
10/09/2025
👉5 እውነታዎች👈
- አንዳንዴ እየወደድክ የምትርቀው አንዳንዴ ደግሞ እየጠላህ የምትቀርበው ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለህ አብረህ የምትኖረው ሰው አለ
- አንዳንዴ ፍቅሩን ሳይገልጽልህ የሚወድህ አንዳንዴ ደግሞ እወድሃለው እያለ የሚጠላህ ብዙ ጊዜ ግን ስሜቱን የማታውቀው ሰው አለ
- አንዳንዴ እየራበህ የማትበላው አንዳንዴ ደግሞ ጠግበህ የምትመገበው ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለህ የምትውጠው ነገር አለ
- አንዳንዴ ሳትኖር የምትሞትበት አንዳንዴ ደግሞ ሞተህም የምትኖርበት ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለህ የምትጓዝበት ህይወት አለ
- አንዳንዴ አስደስቶህ የምታለቅስበት አንዳንዴ ደግሞ አሳዝኖህ የምታለቅስበት ብዙ ጊዜ ግን ዝም ብለህ የምታነባበት ጉዳይ አለ። በቃ ህይወት እንደዚህ ናት