
28/07/2025
#ሦሰት ቀን ብቻ ቀረ
🌿🎄🎄🎄🎄🎄🎄
#"በመትከል_ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 24/2017 ዓ/ም የወረዳችን አጠቃላይ ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ችግኝ በመትከል የበኩሉን ድርሻ በአገባቡ ሊወጡ ይገባል፥ አቶ ደግፌ ኤርሚያስ
የወላይታ ዞን ሚልሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኤርሚያስ የዘንድሮ አንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አስመለክቶ ያስተላለፉት መልዕክት፥
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መሪነት ላለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገራችን አየር መዛባት ለመቆጣጠር እና በምግብ ዋስትና ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የተቻለ እንዲሁም ከሀገር አልፎ በአፍሪካና በአለም ደረጃ ምርጥ ተሞክሮ የሚሆን ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ይህ የችግኝ ተከላ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ዘንድ ተቀባይነት ያገኘና የአከባቢው ገፅታ በመቀየር ለመኖር ምቹና ሳቢ እንዲሁም ከሰው ልጆች ጀምሮ ለአጠቃላይ ፍጥረታት ጤና ወሳኝ እየሆነ የመጣት ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል።
ይህንን ስራ በተሻለ ሁኔታ ለማስቀጠል በዘንድሮ ዓመት እንደ ሀገር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል 700 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል በተያዘው ዕቅድ መነሻ እንደ ወረዳችን ከ912,667 ዘጠኝ መቶ አስራ ሁለት ሽህ ስድስት መቶ ስልሳ ሰባት በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ሰፊ ስራዎች እተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በዚህም በወረዳችን ያሉ ከህጻናትና ከወጣቶች ጀምሮ አጠቃላይ የማህበረሰብ ክፍሎች በቀን 24/11/2017 ዓ ም ዕለተ ሐሙስ ሙሉ ቀን በዚህ ተግባር ላይ መዋል እንዳለባቸው ተጠቁመዋል።
በዕለቱ በወረዳ ደረጃ 912,667 ዘጠኝ መቶ አስራ ሁለት ስድስት መቶ ስልሳ ሰባት ችግኝ ለመትከል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ያለ ሲሆን በሁሉም ቀበሌ በተዘጋጀው ተከላ ቦታ ወይም በXY-ኮርድኔት በተያዘው ቦታ ላይ ጥራትን የጠበቀ ስራ ሌሊት 12 ሰዓት ጀምሮ ቀን ሙሉ መከናወን እንዳለበት ተገልጿል።
በዚህም ለንቅናቄው ስኬታማነት ከወዲሁ የተሻለ እንቅስቃሴ መደረግ ስለሚያስፈልግ የችግኝ ዝግጅትና ወደ ስፍራው የማጓጓዝ ስራ፣ የጉድጓድ ዝግጅት፣ የቅስቀሳ ስራ፣ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦትና ሌሎች ተግባራት በዘርፉ አመራሮችና በባለድርሻ አካላት በጥብቅ ድሲፕሊን መመራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
"በመትከል ማንሰራራት" የዘንድሮ አንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሰው እርስ በርስ ተቀናጅቶ ተናብቦ መስራት የየራሱን ድርሻ በአገባቡ መወጣት እንደሚገባ ተጠቁመዋል።