
12/05/2025
በወላይታ ዞን "የመሐሉን ዘመን ወጥመድ መሻገር" በሚል ሀሳብ ዞናዊ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ነው
ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 4/2017 በወላይታ ዞን "የመሐሉን ዘመን ወጥመድ መሻገር" በሚል ሀሳብ ዞናዊ የአመራር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመሐሉ ዘመን የሚያጋጥሙ የሽግግር ፈተናዎችንና ተግዳሮቶችን ለመሻገር የሚያስችል የተሟላ የአመራር ብቃት ለመገንባት እና የጋራ ግንዛቤን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተገልጿል፡፡
"የመሐሉን ዘመን ወጥመድ መሻገር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሰነድ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም እያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም፣ የወላይታ ዞን የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን ቶማስን ጨምሮ የዞኑ አጠቃላይ አመራር እና የወረዳና ከተማ አስተባባሪ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።