Deacon Mekonen Galcha

Deacon Mekonen Galcha ✥እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ያዉም የተዋህዶ ልጅ
@ እምነቴ በልቤ መሰቀሉ በአንገቴ።�✣

ሣራ ሁለት ጊዜ ሳቀች ‼️❓አንደኛው እግዚአብሔር ልጅ ትወልጃለሽ ሲላትካረጀው በኋላ እንዴት ይሆናል? በማለት በልብዋ የውሸት ሳቅ ሳቀች✅ ሁለተኛው ይስሐቅን በዘጠና ዓመቷ ከወለደች በኋላእግዚ...
27/05/2026

ሣራ ሁለት ጊዜ ሳቀች ‼️

❓አንደኛው እግዚአብሔር ልጅ ትወልጃለሽ ሲላት
ካረጀው በኋላ እንዴት ይሆናል?
በማለት በልብዋ የውሸት ሳቅ ሳቀች

✅ ሁለተኛው ይስሐቅን በዘጠና ዓመቷ ከወለደች በኋላ
እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ስትል የደስታ ሳቅ ሳቀች

📌 በዘመናችሁ የውሸት ሳይሆን
የእውነትና የደስታ ሳቅ ይሁንላችሁ።

የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር፣ የቅዳሴ እና የጸሎት ሥነ ሥርዓት በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን !
02/04/2026

የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር፣ የቅዳሴ እና የጸሎት ሥነ ሥርዓት በሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን !

አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬከሀዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬገብረ ሕይወት መጣ ጻድቁ አባቴደዌዬ ተሻረ ጸና ጉልበቴ🤍Deacon Mekonen Galchaየካቲት 5/2018 ዓ.ም
14/03/2026

አበቃ ሲባል አልቆ ተስፋዬ
ከሀዘን ብዛት ሲፈስ እንባዬ
ገብረ ሕይወት መጣ ጻድቁ አባቴ
ደዌዬ ተሻረ ጸና ጉልበቴ🤍

Deacon Mekonen Galcha
የካቲት 5/2018 ዓ.ም

📔አንቺን መውደድ መታደል ነው! 📔✨ድንግል ሆይ! አንቺን መውደድ ተራ ስሜት ሳይሆን ከሰማይ የሚሰጥ 'ዕድል' ነው። ጌታ 'የመረጥኋችሁ እኔ ነኝ' (ዮሐ ፲፭፥፲፮) እንዳለ፣ አንቺን እንድንወድ...
27/02/2026

📔አንቺን መውደድ መታደል ነው! 📔

✨ድንግል ሆይ! አንቺን መውደድ ተራ ስሜት ሳይሆን ከሰማይ የሚሰጥ 'ዕድል' ነው። ጌታ 'የመረጥኋችሁ እኔ ነኝ' (ዮሐ ፲፭፥፲፮) እንዳለ፣ አንቺን እንድንወድና እናታችን አድርገን እንድንቀበል መመረጣችን የጸጋ ስጦታ ነው። ዓለም በብዙ ነገሮች ስትደለል፣ እኛ ግን በአንቺ ፍቅር መሸነፋችን ትልቅ መታደል ነው። አንቺን መውደድ ማለት ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከፍርሃት ወደ ተስፋ መሻገር ነው። ይህ ፍቅር የነፍስ ስንቅና የሕይወት መረጋጋት ነው።

✨እመቤቴ ሆይ! አንቺን መውደድ ከዋዘኞች ወንበር ያነሳል፣ በክፉዎች ምክር ከመሄድም ይጠብቃል። ምስጉን መሆን ማለት ካንቺ ጋር መሆን ነው። ዛሬም በሕይወቴ ውኃ ፈሳሽ ዳር ተክለሽኝ፣ በቃሉ ብርሃን እንድለመልም አድርጊኝ። አንቺን መውደዴ የዘላለም ክብሬ ነው፤ ስምሽን መጥራቴም የነፍሴ ሰላም ነው።

Deacon Mekonen Galcha
የካቲት 21 ቀን / 2018 ዓ.ም

አለ መቸኮል ደጋግሞ ማየት ። ችኩልነት አገር ያጠፋል መታገስ መልካም ነው ለምሳሌ እየው ላችሁ  መታገስ ብዙ አይነት ነው ለምሳሌ አንድን ችግር  ተሸክመነው ኑረን ኑረን መፍትሄ በምናገኝበት ...
24/02/2026

አለ መቸኮል ደጋግሞ ማየት ። ችኩልነት አገር ያጠፋል መታገስ መልካም ነው ለምሳሌ እየው ላችሁ መታገስ ብዙ አይነት ነው ለምሳሌ አንድን ችግር ተሸክመነው ኑረን ኑረን መፍትሄ በምናገኝበት ቀን የማይረባ ውሳኔ ልንወስን እንችላለን እስከመጨረሻው መጽናት ነው ።
ትዕግስትን ያዘወተረ ሰው ይድናል ማቴዎስ ፳፬፥፲፬
ሁል ጊዜ ያደረጋት

አባ ገብረ ኪዳን🤍

🌺ቅዱስ ዑራኤል 🌺   ❤️❤️☦️❤️❤️እንኳን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ በጥር 🌟🌟ቀን ተሾመ፡፡በመጽ...
30/01/2026

🌺ቅዱስ ዑራኤል 🌺
❤️❤️☦️❤️❤️

እንኳን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ በጥር 🌟🌟ቀን ተሾመ፡፡

በመጽሐፈ ሄኖክ እንደተገለጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሠማራል፡፡

ለነቢዩ ሄኖክም የሰማይን ምሥጢርና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ የገለጸለት፤ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡
ሄኖ📖📖🌟🌟፥🌟🌟

በአምላኩ አማላጅነቱን ተማጸኑት።

በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልዐክ ነው።

አሁንም ይህ ዓለም በአማላጅነቱ አምኖ ጸበሉን ቢጠጣ ከክፉ በሽታ እንደሚፈወሱ ቃልኪዳን ተሰጥቶታል፣

የቅዱስ ዑራኤል በረከት እና ረድኤት በእኛ ላይ ይደርብን, ከክፉ ነገር ይጠብቀን;አሜን🙏

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️ጥር 🌟🌟 በዚህች ዕለት ለከበረች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል ነው።⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐...
28/01/2026

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

ጥር 🌟🌟 በዚህች ዕለት ለከበረች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል ነው።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ"
ትርጉም:-
"ሞት ለሟች ይገባዋል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል"
☦️ቅዱስ ያሬድ

እግዚአብሔር አምላክ በእናቱ በእመቤታችን አማላጅነት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሠውረን፡፡ አሜን!🙏

🌷መልክአ ማርያም📚ንግሥት ሆይ ፣ በማይታየውና በማይዳሰሰው ሁሉ ቁጥር ሰላም እያልሁ፡፡ የድንግልናሽን ምስጋና አፌ ሁል ጊዜ ይናገራል፡፡ እስከ ዘላለሙ አሜን፡፡ ምልጅዋ ረደኤትዋ አይለየን አሜ...
28/01/2026

🌷መልክአ ማርያም📚

ንግሥት ሆይ ፣ በማይታየውና በማይዳሰሰው ሁሉ ቁጥር ሰላም እያልሁ፡፡ የድንግልናሽን ምስጋና አፌ ሁል ጊዜ ይናገራል፡፡ እስከ ዘላለሙ አሜን፡፡ ምልጅዋ ረደኤትዋ አይለየን አሜን🤲💗

🥀ውድ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🙏❤️               28 አማኑኤል (ጌና)               29 በዓለ እግዚአብሔር (ልደት)"ሁለቱ የተለያዩ አይደሉም። ሁለቱም የጌ...
05/01/2026

🥀ውድ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን🙏❤️
28 አማኑኤል (ጌና)
29 በዓለ እግዚአብሔር (ልደት)

"ሁለቱ የተለያዩ አይደሉም። ሁለቱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያዎች ናቸው። ጌና በንዑሳን የጌታ በዓላት ሲከበር፣ ልደት ደግሞ በዐበይት በዓላት ይከበራል። ሁለቱም ግን የጌታ ልደት መታሰቢያዎች ናቸው። ጌታችን የተወለደ ታኅሣሥ 29 ነው። በተአምር ማርያም በ28ም የተወለደበት ነው። በ29ኝም የተወለደበት ነው የሚለው ሁለት ጊዜ ከድንግል ማርያም ተወልዶ አይደለም።

በ28ም፣ በ29ም የጌታ ልደት መታሰቢያ እንደሆነ ለማሳየት ነው እንጂ ጌታ የተወለደ በ29 ነው። በልደቱ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑንና በዚህም ምክንያት አማኑኤል መባሉን እያሰብን ታኅሣሥ 28ትን እናከብራለን።

29 ደግሞ የተወለደበት መሆኑን እያሰብን እናከብረዋለን። ሌላው ነገ ማለትም ታኅሣሥ 28 ገሐድ ነው። የሚጾመው እስከ ሥርቀተ ወርኅ። እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ነው።

ምንጭ፦ መምህር በትረ ማርያም

Deacon Mekonen Galcha

‹‹ታህሳስ 24›› የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የልደታቸው መታሰቢያ በዓላቸው ነው።የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው። የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግ...
02/01/2026

‹‹ታህሳስ 24›› የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የልደታቸው መታሰቢያ በዓላቸው ነው።

የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው። የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር።

መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች።

በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክልዬ ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ስላሴን አመሰገኑ።

ሁለተኛ ተአምር የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ፤ ህጻኑ ተክልዬ ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ።

የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን።

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምልጃ አይለየን🙏

Address

South
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deacon Mekonen Galcha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share