያውቀዋል። መብትና ግዴታ ምን እንደሆነ... በሰው ስር "ጆሮ ጠብ" ሆኖ ሶስት ድግሪ ለተሸከመ አሽቃባጭና ሆድ አደር መቼም አይገባውም!

የወላይታ ችግር የሁላችንም፣ የሁላችንም ቤት ያንኳኳ ህመም ነው። ወላይታ የሌለባት፣ ክብሯ የተናቀባት ኢትዮጵያ ለእኔ ምን ትጠቅመኛለች? ይህ የሚገባህ ግን ከቤት ወጥተህ በሰው ሀገር ስትኖር፣ ማንነትህ ሲናቅ ብቻ ነው። ከቤት ያልወጣ፣ ችግር ያላየ ሰው ስለ ወላይታ ክብርና ጥቅም አይገባውም። ለዚህ እኮ ነው የማንም ተላላኪ መጥቶ የነገረውን የሀሰት ተረት እንደ እውነት ተቀብሎ ወላይታንና ወገኑን አሳልፎ የሚሸጠው! የሌላ ሀገር ሰው በወላይታ መሬትና ላብ በልጽጎ፣ በገዛ ሀገሩ ላይ ይሰራል የእኛዎቹ የገዛ አባቱን እናቱን ሃገሩን ይሰርቃል።

ይህ ቁጭት የሁላችንም ነው። ዝምታችንን ፍሩት! የህዝብ እምባ በመሬት አይቀርም!

🚨 ሰበር ዜና፦ በገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች “የተደበቀ ጩኸት” እና የተጋለጠው የአመራር ብልሽት!በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩ አስተዳደራዊ በደሎች የትውልድን ተስፋ እያጨ...
22/04/2026

🚨 ሰበር ዜና፦ በገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች “የተደበቀ ጩኸት” እና የተጋለጠው የአመራር ብልሽት!
በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታዩ አስተዳደራዊ በደሎች የትውልድን ተስፋ እያጨለሙ መሆናቸው ተሰማ። በዛሬው ልዩ ዘገባችን በገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በርዕሰ መምህር እንድሪያስ አየለ እየተመራ ያለው አስተዳደር፣ ተማሪዎችን ለከፋ ስነ-ልቦናዊ ጫና እና እንግልት እየዳረገ መሆኑን
በገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ተገኝተን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች የሚናገሩት ታሪክ የሚሰማ ጆሮ ላለው ሁሉ እጅግ አሳዛኝ ነው። ተማሪዎቹ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በአቶ እንድሪያስ አየለ ላይ የሚያነሱት ቅሬታ አሁን ላይ "የድረሱልን" ጥሪ መሆኑን አረጋግጠናል።
ከተማሪዎች ጋር ባደረግነው ቆይታ ያሰሙን ዋና ዋና ቅሬታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1.የውሸት ስታቲስቲክስ ወይስ የትውልድ ግድያ?
ርዕሰ መምህር እንድሪያስ አየለ ለራሳቸው "ተሸላሚነት" እና ለትምህርት ቤቱ "የማለፍ ፐርሰንት ጭማሪ" ሲሉ ብቻ፣ ደካማ ተማሪዎችን "ከፈተና አስቀራችኋለሁ እናንተ ተፈትናቿም ያው ናችው የት/ት ቤታችንን የማሳለፍ ፐረሰንት ከፍ ለማድረግ 50 ተማሪ ከተፈተነ ይበቃል" እያሉ በማስፈራራት ቁጥራቸውን ለመቀነስ እንደሚሞክሩ ተማሪዎች ተናግሯል።ተማሪዎች አክለውም ተማሪ አስፈትኖ ውጤታማ ከማድረግ ይልቅ፣ ተማሪዎችን በማሸማቀቅና በማግለል የሚመጣ የውሸት ሪፖርት "የትውልድ ግድያ ነው" ሲሉ ተማሪዎቹ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
2."አቴንዳንስ" እንጂ ትምህርት የለም!
ተማሪዎች ከሩቅ መንገድ ተጉዘው በትምህርት ጥም ወደ ትምህርት ቤቱ ቢመጡም፣ መምህራን ክፍል ገብተው እንዲያስተምሩ የመቆጣጠር ብቃት ያለው መሪ አለመኖሩ ትልቅ ክፍተት ሆኗል። "መምህር አጥተን ባዶ ክፍል ስንቀመጥ ዝም የሚሉት ርዕሰ መምህሩ፣ ለአንድ ቀን የቀረውን ተማሪ ለመጣል ግን የሳምንቱን ስም በአንድ ቀን ይጠራሉ" ሲሉ ተማሪዎች የአመራር ውድቀቱን ገልጸዋል። ዛሬ በገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው የሚመጣው ለእውቀት ሳይሆን ርዕሰ መምህሩን ፈርቶ ለስም ጥሪ ብቻ ሆኗል ስሉ አጥብቆ ምርታቸውን ገልጿል።
3.አቅም ያለው ሲሸሽ—ድሃው ተማሪ መከራውን እያየ ነው!
በዚህ አምባገነናዊና "ራስ ምታት" በሆነ አሰራር ምክንያት፣ አቅም ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን በየአመቱ 12ኛ ክፍል ስደርሱ እያወጡ ወደ ሶዶና ሌሎች አካባቢዎች ለትምህርት እየሰደዱ መሆኑንና በትምህርት ቤቱ የቀሩት አማራጭ የሌላቸው የድሃ ልጆች ደግሞ በርዕሰ መምህሩ ዛቻና ማስፈራራት ስር መውደቃቸውንና ስነልቦናዊ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጿል። የአሁኑ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች "እኛ እድላችንን አግኝተናል፤ ነገር ግን የቀጣይ ትውልድ ነገር በጣም አሳስቦናል" ስሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከተማሪዎቹ አንደበት የሰማነው ይህ መራራ ድምፅ የሚያሳየው፣ የገሱባ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት ከመማሪያ ማዕከልነት ይልቅ ወደ "የፍርሃት ቀጠና" መቀየሩን ነው። በአንድ ርዕሰ መምህር ግትርነትና የዝና ፍላጎት ምክንያት የሺዎች ተማሪዎች ተስፋ እንዲቀጭ መፍቀድ የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል።
ስለሆነም፣ የከተማው ትምህርት ቢሮ ካሳየው አጨብጫቢነት ወጥቶ፣ የዞንና የክልል የትምህርት መመሪያዎች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት አካላት ጉዳዩን በገለልተኛ ወገን በአስቸኳይ እንዲመረምሩትና ተማሪውን ከዚህ "ራስ ምታት" እንዲታደጉት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።ትምህርት ቤት የተማሪዎች የወደፊት ተስፋ መገንቢያ እንጂ፣ እንደ አቶ እንድሪያስ አየለ ላሉ ግለሰቦች የውሸት ስታቲስቲክስ ማምረቻና የዝና መወጣጫ ሊሆን አይገባም!

Address

Wolayita
Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gesuba times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share