29/05/2026
ክቡር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ሞጣሎ ማናቸው?
1. የትምህርት ዝግጅት
👉🏿 የመጀመሪያ እና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት: በጋቼኖ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።
👉🏿 የሁለተኛ ደረጃ (ሃይስኩል) ትምህርት: በቦዲቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል። ልዩ ማስታወሻ: በወቅቱ ትምህርት ቤቱ አዲስ ሲከፈት መጀመሪያ የጀመሩ ሲሆን፣ በ1977 ዓ.ም. በወቅቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አራት ኪሎ) ከገቡ ሶስት የአካባቢው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
👉🏿 የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (BSc. Degree): በ1980 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
👉🏿 የሁለተኛ ዲግሪ (MA Degree): በ1990 ዓ.ም. ወደ ህንድ ሀገር (ኒው ዴልሂ) በመጓዝ፣ ከ1991 እስከ 1992 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ትምህርታቸውን አጠናቀው በኢኮኖሚክስ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
👉🏿 ፖስት ግራጁየት ዲፕሎማ በከተማ አመራርና ልማት ስትራቴጂ ከኔዘርላድ እራስማስ ዪኒቨርሰቲ ተመርቀል። 1997
2. የስራ ልምድ እና የኃላፊነት ታሪክ
✍️ከ1981 – 1985 ዓ.ም በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በከፍተኛ ስታትስቲሽያንነት አገልግለዋል።
✍️ ከ1986 – 1988 ዓ.ም.: የኢህአዴግ ስልጣን መያዝን ተከትሎ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከዳይሬክተርነት እስከ ኮሚሽነርነት አገልግለዋል።
✍️ ከ1989 – 1995 ዓ.ም.: ወደ ክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በመዛወር፣ በወቅቱ የነበረው የሰነ-ሕዝብ እና ስታስቲክስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን መርተዋል።
✍️ ከ1996 – 1998 ዓ.ም.: በክልሉ የካቢኔ ማዕረግ የሐዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፋይናንስ ዋና መምሪያ ኃላፊ በመሆን፣ ከተማዋ የዛሬውን ዘመናዊ መልክ እንድትይዝ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
✍️ ከ1999– 2002 ዓ.ም.: የደቡብ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን አመርቂ ስራዎችን መርተዋል።
✍️ ከ2003 – 2008 ዓ.ም.: በፌደራል ደረጃ፣ የፌዴራል ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት መርተዋል።
✍️ ከ2008 – 2013 ዓ.ም.: በፌደራል የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል።
✍️ ከ2014– 2016 ዓ.ም.: የኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን (Cabinet Minister) በሀገር ደረጃ መርተዋል።
✍️ ከ2016 – 2017 ዓ.ም.: በሀገሪቱ አዲስ አደረጃጀት መሰረት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሰርተዋል።
✍️ ከ2017 ዓ.ም. እስከ አሁን: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው በከፍተኛ አመራርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በእሳቸው ጠንካራ አመራር የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት:-
፩. የክልል ምስረታ እና የፖለቲካ መረጋጋት ሥራዎች:
✍️ ክልሉን ከቀውስ መታደግ፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገና በምስረታው ዋዜማ ላይ እያለ ሊፈርስ፣ ለብተና እንዲሁም ለከፋ ቀውስ ሊጋለጥ ጫፍ ደርሶ በነበረበት ወቅት፣ ክቡር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸውና የክልሉ አመራሮአች ጋር በመሆን በሳልና ቁርጠኛ አመራር በመስጠት ክልሉን ማረጋጋት ችለዋል።
✍️ የልማት ማዕከል ማድረግ፦ በዚህም ጥረታቸው ክልሉ ካንዣበበበት የብተና አደጋ ወጥቶ የተረጋጋ የልማት ማዕከል እንዲሆንና በበርካታ የሥራ ዘርፎች ተወዳዳሪ ክልል ሆኖ እንዲቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
✍️ የእርቀ ሰላምና አንድነት መድረክ ማዘጋጀት፦በወላይታ ዞን ተፈጥሮ በነበረው የፖለቲካ ግብ ልዩነት መነሻነት የተፈጠረውን የቂም በቀል መንፈስ በመስበር ማንም ያልደፈረውን የዕርቅ፣ የሰላምና የአንድነት መድረክ ያዘጋጁ ሲሆን፣ በጥላትነት የሚተያዩ ጎራዎችንም ወደ አንድ የጋራ አጀንዳና የልማት ዕቅድ ማምጣት አስችለዋል። እንዲሁም አጉል አመለካከቶችን መዋጋት፦በአካባቢው በተወሰነ ጊዜ ሰፍኖ የነበረውን ጅምላ እስራት፣በስልጣን ላይ የመባለግ የፖለቲካ ዝንባሌ፣ የመጠላለፍ እና የጥላቻ ልምምድ በተግባር በመንቀል፣ ቡድኖች ከከንቱ የፖለቲካ ሽኩቻ ወጥተው በሰላምና በልማት ላይ እንዲያተኩሩና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አድርገዋል።
፪. የመሠረተ ልማት እና የግንባታ ሥራዎች:-
✍️ የከተማ ውስጥ አስፋልት ግንባታ፦** ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የወላይታ ከኮካቴ እስከ ግብርና ኮሌጅ ድረስ ያለውን የከተማ ውስጥ አስፋልት በተሳካ ሁኔታ በማስጀመርና በቁርጠኝነት በመምራት ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ አቅረበውታል።
✍️ የወላይታ (ሱማሞ) አየር ማረፊያ፦** የካሳ ክፍያ ችግር ሳይፈታለት ለረጅም ጊዜ ዘግይቶ የነበረውን የሱማሞ አየር ማረፊያ በቁርጠኛ አመራር ወደ ሥራ በማስገባት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ እየመሩት ይገኛሉ።
✍️ የጨራቄ ተንጠልጣይ ድልድይ፦የጨራቄን ተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ በተመሳሳይ መልኩ በቁርጠኝነት በመምራት በስኬት ማስመረቅ ችለዋል።
✍️ የመንገድ ልማት ጥያቄዎችን መመለስ፦ ለረጅም ዓመታት የልማት ጥያቄ ሆኖ የቆየውን ከጋቼኖ እስከ ዳሞት ኦፋ ያለውን መንገድ በማሠራት ኅብረተሰቡ ለጤና፣ ለትምህርትና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ቅርብ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል።
✍️ የመሠረተ ልማት ችግሮችን መፍታት፦ በጥቅሉ በየአካባቢው የሚስተዋሉ የመንገድ፣ የድልድይ እና የጤና ተቋማት መሠረታዊ ችግሮችን በየደረጃው በመፍታት ረገድ ትልቅ አመራር እየሰጡ ይገኛሉ።
፫. የቱሪዝም፣ የአደረጃጀት እና የከተማ ማሻሻያ ሥራዎች:-
✍️ የኮሪደር ልማትና ኢኮ-ቱሪዝም፦ ከወላይታ ሶዶ ከተማ እስከ ዳሞት ተራራ ያለውን የመንገድና የመወጣጫ ደረጃ በማሰጀመር የአካባቢውን ኢኮ-ቱሪዝም ለማስፋት፣ ከካርቦን ፕሮጀክት (*Carbon Project*) ጋር በማስተሳሰር ከግማሽ በላይ ሥራውን አጠናቀዋል።
✍️ የከተማ ተወዳዳሪነትና የሆስፒታሎች ደረጃ፦ የሶዶ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በማስጀመር ከተማዋ ወደ ተወዳዳሪነት እንድትሸጋገር ያደረጉ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከደረጃ በታች የነበሩ ሆስፒታሎችን ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ አድርገዋል።
✍️ በብቃት (*Merit*) የሚመሩ ተቋማት፦ የአካባቢውን ተወዳዳሪነትና አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት ምሁራንንና ወጣት ኃይል በማደራጀት፣ ተቋማት ቁመናቸውን እንዲፈትሹ የአሰራር ስርዓት ተከትለው እንዲሠሩ አድርገዋል።
✍️ የጀግኖች ሐውልት ግንባታ፦ተጀምሮና ተከልክሎ ለረጅም ጊዜ ቆሞ የነበረውን የወላይታ ጀግኖች ሐውልት በቁርጠኝነት በመምራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አስመርቀው፣ የሕዝቡን የፖለቲካና የባህል ልዕልና ከፍ አድርገዋል።
፬. የዜጎችን መልሶ ማቋቋም ሥራዎች
✍️ የኮይሻ ተፈናቃዮችን ማቋቋም፦ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ተፈናቃዮችን ወደ አባላ አባያ አካባቢ በማሠማራትና በማስፈር፣ ከ(500) በላይ አባወራዎች በተሟላ የልማት ዕቅድ እንዲቋቋሙ አድርገዋል።
፭. የወላይታ ልማት ማኅበር (ወልማ) ማነቃቃት:-
✍️ ለ8 ዓመታት ቆሞ የቆየን ሕንጻ ወደ ሥራ ማስገባት፦ ለስምንት ዓመታት ያህል ያለእንቅስቃሴ ቆሞ የነበረውን የማኅበሩን ሕንጻ ሕዝቡን በማነሳሳት ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረጉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በማኅበሩ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴና ንቅናቄ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል።
✍️ በምሁራን ማደራጀት፦የወላይታ ልማት ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ በመሆንም ልማት ማኅበሩን በአዲስ መዋቅርና በምሁራን በማደራጀት ሕዝባዊ ተቋምነቱን መልሰው እንዲያንሰራራ አድርገዋል።
✍️ የልማትና የቴክኖሎጂ ማዕከል፦ማኅበሩ የወላይታ ሕዝብ የልማት፣ የባህል፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ እምብርት ሆኖ እንዲያገለግል በከፍተኛ ትጋት እየሠሩ ይገኛሉ።
፮. ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች (*Challenges*)
እነዚህ ሰፊ የልማት ሥራዎች በሚከናወኑበት ወቅት የሚከተሉት ፈታኝ ሁኔታዎች አጋጥመው በአመራር ብቃት እየተመሩ ይገኛሉ፦
✍️ የኦቶና ሆስፒታል የእሳት አደጋ፦ የኦቶና ሆስፒታል የደረሰበት የእሳት አደጋ ትልቅ ፈተና የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት በአግባቡ እየተመራና መልሶ የማቋቋም ሥራ እየተሰራለት ይገኛል።
✍️. የመንገድና የአየር መንገድ ፈተናዎች፦ከኮካቴ እስከ ግብርና ኮሌጅ ያለው መንገድ እንዲሁም የሱማሞ አየር መንገድ ሥራዎች በበርካታ ውጫዊ ፈተናዎች የተከበቡ ቢሆንም፣ በልዩ ትኩረትና ክትትል እየተመሩ ነው።
✍️. የስታዲየም ግንባታ ምህዳር፦በከባድ ሁኔታና ፈታኝ ምህዳር ውስጥ የተጀመረው የወላይታ ሶዶ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ገቢ ማሰባሰብ በተቀናጀ መልኩ በጥሩ ሁኔታ እንዲቀጥል አሁንም በትጋት እየተሰራ ይገኛል።
ይቀጥላል…