24/12/2025
፨፦ከቀድሞው የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃማርያም ደሳለኝ ቦሼ አንደበት......
የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃ /ማርያም ደሳለኝን በተለያዩ አጋጣሚዎች አግኝቻቸው አውቃለሁ። በአንድ ወቅት እንደጋሞ ህዝብ የአጋጠመንን ህዝባዊ ጥያቄ ይዘን ቤተመንግሥት ድረስ ዘልቀን የነበረ ጊዜ ስለጋሞ ህዝብና ስለጋሞነት እንዲህ ብለው ነበር።
"እኔ ለጋሞ ህዝብ ታላቅ ክብርና አክብሮት አለኝ።
ገና በወጣትነት ዕድሜዬ ለመጀመሪያ ጊዜ መሠረተ ትምህርት ለማስተማር የዘመትኩት "ጋሞ ካምባ ሶርባ" የተባለ አካባቢ ስለነበር በዚያ በወጣትነት ዕድሜዬ ከጋሞ ህዝብ ላይ መልካም ሥነ ምግባርን ፣ ፍቅርንና የክራር ጭፈራን ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ተምሬአለሁ።
ሥራ የተቀጠርኩት በጋሞ ምድር በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነው፣ሚስት ያገባሁት እና ልጆቼን የወለድኩት በጋሞ ምድር አርባምንጭ ከተማ ነው።
በአጠቃላይ የጋሞ ምድርና ህዝብ ለእኔ እዚህ መድረስ ያስቻሉኝ የበረከቴ ምንጭ ናቸው።
የጋሞ ህዝብ ጥንታዊ ታሪክ በተመለከተም ጥንት የወላይታ ህዝብ ከአካባቢው ህዝብ ጋር በወሰን፣በግጦሽ እና በሌሎች ምክንያቶች በሚፈጠሩ የእርስ በእርስ ግጭቶችና ጦርነቶች ሁሉ የዎላይታን ህዝብ በመምራት እና በማገዝ ለዎላይታ ህዝብ ነፃ መውጣት ከፍተኛ መስዋዕትነት ይከፍል ስለነበረ ታላቁ የዎላይታ ህዝብና አባቶች ዳሞት ተራራ ከአካባቢው ሁሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ለተደረገላቸው ድጋፍና መስዋዕትነት መታሰቢያ እንዲሆናቸው በመሸለማቸው አሁን ድረስ በዳሞት ተራራና አካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ከጋሞ ከልዩ ልዩ ከአባቢዎች የመጡ እና በወላይታ ህዝብ ዘንድ የተከበሩ "የጋሞ ማላ"የሎንቴ ማላና ሌሎች ጎሣዎች እንደሆኑ እንዲሁም የእርሳቸውም የዘር ሀረግ ሲመዘዝ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ ከጋሞ እንደሆኑ በከፍተኛ የቁጭት ስሜት ውስጥ ሆነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ቤተመንግሥት ውስጥ በዎላይተኛ ቋንቋ ስለጋሞ ህዝብ ታላቅነት ፣ሃያልነት ሠላማዊነት ከልብ በመነጨ ስሜት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
(ምንጭ፦እንቆቆ ኮሶ ሻራ)
፨፦፨፦፨፦፨፦፨፦፨፦፨፦፦፨፦፨፦፨፦፨፦፨፦፨፦
የቁጫ ህዝብ የጋሞ አካል ስለመሆኑ አስቀድሜም አውቃለሁ በቁጫ ወረዳ በመሄድ በአካል ተገኝቼ ህዝብ ሰብስቤ እውነታውን ሰምቻለሁ።" አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ(የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር)
*************************************. ለጥቅም ስባል ጋሞን ማጥቃት ከባድ ጥፋት ነው!
**ከመሬት ተነስቶ ነባር የጋሞ ህዝብን ለመበተን የሚደረግ ሩጫ የጥገኞች ሰራ ነው! መቼም አይሳካም።
*** በጋሞ ዞን የማንነት ጥያቄ የሚያነሱት ጋሞዎች ሳይሆኑ በሴራ ፖለቲካ የተካኑ ሌቦች ናቸው!
**በታሪክ የማውቀው ቁጫ እና ዶርዜ ጋሞ ስለመሆናቸው ማስረጃ አያስፈልግም! ጋሞ ናቸው።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ መድረክ ካዎራው ተወስዶ በማህበራዊ ገጽ ከተለቀቀው የተወሰደ።
(ምንጭ ፦ መዓዛ አሸናፊ እና ሸዋ ኮሶ ሻራ)