My Views

My Views Providing genuine information.

28/01/2026

ወደ ኦርቶዶክስ የማልመለስበት ምክንያት ይህና ያ ነዉ ብላለች እየተባለ በስሜ እየተፃፈ ፓስት የሚደረግ ፅሁፍ ብዙዎችን ሲያከራክር አልፎ ተርፎም የኦርቶዶክስ መምህራን የኔ ፅሁፍ እንደሆነ አምነዉ ለኔ የማይገባኝን መልስ ጭምር ሰጥተዉበት አይቼ አዝኛለሁ።
የኔ ትክክለኛ ስምም ሆነ ፔጅ አፃፃፍ Sofia Shibabaw ሲሆን Sofiya Shibabaw በተሰኘ የዉሸት አካዉንት ሁልጊዜ ያላልኩትን አለች በማለት ለክርክርና ንትርክ ሲዳርጉኝ አያለሁ።
ሰሞኑን ደግሞ የግእዝ ቅዳሴዎችን ፓስት በማድረጌ ተወዛግበዉ መሆኑ ይሆናል ከኦርቶዶክሳዉያን ጋር ለማቃቃር ይሁን ለማማር
ወደ ኦርቶዶክስ የማልመለሰዉ ለዚህና ለዚህ ነዉ አለች እያሉ ደጋግመዉ ይለጥፋሉ።

የሚገርመኝ የዉሸት ሲሆን ላይኩም ሼሩም ኮሜንቱም ይበዛል።
እኔ ከኦርቶዶክ ቤተ ክርስትያን ወጥቻለሁ ብዬም ስለማላዉቅ የማልመለሰዉ ለዚህና ለዚያ ነዉ ብዬ ልፅፍ ፈፅሞ አልችልም።
እናት ቤክርስትያን ላይ ጥያቄ ሲኖረኝ በአክብሮት እንደልጅ ጥያቄዬን አቀርባለሁ እንጂ ለክርክርና ለንትርክ ድፍረቱም ፍላጎቱም የሌለኝ መሆኑ ይታወቅልኝ!!

21/01/2026
 #ካዎ ጦና ጋጋ ማን ናቸው?👇👇👇👇ካዎ ጦና ጋጋ ከአባታቸው ከቦሻሻ ጋጋ ጎቤ እና የዘር ሀረጋቸው ከአርሲ ኦሮሞ ማዳልቾ ከሚባል ጎሳ ከሚመዘዙ እናታቸው ከአቤንቶ ዎርቄ ጎባና በ1858 ዓ.ም ...
21/01/2026

#ካዎ ጦና ጋጋ ማን ናቸው?👇👇👇👇

ካዎ ጦና ጋጋ ከአባታቸው ከቦሻሻ ጋጋ ጎቤ እና የዘር ሀረጋቸው ከአርሲ ኦሮሞ ማዳልቾ ከሚባል ጎሳ ከሚመዘዙ እናታቸው ከአቤንቶ ዎርቄ ጎባና በ1858 ዓ.ም በጊዜው ዳልቦ ጋሩዋ/ካዎ ጎቤ ጋሩዋ/ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተወለዱ፡፡ ጦና የቦሻሻ ጋጋ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ ዴሌ፣ሀሉ እና አላምቦ የሚባሉ ሦስት ወንድሞች እና ቴማሜ እና ቡንአሬ የሚባሉ ሁለት እህቶች በአጠቃላይ አምስት ወንድምና እህት ነበሯቸው፡፡

ካዎ ጦና በልጅነታቸው እንደማንም የነገስታት ልጅ በአያታቸው በካዎ ጎቤ ቤተመንግስት የፈረስ ጉግስ፣ አደን፣ ባህላዊ የእርሻ አሠራር፣ የለቅሶ፣ የሰርግና ሌሎችን ባህላዊ ሥርዓቶችን በሞግዚታቸው አቶ ባዳቾ(በኋላ ግራዝማች) አማካይነት ሙሉ እውቀት በማግኘት በድሎትና በእንክብካቤ እንዳደጉ ይታወቃል፡፡ ካዎ ጦና ከልጅነታቸው ጀምሮ በጣም ንቁ እና ነገሮችን የመረዳት ችሎታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በሽማግሌዎች ዘንድ ለወደፊት ጠንካራና ትልቅ ኃላፊነት ሊረከቡ የሚችሉ መሆናቸውን ገና ከጥዋት ጀምሮ ያስመሰክሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ጦና ከልጅነታቸው ጀምሮ ከእድሜ እኮዮቻቸው ጋር ትግል(Baaxiyaa) የመግጠም ጨዋታን የሚወዱና በዚህም የአካባቢውን ወጣቶች በትግል ከማሸነፍ የማይመለሱ በመሆኑ ጦና አሸናፊ ነው(Xooni Xooniyaaga) እየተባለ ይዘመርላቸው እንደነበር ይነገራል፡፡

ከዎ ጦና በነበሩበት ዘመን ዘመናዊም ሆነ የቤተክርስቲያን ትምህርት ወደ አካባቢው ያልገባ በመሆኑ ትምህርት ለመማር ዕድል ያላገኙ ቢሆንም በጊዜው ለነገስታት ልጆች የሚሰጠውን የሕይወት ክህሎት ትምህርት በጥብቅ ሥነ-ሥርዓት ተከታትለዋል፡፡ ይህም የዎላይታ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት፣ባህላዊ ህጎችንና ደንቦችን፣ የጦር ስልትን፣ አደንና የውሃ ዋናን የእርሻ አሠራርን፣ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትን እንዲሁም የንግድ ሥርዓትን ከሽማግሌዎችና ከባለሙያዎች በጥንቃቄ እንደተማሩ ይነገራል፡፡

በ1885 መጨረሻ አካባቢ አያታቸው ካዎ ጎቤ በጠና በመታመማቸው አስተዳደራዊ ሥራውን በሚገባ መፈጸም ባለመቻላቸው የወላይታ ሁሉንም ጎሳዎች የሚወክሉ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ ቤተመንግስት/ካዎ ጋሩዋ/ በመምጣት ንጉሱ ቀጣዩን አዲስ ንጉስ እንዲያስታውቋቸዉ ይጠይቃሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ካዎ ጎቤ ልጃቸውን ሀዳሮን እንዲያነግሱ ይነግሯቸዋል፡፡ ነገር ግን የዎላይታ ሽማግሌዎች በመሉ ድምጽ የታላቅ ልጅ እያለ ታናሽ አይነግስም በማለት ጦናን ከንጉስ ጎቤ ይውንታ ውጪ በሕዝብ ፍላጎት ብቻ በመስከረም/ግፋታ/ ወር 1866ዓ.ም የንግሥና ቀለበት በማጥለቅ አነገሷቸው፡፡

ነገር ግን ጦና ገና የ12ዓመት ልጅ ስለነበሩ 20 ዓመት እስኪሞላቸው በዎንቤቶ(መስፍን) ሶራቶ ሞግዝትነት ሲመሩ ቆይተው ከ7ዓመታት የሞግዝት አስተዳደር በኋላ በሙሉ ኃላፊነት አገር መምራት እንደጀመሩ የብሔሩ አፈታሪክና የተጻፉሁፍ መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡

የቅድመ አያታቸው ማለትም የንጉስ ዳሞቴ አስተዳደር በብዙ መልኩ ለህዝቡ ምቹ ስላልነበረ ሰላማዊና ዲሞክራሲዊ በሆነ ተቃውሞ ህዝቡ ካዎ ዳሞቴን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ ልጃቸውን ማለትም የንጉስ ጦናን አያት ንጉስ ጎቤን አነገሰ፡፡ የአያታቸው የንጉስ ጎቤ ዘመን ወላይታ ላይ እጅግ የተረጋጋ የብልጽግና ዘመን ነበር፡፡ ይህ ጊዜ ቀደም ሲል በአጉራባች ህዝቦች ተወርሮ የነበረውን የወላይታን መሬት የማስመለስ ዘመቻ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀበትና ዎላይታ አሁን ያለውን የድንበር ቅርጽ የያዘበት ዘመን ስለነበር የጎቤ ዘመን በዎላይታ ታሪክ ውስጥ ህዝቡ በተሟላ ሰላም የኖረባቸው አርባ ሶስት ዓመታት ነበሩ፡፡

የንጉስ ጦና የሥልጣን ዘመን እንደ አያታቸው ካዎ ጎቤ ሁሉ ለሕዝቡ የተትረፈረፈ እህልና ሀብት የነበረበት የጥጋብና የብልጽግና ዘመን ቢሆንም ወቅቱ አብሲኒያዎች በሥልጣን ሽኩቻና በድንበር መስፋፋት የተወጠሩበት ጊዜ በመሆኑ በተለይም የአፄ ዮሐንስን ሞት ተከትሎ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በ1881 ዓ.ም ራሳቸውን ንጉሰ ነገስት ዘኢትያጵያ በማለት ዘውድ ከጫኑ በኋላ፡፡

ቀደም ሲል በሸዋ የጀመሩትን የድንበር ማስፋፋት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ተካታታይ ጦርነቶችን ዎላይታ ላይ የከፈቱበት ጊዜ በመሆኑ የዎላይታ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ትልቅ ስጋት ላይ የወደቀበት ወቅት በመሆኑ የንግሥና ዘመናቸው በውጫዊ ግፊት ምክንያት በከፍተኛ ጫና ላይ የወደቀበት ወቅት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ካዎ ጦና መላውን የዎላይታ ህዝብ አንድ በማድረግ ለሰባት ዙሪ የመጣዉን የምኒልክን ሠራዊት ፍጹም በማይታመን ሁኔታ በጊዜው ኃያላን መንግሥታት እንኳን ያላሰቡትን “ባዮሎጂካል” የጦር መሳሪያ ማለትም ፈንጣጣን እና ንብን ጭምር በመጠቀም ዎላይታን እንዲወጋ ከዳግማዊ ምኒልክ የተላከውን ሠራዊት በተለያየ ጊዜ አፈር ከመሬት በማልበስ መልሷል፡፡

ነገር ግን በ1887ዓ.ም ዘመናዊ የጦር መሳሪያና ሁሉንም የምኒልክ የጦር መሪዎችንና ሚንስተሮቻቸውን እንዲሁም ምኒልክ እራቸው በአካል በተሳተፉበት የመጨረሻ ዙር ጦርነት የጦናን የጦር ስልት ከአንዳንድ አገርንና ህዝብን ከከዱ ሰዎች አማካይነት መበውስድ ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ጦናን በጥይት በማቁሰልና በመማረክ ወደ አዲስ አባባ በመውስድ ፊት በር ተብሎ በሚጠራው ከታላቁ ቤተመንግሥት ፊት ለፊት በሚገኘው ቦታ በግዞት እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡

አንዳንድ የጽሁፍ መረጃዎች ንጉስ ጦና በአዱዋ ጦርነት ወቅት ከግዞት በመውጣት ንጉሰ ነገሥቱ ሁሉንም ሹማምንቶች ይዘዉ ወደ ጦርነቱ ሲሄዱ ሀገሪቱ ውስጥ የአስተዳደር ክፍተት እንዳይፈጠር ኃላፊነት እንደሠጧቸው የሚገልጹ ቢኖሩም (አካሉ ወልደማሪየም ሩሕ መጽሔት ታህሳስ 1985 ገጽ 10-11 ይመልከቱ) ነገር ግን ጦና በአድዋ ጦርነት ሠራዊት የመምራት ሚና ተሰጥቷቸው በጦርነቱ እንደተሳተፉ በርካታ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ዳግማዊ ምኒልክ ከብዙ ማግባባት በኋላ ጦናን ክርስትና በማስነሳት በ1895ዓ.ም መልሰው የወላይታን አውራጃ እንዲገዙ ከጦና ጋር የጠበቀ ዝምድና በመሻት ከሸዋንግዥት(ሾንግቴ) ጋር (Political Merge) የፓለቲካ ጋብቻ እንዲፈጽሙ በማድረግ እንዲሁም ስድስት መቶ ጠብመንጃና ብዙ ጋሻ መሬት በጉልት መልክ በመስጠት ወደ ወላይታ ላኩዋቸው፡፡ የዎላይታ ህዝብ በሸዋን ግዥት ጋብቻ ዙሪያ ደስተኛ ስላልነበረ “Shonggitee Wolayitta Bayzzida Badame” በማለት ስለእሰቸው ቅሬታውን ይገልጽ ነበር፡፡

ጦናም ከምኒልክ በተሰጣቸው የጦር መሳሪያ ከምኒልክ ጋር ስዋጋ አልረዳችሁኝም በማለት አጎራባች ህዝቦችን በመውጋታቸው ከንጉሰ ነገስቱ እውቅና ውጪ ጦርነት ከፍታሃል በመባል ከሥልጣን እንዲወርዱ ተደርገው እንደገና ለግዞት ወደ አንኮበር እንደተላኩ ይነገራል፡፡ በዚህም ምክንያት ጦና በምኒልክ ሥር ዎላይታን ያስተዳደሩበት ጊዜ እጅግ አጭር ነበር፡፡

በመጨረሻም ንጉስ ጦና ከግዞት በመውጣት ወደ አዲስ አበባ በመመለስ በ1909ዓ.ም ተፈጥሯዊ ሞት በመሞት አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያ አጠገብ በሚገኘው ባለወልድ ቤተክርስትያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም መቃብራቸው በዚያ ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ንጉስ ጦና በህይወት ዘመናቸው የዎላይታን ህዝብ አንድ አድርጎ በመምራት ለፈጸሙት ተግባር የህዝቡ አንድነት ተምሳሌት ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ንጉስ ጦና በዘመናቸው በማህበረሰቡ ነባር ሥርዓት በማደግና በማለፍ የራስን አስተዳደር በመምራት፤ ብሔራዊ ኩራት በመሆን፣ ወጣት ሠራዊት በማደራጅትና በመምራት በተከታታይ የመጣውን የጠላት ጦር መክቶ በመመለስ ጀግንነታቸውን አስመስክረዋል፡፡

በዘመኑ የሰዎች የፈጠራ ሥራ እንዲያድግና የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች የምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማደረግ ለዕደ-ጥበብ ሥራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሁሉንም ባለሙያዎችን አንድ ቦታ በማሰባሰብ የጎጆ እንዱስትሪ ለማስፋፋት ያደረጉት ጥረት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

በታሪክ ምሁር አቶ #አዳነ አይዛ የተዘጋጀ

 #ኩኔ  #ደመላሽ  #የዶክተሬት  #ድግሪ  #ለመጀመር  #የሚያበቃውን  #ምዘና  #በኩራት  #በማለፉ  #ከልብ  #ደስ  #ብሎኛልና  #እንኳን  #ደስ  #ያለህ  #ያለን  #እላለሁ።በፕሮፌሰ...
20/10/2025

#ኩኔ #ደመላሽ #የዶክተሬት #ድግሪ #ለመጀመር #የሚያበቃውን #ምዘና #በኩራት #በማለፉ #ከልብ #ደስ #ብሎኛልና #እንኳን #ደስ #ያለህ #ያለን #እላለሁ።

በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ትምህርት ሚንስተር በአዲሱ የትምህርት ምዘና መሰረት የ3ኛ ዲግሪ (PHD) ትምህርት ለመጀመር የሚያበቃውን የNGAT ፈተና ማለፉን በሰርተፍኬት አረጋገጠ።

አሁን ዶክተር ኩኔ ለመባል ስፓንሰር እና አራት ዓመት ብቻ ነው የሚያስፈልገው።

ስለዚህ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሁል ጊዜ ስፖንሰር በመፈለግ ለጉድለትዋ ሙላት ለሆነው ልጃችን ለአራት አመት ትምህርቱ ስፖንሰር በመፈለግና ከቻልንም በመሆን ደስ እናሰኘው።

ኩኔ በልህቀት ከፍ ባለ መጠን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከፍ ያደርጋታልና ተባብረን ከፍ እናደርገው በማለት ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

Kune Demelash kassayeን የምትወዱት ይህን መልእክት ለሁሉ አድርሱልኝ።

Address

S**o
HTTPS://WWW.GOOGLE.COM/MAPS/PLACE/SODO/@6.8651426,37.7623961,15Z/DATA=!4M2!3M1!1

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when My Views posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to My Views:

Share