
10/04/2025
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አበባየሁ ዮሐንስ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን ያሉበት ደረጃ ለማየት መስክ ምልከታ አደረጉ 🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🥀🥀🥀🥀🎋🎋
፣ ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም
የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አበባየሁ ዮሐንስ የ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የአሬንጓዴ አሻራ ቅድሜ ዝግጅት ስራዎችን ያሉበት ደረጃ ለማየት መስክ ምልከታ አደረጉ።
🌲🌲በምልከተው ለአሬንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ዘርፈ ብዙ ጠቀመታ ያላቸውን የተለያዪ የደን ችግኝ ስራዎች ያሉበት ደረጃ እና ለበልግ ተከላ የደረሱ ችግኞችንና ለበልግ ወቅት ችግኝ ተከላ እየተዘጋጀ ያለው ጓድጓድ ቁፋሮ ሰራም ጭምር ታቅዶ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ትልቅ ለአረንጓዴ አሻራ ለትውልድ ቅርስ መሆኑን ተመላክቷል።
🌲🌲በግብርና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እና ሌሎችም የግብርና ልማት ስራዎችን ያሉበት ደረጃ ተዘዋውረው ጎበኝተዋል።
በመስክ ምልከታው የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አበባየሁ ዮሐንስ፣ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸው በቀለ፣ የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ምሁራን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ላምበቦ ቡልአሞ ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በጉብኝት ቦታ ተገኝተዋል።