Soddo Ethiopia Catholic Andinet

Soddo Ethiopia Catholic Andinet Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Soddo Ethiopia Catholic Andinet, Media, Sodo.

🤲🤲🙏🙏🙏
16/11/2025

🤲🤲🙏🙏🙏

‎ ‼️
‎እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ክብሩን ይውሰድ!!
‎ዳግም የደስታ ብስራት ለሀገረስብከታችን፣ ዳግማዊ መስከረም አምስት፣ እጅጉን ደስ እያለን ፈጣሪን የምናመሰግንበት ሰበር እነሆ።

‎በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሶዶ ሀገረስብት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ደጀነ ሂዶቶ ክቡር አባ አለማየሁ ወ/የሱስን የገሀገረስብከቱ ጳጳስ እንደራሴ (Diocesan Director and Vicar Delegate) ሆነው እዲደያገግሉ ኃላፊነት ሰጥተዋል።

‎ # ክቡር_አባ_አለምአዬሁ_ወልደየሱስ ከዚህ በፊት የበሌ ሀዋሳ ፍልሰታ ማርያም ቁምስና ቆሞስ በመሆን እያገለገሉ የቆዩ ሲሆን፣ በተለያዩ ቁምስናዎች በማገልገል ስኬታማ የሆኑ፣ በሁሉም ማህበረሰብ ዘንድ ተወዳጅና፣ እጅግ ትሁት፣ሩህሩህ፣ ለብዙዎች ምሳሌ የሚሆኑ፣ በሁሉም ምዕመናን እጅጉን የሚወደዱ ታታሪ የስራ ሰው ናቸው፣ በተለይ ለወጣቶችንና ህጻናት ጊዜያቸውን ሰጥተው የሚያስተምሩ፣ የሚመክሩ በብዙ የሚያደምጡ፣ የምዕመናን ቤት በመጎብኘትና ፣ በጸበል ቤታቸውን በመባረክ ተደራሽ እና ጠቃሚ የሆነ መንፈሳዊ ምክር በመለገስ ጠንካራውን ይበልጥ የሚበረታቱ ደካማውን ከድካሙ ለመመለስ የሚጥሩ እጅግ ታታሪ አባት ናቸው።

‎ይህ ሆኖ ያየነው በብጹዕነታቸው አስተዋይነት፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት መሆኑ እውን ነው። በእውነቱ ሁሉም ሰው በልቡ የተመኘው፣ ቢሆን ብሎ ያሰበው፣ በጸሎቱም ወደ ፈጣሪ የጠየቀው የብዙዎች የልብ መሻት እንደሆነ እናውቃለን። በዚህ አጋጣሚ ብጹዕነታቸውን ከልብ እናመሰግናለን፣ ሀገረስብከታችን በብዙ አቅጣጫ አዎንታዊ ለውጥ ላይ መሆኑኗን በተግባር እያሳዩን ስለሆነ በሚሆነው ሁሉ ደስታችን ወደር የለውም፣ የአንድ ተቋም ስኬቱ መዋቅራዊ አደረጃጀቱ( The success of every organization is its strong structural foundations ) መሆኑ ይታመናል፣ በመሆኑም ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ ትልቅ ክህሎት እና ብስለትን የሚጠይቅ ሲሆን ይህንን እርስዎ ከእግዚአብሔር የተቸሩት ስጦታ ነውና ፈጣሪን እናመሰግናለን። ሌላው በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በእርስዎ አስተዋይ መሪነት ፣ በመርህ ውስጥ በመሆን ላደረጉልን ድንቅ ለውጦች በተለይ በወጣቱ እና ህጻናት ላይ ለተደረጉ እጅግ ሳቢና የወደፊቷን ቤተክርስቲያን ተስፋ የሚያለመልሙ መርሀግብሮች ላይ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ተግባር ድረስ ለተከወኑ ልዩ ልዩ ስራዎች እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ ቸሩ መድሀኒአለም በነገር ሁሉ ይርዳዎት፣የእናታችን እጅግ ንጽህት ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ እና በረከቷ ከእርስዎ ጋር እንዲሆን በፀሎታችን እያሰብን እኛም ለሀገረስብከቱ ማድረግ በምንችለው ሁሉ ከጎንዎ መሆናችንን እናሳውቃለን።

‎ክቡር አባ አለማዬሁ እጅጉን የስራ ሰው ናቸው ። እሳቸው ባገለገሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በሰው መወደድን ብቻ ሳይሆን የጊዜ አጠቃቀማቸው፣ የማስተማር ክህሎታቸው እጅጉን ከፍ ያለ፣ በአስተዳደራዊ ስራቸው ፍትህ እና ርትዕን በማስቀደም ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ ለውጥ የሚተጉ ብርቱ አባት ናቸው።

‎ #እሳቸው
‎የደከሙትን በመምከር፣ የሚያጠፉትን በመገሰጽ ከቤተክርስቲያን እንዳይጠፉ ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፣ ከቤታቸው በህመም እና በእርጅና ምክንያት ቤተክርስቲያን መምጣት ያልቻሉ ቆራቢያንን እስከ ቤታቸው ሳያቋርጡ በመሄድ የሚያቆርቡ፣የታመሙትን የሚጎበኙ፣ የቤተክርስቲያን ሚስጢራትን ተደራሽ ለማድረግ ዘወትር የሚተጉ፣ የቤተክርስቲያን ማህበራዊ እና የልማት ስራዎችንም በመተግበሩ ረገድ ስኬታማ በመሆን ያለልዩነት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ በመርዳት የምናውቃቸው ለብዙዎች ምሳሌ የሚሆኑ ጠንካራ አባት ናቸው።

‎ #ሌላው እኝህ አባት እጅጉን በሳልና ውሳኔዎችን በጊዜ የሚወስኑ ቀጠሮ አክባሪ ፣በጊዜ አጠቃቀማቸው ጠንቃቃ የሆኑ በህጻን በአዋቂው የሚወደዱ በመርህ፣ እውቀት እና በአስተዋይነት የሚጓዙ ሚዛናዊ የሆኑ፣ ነገሮችን ከንግግር በላይ አድርገው በተግባር የሚገልጡ፣ በስራቸው ምስጉን እና እጅግ ተወዳጅ አባት ናቸው።

‎ ዛሬም እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንዎን ይባርክ፣ በጥበብ እና በማስተዋል የተሰጥዎትን የቤተክርስቲያን ተልዕኮ እንዲወጡ መንፈስ ቅዱስ በነገር ሁሉ ይምራዎት፣ እጅግ የተሳካ የአገልግሎት ጉዞ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

‎ #ብጹዕ አባታችን አቡነ ደጄነ ሂዶቶ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን፣ እንወድዎታለን።

‎ .
#‎shere to follows thanks

እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
22/06/2025

እግዚአብሔር ይመስገን 🙏

አባታችን ❤️የዛሬ 📷
15/06/2025

አባታችን ❤️
የዛሬ 📷

Address

S**o

Telephone

+251930776547

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Soddo Ethiopia Catholic Andinet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category