Wolaita News

Wolaita News Freedom for wolaita

ሰበር የድል ዜናወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል*************************ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን እንደሚወክል የኢትዮጵያ እግር...
01/07/2025

ሰበር የድል ዜና

ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል
*************************

ወላይታ ድቻ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን እንደሚወክል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይፋ አደረገ

በቅርብ በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜበሲዳማ ቡና 2 ለ 1ተሸንፎ የነበረው ወላይታ ድቻ የሲዳማ ቡና ውጤት በመሰረዙ በአፍሪካ መድረክ ተሳታፊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ሲዳማ ቡና በፍጻሜ ጨዋታው የታገዱ ተጫዋቾችን በመጠቀሙ ውጤቱ እንደተሰረዘበት ይፋ ተደርጓል፡፡

ሰኔ 12.2017 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ           መጣ (ት.ዳን "10፥13")እንኳን ለሊቀ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ::
19/06/2025

ሰኔ 12.2017

ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ
መጣ (ት.ዳን "10፥13")

እንኳን ለሊቀ መልዓኩ ቅዱስ
ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ::

የከተማ ወጣት ወደ ጠላ ዞረ  News I የሀገራችን ባህላዊ አልኮል መጠጦች መካከል ጠላ አንዱ ነው። የፈረንጆች የሆኑት ቢራ እና ድራፍት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው ኪስ እየጎዳ በመምጣቱ በተለይ...
11/06/2025

የከተማ ወጣት ወደ ጠላ ዞረ

News I የሀገራችን ባህላዊ አልኮል መጠጦች መካከል ጠላ አንዱ ነው። የፈረንጆች የሆኑት ቢራ እና ድራፍት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው ኪስ እየጎዳ በመምጣቱ በተለይ የቢራ ወዳጅ የሆነው የከተማ ሰው ፊቱን ወደ ሐላ እያዞረ ይመስላል።

በትናንሽ የክፍለ ሀገር ከተሞች በቀላሉ የሚገኘው ጠላ አሁን አሁን በአዲስ አበባ ከፍተኛ ተጠቃሚ በማግኘቱ ትላልቅ ጠላ ቤቶች በመሃል ቦሌ እየተከፈቱ ይገኛሉ።

ጃምቦ ሃውስ በቀላሉ በየሰፈሩ የሚገኝባት አዲስ አበባ አሁን ወደ ጠላ ሃውስ እየተቀየረ ይመስላል።

የኑሮ ውድነት እና የቢራ ዋጋ ውድነት ሳይጠጣ እንዲያዞረው ያለው ወጣቱ ክፍል ቢራን ከመተው ይልቅ በቅናሽ ዋጋ የሚያገኘውን የሀገር ኬሚስትሪ የሆነው ጠላ እያዘወተረ እንደሆነ ተመልክተናል።

የአልኮል መጠኑ የማይታወቀው ጠላ በአንዳንድ ስፍራዎች በወረፋ እየተጠጣ "አለቀ" የሚባልበት የጠላ መሸጫ ቦታዎች አሉ።

ይህ መረጃ ሲለቀቅ በርካታ ወጣቶች ጠላን እየተጎነጩ እንደሚያነቡ ይገመታል።

ባትጠጡ ይመከራል፣ ካልጠጣው ሞቼ እገኛለሁ ካላችሁ በልክ፣ በኃላፊነት ይሁን!

ኧረ ጠላ ጠላ እኔን ጥልል ያርገኝ
እንቅልፌ ሳይመጣ እምታጋድመኝ!

የዎላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ለፊፋ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው። "በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየደረሰ ያለውን በደል ለፊፋ እናቀርባለን" ያሉ ደጋፊዎች ንቅናቄው በሀገር ውስጥና ከሀገር ...
09/06/2025

የዎላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ለፊፋ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው። "በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየደረሰ ያለውን በደል ለፊፋ እናቀርባለን" ያሉ ደጋፊዎች ንቅናቄው በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተሰባሰቡ አስተባባሪዎች እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሀገር ውጭ ያለውን አለም አቀፍ ሞዴል ሰናይት ማሪዮ እንዳለችበት ታውቋል።

ሁላችሁም የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎችና ህዝቦች ይህን ይፋዊ ገፅ ባለመከተል ድምፃቹህን አሰሙ 💪💪💪
08/06/2025

ሁላችሁም የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎችና ህዝቦች ይህን ይፋዊ ገፅ ባለመከተል ድምፃቹህን አሰሙ 💪💪💪

ከዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የዎላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ላይ በደረሰው እንግልት ፣ግድያ፣እስራትና ወከባ በተ...
08/06/2025

ከዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የዎላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ላይ በደረሰው እንግልት ፣ግድያ፣እስራትና ወከባ በተመለከተ አስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው እለት ሰኔ 1/10/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም በወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና መካካል የሚደረገውን የዋንጫ ጨዋታ ለማየትና የሚወደውን ክለብ ለመደገፍ ሀገር ሰላም ብሎ አዲስ አበባ መጓዙ ይታወቃል። ሆኖም ግን ሀላፊነት በጎደለው የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌደረሽን ውሳኔ የተነሳ ደጋፊዎች ቅሬታ ውስጥ ቢገቡም በሰላማዊ መንገድ በከተማው ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት ኃላፊነት በጎደለ መልኩ በጸጥታ አካላት በተወሰደ እርምጃ የአንድ ሰው ህይወት ስያልፍ፣ ሌላ አንድ ሰው ክፉኛ ከመቁሰሉ ባሻገር በርካቶች እስራትና ድብደባ መፈጹሙን ፓርቲው ባገኘው መረጃ አረጋግጧል። በክስተቱ ሕይወት ላጡ መጽናናትን ለቆሰሉ፣ ለታሰሩና ለተደበደቡ ወገኖች ቶሎ ማገገምን እየተመኘን በንጹሀን ግድያና ለደረሰው እንግልት መንግስት አፋጣኝ ርምጃ ወስዶ ሕባችንን እንድያሳውቅ አጥብቀን እየጠየቅን በህዝባችን ላይ ለደረሰው በደል ሁሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደረሽን ተጠያቂ መሆኑን ጭምር ልናስገነዘብ እንወዳለን።

ፍትህ ለመላው ዎላይታ ሕዝብና ለዎላይታ ድቻ ደጋፊዎች!!!

የዎህዴግ ጽ/ቤት
01/10/2017 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ/ኢትዮጵያ

ጫወታው መሰረዝ አለበት 😭😭😭😭ደጋፊ ሞቷል ብዙዎች ታስረዋል 😭😭😭
08/06/2025

ጫወታው መሰረዝ አለበት 😭😭😭😭
ደጋፊ ሞቷል
ብዙዎች ታስረዋል
😭😭😭

የህወሓትን መሰረዝ ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ለፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠየቀ ህወሃት በኩሉ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ህወሓትን "ሕገወጥ የፖለቲ...
15/05/2025

የህወሓትን መሰረዝ ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት
ለፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠየቀ

ህወሃት በኩሉ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን "ሕገወጥ የፖለቲካ ፓርቲ" ብሎ መሰረዙን ተከትሎ፣ የአፍሪካ ህብረት ለፀጥታ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አቀረበ።

ህብረቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ፣ ሁኔታው ወደ ከፋ ግጭት ከማምራቱ በፊት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስቧል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሰብሳቢ ክቡር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ፤ የኢብም ውሳኔ የሰላም ስምምነቱን በግልጽ የሚፃረርና በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የተደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል።

ህብረቱ፤ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ በመሰብሰብ በጉዳዩ ላይ እንዲወያይና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

ህወሃት ምርጫ ቦርድ ህወሃትን ከፓርቲነት የሰረዘበት መንገድ ተቀባይነት የለውም ያለ ሲሆን ምርጫ ቦርድ ለአንድ ወገን ያደላ ውሳኔ አሳልፏል ብሏል።

ህወሃት ችግሮችን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በድርድር እና በንግግር ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ፍቃደኛ የፌደራል መንግስቱ ዳተኝነት አሳይቷል ብሏል።

በዚህም የምርጫ ቦርድ ለአንድ ወገን ያደላ ውሳኔ የፕርቶሪያውን ስምምነት አደጋ ውስጥ ጥሎታል ያለ ሲሆን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ለፌደራል መንግሥቱ እንዲሁም ለአደራዳሪዎቹ የሚከተለውን ጥሪ አቅርቧል።

1. በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል አስቸኳይ የፓናል ውውይት እንዲካሄድ ጫና እንዲደረግ
2. የአፍሪካ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት ይሄን ጉዳይ አጀንዳ እንዲያደርገው እና በቀጣይ ስብሰባ ሲቀመጥ እንዲወያይበትና የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንዲመረምር፣
3. ውይይት እስከሚደረግ የፌደራል መንግሥቱ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንዲሰርዝ ጫና እንዲያሳድር እና ግፊት እንዲያደርግ ጠይቋል።

የአከባቢው ህብረተሰብ እንዲተች 🤔🤔🤔
15/05/2025

የአከባቢው ህብረተሰብ እንዲተች 🤔🤔🤔

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሆሳዕና በዓል እየተከበረ ነውእንኳን አደረሳችሁ!
13/04/2025

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሆሳዕና በዓል እየተከበረ ነው

እንኳን አደረሳችሁ!

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር "መጋቢት 24" ቀንን በድምቀት ለማክበር እንዲያስችል እለቱን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ቦዲቲ ፤ መጋቢት ፤ 18/2017 ዓ.ም በወላይታ ዞን ...
27/03/2025

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር "መጋቢት 24" ቀንን በድምቀት ለማክበር እንዲያስችል እለቱን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

ቦዲቲ ፤ መጋቢት ፤ 18/2017 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር "መጋቢት 24" ቀንን በድምቀት ለማክበር እንዲያስችል እለቱን አስመልክቶ "የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች!" በሚል አርስት በተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

መድረኩን የቦዲቲ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ሳሙኤል የመሩ ሲሆን ቀኑ በተሻለ ድምቀት እንዲከበር ዘንድ ለቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተዋቀረ አብይ ኮሚቴ የመድረኩ ተሳታፊ ነበር ።

አቶ ፍሰሃ በመድረኩ እንደገለፁት "መጋቢት 24" በኢትዮጵያ በርካታ መልካምና በጎ የሆኑ ኩነቶች የተፈጠሩበት ልዩ ቀን በመሆኑ ከሌሎች ቀኖች ለየት ባለ መልኩ ደምቆ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ መጠናቀቅ አለባቸው ብሏል።

ቀኑ በተለይ እንደ ሀገር በርካታ ፈተናዎችን በማለፍ በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚው እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ ስኬቶችና ድሎች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ አቶ ፍሰሃ በመድረኩ ገልጸዋል።

መጋቢት 24 ቀን የሚከበርበት ምክንያት በባለፉት ዓመታት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም በውጭ ዲፕሎማሲ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ህዝባችን ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኝና መሳሳት ተፈጥሮ የተጀመሩ ስኬቶችን በአብሮነት ለማስቀጠል ነው ተብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቀኑ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ሰርጾ በመግባት በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ግንዛቤ ስራን ከመስራት አኳያ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ትልቁን ድርሻ ልወጣ ይገባል ብሏል።
Wolaita News

Address

Main
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share