26/03/2025
ዎላይታ ቱሣ
1989 ዓ/ም ክረምት ላይ ከእነ ሙሴ ሙንኤ፣ አብርሃም
ባልቻ፣ አብርሃም ጩርፎ ወዘተ በኃላ ተቀዛቅዞ የነበረው
የዎላይታ እግር ኳስ ምስጋና ለቄስ አባ ጂኖ ቤናንቲ
ይግባና ዳግም አንሰራራ፡፡
በዓመቱ ከዞን አሸናፊነት ቀጥሎ የደቡብ ክልል ጥሎ
ማለፍ አሸናፊ መሆኑን በማወጁ ወደ ጂማ ያቀናው ቱሣ
ለዋንጫ ለማለፍ በወቅቱ ታዋቂ ተጫዋቾችን የያዘውን
ኒያላ ገጥሞ 3:0 ከመመራት ተነስቶ በድንቅ ልጆቹ ብቃት
ታግዞ አሸናፊ የሆነበት ከባዱ ጨዋታ አይረሳም፡፡
በፍጻሜው ጨዋታ አልማ (አማራ ልማት ማህበር)
የገጠመው ዎላይታ ቱሣ 1:0 በማሸነፍ የ1989 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ፡፡
በዚህም 1990 ዓ/ም ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ
confi.ዋንጫ ተሳትፎ ከኤርትራው ቀይ ባህር ቡድን ጋር
ተጫውቶ በደርሶ መልስ ጨዋታ በድምር ውጤት መሸነፉና
እንደተመለሰ ሆን ተብሎ ቡድኑ እንዲፈርስ መደረጉ
ያንገበግባል፡፡ ሀላባ ቁሊቶ ድረስ በመኪና ተንጠልጥለን
የሄድንበት የአቀባበል ሂደት ገራሚ ነበር፡፡
እልህ አስጨራሹና ተስፋ የማይቆርጠው ደፋሩ የቡድኑ
አምበል አሰፋ ሆሲሶ፣ ጌታሁን ታደሰ (ጌቼ) የተባለ አሞራ
በረኛ ብቃቱን ለመግለጽ ቃላቶች ያጥሩኛል (የቅ/
ጊዮርጊስና ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረ፣ ዘርሁን የተባለ
ጎበዝ በረኛ ( አሮጌ አራዳ)፣ በአስተማማኝ የተከላካይ
መስመር ታከለ ቡቼ፣ አገኜው፣ ሳንቾና በኃላ ላይ ፔሌ
(በቀለ ባልቻ) ፣ጉጌ፤ ገሬ የሚባሉ የአርባምንጭ ልጆች
ወዘተ እያሉ ጎል ማስቆጠር ይናፍቃል፣ አስጨናቂ ታቦር
የተባለ በራሪ ሰው፣ የልጅ አዋቂ አሸናፊ ደበበ፣ ባቡሬ
ጊጊሩ፣ ምስጋና ባንጫ፣ የፊት ለፊት መስመሩን የሚመሩት
የጭንቅላት ኳስ በመግጨትና ጓል በማስቆጠር አደገኛ
የነበረው ሙሴ ጳውሎስ፣ ኳሷን የፈጠሩ ያህል
የሚያሰቃዯት ፤ ሙሉ በሙሉ የዘመናዊ አጥቂ ባህሪ
የተላበሱት ቃቆ ( ኢብራሂም ረሽድ) ከሶዶ እና ክሪዝ
(አለማየሁ የአባቱን ስም ረሳሁት) ከአርባምንጭ
በጥበባቸው ገዙን ፤ ማረኩን እስከ አሁንም ድረስ ሌላ
በእነሱ ደረጃ የተሰራ ኢትዮጵያዊ ጨራሽና አዝናኝ አጥቂ
አላየሁም፡፡ ስማቸውን ያላስታወስኳቸውን ይቅርታ
ተማፀንኩ፡፡
Wolaytta tuussaa እና ሶዶ ከነማ ያደርጉ የነበረው
የደርቢ ጨዋታ ወንድማማቾችን ቤት ውስጥ ለሁለት
ከፍሏል፤ የተጣላ የተኮራረፈ ስንቱ ነበር መሰላችሁ ፡፡
በቱሣ አልጋ ወራሽ ዎላይታ ድቻና በሶዶ ከነማ ቡድኖች
ዳግም የዎላይታ ደርቢ ጨዋታ ለማየት እንታደል ይሁን?
አይዞን ሶዶ ከነማ!!
የቱሣ አርማና ስያሜ ግን ከልቤ አልወጣ ብሎ
አሰቃይቶኛል፡፡ ከታጣ አርማና ስያሜ ይናፍቃል፡፡
ዎላይታ ቱሣ ከኳሱ በተጨማሪ በዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ
ለዎላይታ ባለውለታ ነው፡፡ ካሙዙ ካሣ የማን ውጤት
መሰላችሁ !!
ለቄስ አባ ጂኖ ቤናንቲ ክብርና አድናቆት አለኝ፡፡
ዎላይታ ቱሣ ጣይሳይ ጣዮ
ሚዞፖ ዎቶፖ ዱፎይ ዶዮ
ዎላይቶ ኔ ዎጋ ባሻይ ባዮ፡፡
Photo credit for Mesay p. Thank u
ምንጭ: Amsalu Mesene Wolaita