25/10/2024
የብርሃኑ ነጋ ተሿሚ ፕረዚዳንት የ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ዘቻ እና ማስፈራሪያ ከምን የመነጨ ይሁን ? የትም ያልተሞከረ ሀገርአቀፍ አሰራር ያፈነገጠ የብርሃኑ ነጋ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አመራሮች ሹመትና ጠልቃ ገብነት ምን ታስቦ ነው? እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ምላሽ አላቸው
እንደተለመደው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የፓለቲካ ወጌሻ ልዩ እንግዳ ዝግጅት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ከፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ ማድረግ ልዩ ዝግጀት አሰናድተው እነሆ እንደሚከተለው አቅርቧል ተጋበዙልን🙏
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንግዳችን እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ። ያዉ ባለፈዉ እንዳሉት የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ መግባት እችላለሁ ?
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ተፈቅዷል።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ዛሬ ስለ ዩንቨርስቲዎች እናወራለን።
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መልካም ደስ ይለኛል።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንቶች በቀጥታ ከማዕከል የሚሾሙበት አሰራር ቀርቶ የአካዳሚክ ማህበረሰብ ጭምር በሚሳተፉበት ምርጫ እንዲሆን መደረጉ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ሀገር አቀፍ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ በብርሃኑ ነጋ የተሾሙ አካላት እያስተዳደሩ ቀጥለዋል፤ ይህ በዩኒቨርስቲው እና በዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጥረዉ ተፅዕኖ ይኖር ይሆን ?
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በሚገባ። በመጀመሪያ በሐገር አቀፍ ደረጃ ያለዉ አሰራር በወጥነት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መተግበር አለበት። ሌላዉ ይህ የምርጫ አሰራር በተቋም ደረጃ ዲሞክራሲን ለመለማመድ እድል የሚሰጥ ነው። ከዛ ባለፈ ለዩኒቨርስቲው እድገት ያለዉ ሚና ማሰብ ከሚቻለዉ በላይ ነው።እጩዎቹ በዩኒቨርስቲው ለማምጣት ስላሰቡት እድገት በአጭርና በረዥም ጊዜ ግባቸዉ ምን እንደሆነ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመማር ማስተማር ላይ ሥራ ላይ እና በመሳሰሉት ምን ለመሥራት እንዳቀዱ የሚያቀርቡበትና የተሻለ ሰዉ እንዲመረጥ እድል የሚሰጥ ነው።
በዚህ አይነት ቀድሞ በፖለቲካ ዉግንና ይደረግ የነበረዉ ሹመት በተወሰነ ደረጃ የተሻለ አቅም ያላቸዉ ሰዎች ዩኒቨረስቲዎችን እንዲመሩ እድል የፈጠረ አሰራር ነው። ይህ ጥሩ አሰራር በዎላይታ ሶዶ ብቻ እንዲቋረጥ መደረጉ በጣም አሳዛኝ ነው። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ለሕግ የማይገዙ ፈላጭ ቆራጭነትን የሚሹ መሆናቸዉን ያሳያል።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በእርግጥ የሹመት ደብዳቤ የጻፉት ብርሃኑ ነጋ ናቸዉ፣ ጊዜያዊ በሚል፤ የተሾመዉ ግለሰብስ ላይ ችግር የሚሉት ነገር አለ ?
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ጉዳዩ የግለሰብ አይደለም፥ የመርህ፣ የሕግና የአሰራር ነው። ምናልባት አንድ ዶክተር መድሕን ማርጮ የተባለ ምሁር በጉዳዩ ላይ አስተያዬት በመስጠቱ፣ የአሁኑ ፕሬዘዳንት በዉስጥ መሥመር "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ብሎ ጽፎለት፣ የለጠፈዉን አይቸዋለሁ። እንግዲህ በዚህ ደረጃ ምርጫም ቢደረግ ያለዉን አሰራር ጠልፎ አለአግባብም ቢሆን ያስመርጠኛል ብለዉ የሚያምኑት አካል ይኖር ይሆን የሚል ጥርጣሬም የሚያጭር ነው።
እኔ በበኩሌ ግን የአሁኑም ፕሬዘዳንት፣ እቅዳቸዉን አቅርበዉ እድሉ ተሰጥቷቸዉ በሐቀኛ መንገድ ቢወዳደሩ ችግር የለብኝም። ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን፣ የትዉልድ ተሻጋሪ ተቋም ግምባታ እና በሕግ የመመራት ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የምክትል ፕረዚዳንቶችም ጉዳይ የግለሰብ ሳይሆን፣ የትዉልድ ተሻጋሪ ተቋም ግምባታ እና በሕግ የመመራት ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የምክትል ፕረዚዳንቶችም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህ የዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንቶችን በምርጫ የመሾም አሰራር በተጨባጭ ለዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሚፈይደዉ አሁናዊ ነገር ካለ ቢያስቀምጡልን ?✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የዎላይታ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ ባለ ያለመግባባት ምክንያት ለዘመናት ሲቀጣና ለተንኮለኛ አሰራሮች ተጋልጦ የኖረ ሕዝብ ነው። ይህን ዩኒቨርስቲ ማስከፈቱም ከብዙ ፈተናዎች በኃላ ነው የተቻለዉ። አሁን ደግሞ መንግስት የትምህርት ጥራት ወድቋል ብሎ ተማሪዮችን በገፍ እየጣለ ነው።
ስለዚህ ነገ ከነገ ወዲያ የዩኒቨስቲዎች መዘጋት እና የደረጃ ማዉረድ ሥራ ሊሰራ ይችላል። ስለዚህ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ብቁ ፕረዚዳንቶችን አግኝቶ እራሱን ማሳደግ አለበት። ይሄን የምለዉ ግጭትን ከማስወገድ፣ አቅምን ለእድገት አሟጦ ከመጠቀም አንጻር ነው እንጂ መቼስ የዛ አይነት ዉሳኔም ከመጣ በአካባቢው ሲሰራ ከኖረዉ የብሔር ጭቆና አንጻር በተለዬ ሁኔታ መታየቱ የግድ ነው። በዋናነት ግን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ እንዲያድግ፣ እንዲዘምንና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ነው።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን። ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏