Wolaita Post

Wolaita Post we are in community visit our page

01/07/2025

# ዎ.ሶዶ @የደስታ አገላለጽ🙏🙏

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች
01/07/2025

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በቀን 24/10/2017 ዓ/ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አበይት ጉዳዮች

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት እየጎበኙ ይገኛልሰኔ 22/2017 ዓ.ምበወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ክልል አቀፍ የሰላምና ልማት ...
30/06/2025

የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት እየጎበኙ ይገኛል

ሰኔ 22/2017 ዓ.ም

በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ክልል አቀፍ የሰላምና ልማት ኮንፈረንስ በመካፈል ላይ የሚገኙ ተሳታፊዎች በከተማው እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የኮሪደር ልማቱ ለከተማው ተጨማሪ ዉበት ከማላበሱም በላይ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩ በጉብኝቱ ተጠቅሷል።

ኮንፈረንሱ በክልሉ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ።

በጉብኝቱ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከፌዴራልና በየደረጃው ከሚገኙ መዋቅሮች የተወጣጡ የክልሉ ተወላጅ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ሰፈራ ጣቢያ ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አደረገ ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 11/2017 በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር...
18/06/2025

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ሰፈራ ጣቢያ ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አደረገ

ወላይታ ሶዶ፤ሰኔ 11/2017 በወላይታ ዞን የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ሰፈራ ጣቢያ ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አድርጓል።

በዞኑ ከካዎ ኮይሻ እና ኪንዶ ዲዳዬ በመሬት መንሸራተትና ናዳ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው የሰፈራ ጣቢያ ሁለተኛ ዙር ድጋፍ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር አበርክቷል።

የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማስተባበር የመጀመሪያ ዙር ያደረገ ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ህዝቡን በማስተባበር ከፍተኛ ድጋፍም አድርጓል።

"ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ሀሳብ ለተጎጂ ወገኖች ከ2.5 ሚልዮን የሚበልጥ የቤት መሥሪያ የሚሆን ቁሳቁስን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀጣይም መሰል ድጋፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

የወላይታ ዞን አስተዳደር የወረዳው አስተዳደር ላበረከተው ከፍተኛ ድጋፍና ለሰጠው ትኩረት ምስጋና በማቅረብ ሌሎች ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ለሰብዓዊ ድጋፍ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸውም አሳስቧል።

በዞኑ በአበላ አባያ ወረዳ አባያ ጫውካሬ ቅጣ አከባቢ መልሶ ለማቋቋም የሚሰራው የሰፈራ ጣቢያ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

 #የደመወዝ ጥቅማ ጥቅም፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ለገቢዎች ቢሮ በስሩ ለሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጭማሪ ይፋ ሆኗል‼️
16/06/2025

#የደመወዝ ጥቅማ ጥቅም፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ ለገቢዎች ቢሮ በስሩ ለሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጭማሪ ይፋ ሆኗል‼️

ፖል ፖግባ ወደ ሜዳ ሊመለስ ነው !   | ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል። ሞናኮ ለፖል ፖግባ የሁለት አመት ኮንትራ...
13/06/2025

ፖል ፖግባ ወደ ሜዳ ሊመለስ ነው !

| ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ከፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል።

ሞናኮ ለፖል ፖግባ የሁለት አመት ኮንትራት ማቅረባቸው ሲገለፅ አሁን ላይ በክለቡ እና ተጨዋቹ መካከል ንግግሮች መቀጠላቸው ተነግሯል።

አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ከእግርኳስ ለአራት አመታት ታግዶ የነበረው ፖግባ እገዳው ወደ 18 ወራት ተቀንሶለት ወደ እግርኳስ መመለሱ ይታወሳል።

ፖል ፖግባ ከጁቬንቱስ ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡን ተከትሎ ሞናኮን በነፃ ዝውውር ይቀላቀላል።

በሌላ በኩል ሞናኮ የባርሴሎናውን ተጨዋች አንሱ ፋቲ ለማስፈረም በመስራት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ኢራን በእስራኤል በተገደሉባት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠች  | ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እና ባለስልጣናትን የሚተኩ ሹመቶችን ሰጥታለ...
13/06/2025

ኢራን በእስራኤል በተገደሉባት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ምትክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠች

| ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እና ባለስልጣናትን የሚተኩ ሹመቶችን ሰጥታለች።

በዚህም ሜጀር ጄነራል ሰይድ አብዱረሂም ሙሳቪ የኢራን ጦር ኃይል ኤታማዦር ሹሞች ሊቀመንበር ሆነዋል።

እንዲሁም ሜጀር ጄነራል አሊ ሻዴማኒ የኻታም አል-አንቢያ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥ ሲሆኑ፣ ሜጀር ጄነራል መሀመድ ፓክፑር የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሆነው ተሹመዋል።

እስራኤል በሰነዘረችው ጥቃት ኢራን ቁልፍ የሆኑ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እና የጦር መሪዎችን አጥታለች።

 ‼️አሁን በተራራ ውስጥ የተደበቀ የኢራን ዋነኛ የኑክሌር ጣቢያ በእስራኤል ቦንብ እየተደበደበ ነው።እስራኤል በ ፎርዶን ግዛት የሚገኘውን የኢራን ዋነኛ የኑክሌር ጣቢያን መታች የእስራኤል አየ...
13/06/2025

‼️

አሁን በተራራ ውስጥ የተደበቀ የኢራን ዋነኛ የኑክሌር ጣቢያ በእስራኤል ቦንብ እየተደበደበ ነው።

እስራኤል በ ፎርዶን ግዛት የሚገኘውን የኢራን ዋነኛ የኑክሌር ጣቢያን መታች የእስራኤል አየር ሃይል አሁን ላይ የኢራን በጣም በጥልቀት የመሬት ውስጥ የኑክሌያር ማበልፀጊያ ተቋም የሆነውን ፎርዶን በቦምብ እየደበደበ መሆኑን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባው ፎርዶ የኑክሌያር ማብሊያ የአየር ላይ ጥቃቶችን ለመቋቋም የተነደፈ እና የኢራን የዩራኒየም ማበልፀጊያ ማዕከል ሆኖ ቆይቷል።
ኢራን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ እና በእስራኤል ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፀጥታው ምክር ቤት ልካለች፡፡

  🙏👉ዛሬ ማለዳ በከተማችን ወላይታ ሶዶ መርካቶ ዩሹዋ ቀበሌ ጊሼ ሰፈር በተከሰተው የተሽከርካሪ አደጋ ይህ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ወጣት ጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ምንክያት ማ...
16/05/2025

🙏

👉ዛሬ ማለዳ በከተማችን ወላይታ ሶዶ መርካቶ ዩሹዋ ቀበሌ ጊሼ ሰፈር በተከሰተው የተሽከርካሪ አደጋ ይህ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ወጣት ጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ምንክያት ማውራት የማይችል በመሆኑና ፤ ምንም አይነት መረጃ ሰለእሱ ማወቅ አልቻልንም።ኪሱ ውስጥ መታወቂያ፣ስልክም አልተገኘም።አብሮት ያለ ሰውም የለውም።ስለዚህ ይኼንን ወጣት በቅርበት የሚያወቅ ሰው ካለ #ኦቶና ሆስፒታል ጥንቃቄ ክፍል ውስጥ ሰለሚገኝ እሱን የሚያውቅ ሰው ካለ ይተባበረን።
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ !!

 #ከባድ የመክና አደጋ😭😭 በወላይታ ሶዶ ከተማ በመርካቶ ዩሿ ቀበሌ በአዲሰ  ወደ ሀዋሳ መንገድ በተለምዶ መናፈሻ ሠፈር  በተከሰተው አንድ ትልቁ ተሳቢ መክናና ከዶልፊን ጋር በመጋጨት በቁጥር...
16/05/2025

#ከባድ የመክና አደጋ😭😭 በወላይታ ሶዶ ከተማ በመርካቶ ዩሿ ቀበሌ በአዲሰ ወደ ሀዋሳ መንገድ በተለምዶ መናፈሻ ሠፈር በተከሰተው አንድ ትልቁ ተሳቢ መክናና ከዶልፊን ጋር በመጋጨት በቁጥር ከ4 ሰው በላይ ሞትን ለሎችም በ comma ሆስፒታል ገብቶአል በጣም ያሳዝናል ።
#ነፍስ ይማርልን።

በእርጋታ በማስተዋል በማሽከርከር የራሳችን የሌላውን ህይወት ንብረት ከትራፊክ አደጋ እንጠብቅ።

ሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሠረዘአዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታ...
14/05/2025

ሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሠረዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-

መቀሌ፦ ሰላም ለሀገሬ ይሁን !!የፌደራል ፖሊስ ወደ ትግራይ እየገባ ነው ። በፕርቶሪያው ስምምነት መሰረት የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ በመግባት የፌደራል ተቋማትን ይጠብ...
14/05/2025

መቀሌ፦ ሰላም ለሀገሬ ይሁን !!
የፌደራል ፖሊስ ወደ ትግራይ እየገባ ነው ። በፕርቶሪያው ስምምነት መሰረት የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ በመግባት የፌደራል ተቋማትን ይጠብቃል፣ህግ ያስከብራል።

በዛሬው ዕለት በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት መቀሌ ገብተዋል። ህወሃት ዛሬ በምርጫ ቦርድ ከፓርቲነት መሰረዙ ይታወቃል።

Address

Gununo
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Post posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share