Alemayehu Bawud

Alemayehu Bawud Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alemayehu Bawud, Digital creator, Arada, Sodo.

02/02/2025

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬ ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳልፏል

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬ ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የፓርቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ 2 ሺህ 100 ተሳታፊዎች በታደሙበት በደማቅ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በትናንትናው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

በጉባኤው 1 ሺህ 700 የድምፅ ተሳታፊዎች እንዲሁም የ15 ሀገራት ፓርቲዎች አመራርና ተወካዮችን ጨምሮ 400 የሀገር ውስጥና የውጭ እንግዶች በተጋባዥነት መገኘታቸውም የሚታወቅ ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ጉባኤው ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ተወካዮችን ባሳተፈና በዴሞክራሲያዊነት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም ጉባኤው መድረኩን የሚመሩ የፕሬዚዲየም አባላትን በመሰየም በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በስፋት መወያየቱንና አጀንዳዎችን መርምሮ ማጽደቁንም ተናግረዋል።

በዚህም የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት እና የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ በስፋት በመወያየት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል ብለዋል።

በመቀጠልም የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚቴ ሪፖርቶች ለጉባኤው ቀርበው ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ መጽደቃቸውንም ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ጉባኤው በፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል ነው ያሉት።

ከአንደኛ ጉባኤ ማግስት በፓርቲው በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ፈተናዎች እና ፈተናዎችን ለማለፍ የተሄደበትን ርቀት በስፋት መገምገሙንም አንስተዋል።

በዚህም የብልፅግና እሳቤ እስከ ታችኛው ህብረተሰብ ክፍል መድረሱ እና እሳቤው ባህል እየሆነ መምጣቱ የተረጋገጠበት ጉባኤ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉባኤው በነገው ዕለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን የፓርቲ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የአመራር ምርጫ ይደረጋል ብለዋል።

ለዚህም በዛሬው ዕለት አስመራጭ ኮሚቴ በመሰየም የዕለቱ ስብሰባ አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ጉባኤው ለመጪዎቹ ዓመታት የሚያገለግሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

23/01/2025
19/01/2025

"ብርሃነ ጥምቀቱ ክርስቶስ የትህትናን ኃያልነት በተግባር ያስተማረበት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከበር በአስተምሮው መሰረት ትህትናን ተላብሰን ዝቅ ብለን ለማገልገል፤ ለመተባበር እንዲሁም ለአንድነትና ለሰላም ለመትጋት ራሳችንን በማዘጋጀት ሊሆን ይገባል። "

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

19/01/2025
18/01/2025

እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ጥምቀት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ኅብረ ብሔራዊ በዓላችን ነው። በሃይማኖታዊነቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት ወርዶ፣ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ እናስብበታለን። ይሄም የጠፋውን አዳም ለመፈለግ የተደረገ ጉዞ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በወደቀበት በእያንዳንዱ ዱካ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ ተከትሎ ዋጅቶታል። በዚህም አዳምን ወደ ጥንት ክብሩ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከጥንቱ የበለጠ ክብር ሰጥቶታል።

ይሄም ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚያስተምረን ብዙ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የወደቀችበት ብዙ ነው። በእያንዳንዱ በወደቀችበት ውድቀት ተከትለን ማንሣት አለብን። የትርክት፣ የሀገረ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የመግባባት ውድቀቶቿን ወደ ትንሣኤዋ መቀየር አለብን።

ክርስቶስ አዳምን ሲያድነው እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ አለብህ አላለውም። አዳም ዐቅም እንደሌለው ያውቃልና። መዳኑን እርሱ ራሱ ሊያደርገው እንደማይችል ያውቃል። ስለዚህ ክርስቶስ ተገብቶ ፈጸመለት።

ኢትዮጵያችን በዘመናት መከራዎች ደክማለች። በዘመናት ድህነትና ኋላ ቀርነት ተጎድታ ዐቅም አጥታለች። እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ ነበረባት የሚለው አሁን ለውጥ አያመጣም። መደረግ ያለበትን እኛ ልጆቿ ዛሬ እናድርገው። ስለ ሀገራችን እኛ ቤዛ እንሁን። ቤተልሔም መወለድ ካለብን እንወለድ። በባሕር መካከል መቆም ካለብን እንቁም። መሰደብ ካለብን እንሰደብ፣ መሰቀል ካለብንም እንሰቀል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያመጣ ይሁን። ዛሬ እያደረግነው ያለነውም ይሄንኑ ነው።

ጥምቀት ባህላዊ በዓላችንም ነው። የኢትዮጵያ የመስክ ላይ ትዕይንት ማቅረቢያ በዓል ነው። መስኩና ወንዙ ይታይበታል። ልብሳችን እና የወግ ዕቃዎቻችን ለዓለም እናሳያለን። የፀጉር አሠራራችንን እና ዜማዎቻችንን እናቀርባለን። ጥምቀት የኢትዮጵያ ባህል የአደባባይ ሙዝየም ነው።

ብዙ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይሄንን ወቅት ከሚመርጡበት ምክንያቶች አንዱ ይሄ የአደባባይ ሙዝየም ነው። ከገጠር እስከ ከተማ ፤ ከዳር እስከ መሐል፤ ከውጭ እስከ ሀገር የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው።

ጥምቀት ኅብረ ብሔራዊ በዓልም ነው። የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ለማየት የፈለገ ሰው አንዱ አማራጩ የጥምቀት አደባባይ ነው። በአንድ አደባባይ ሺህ ዓይነቱን ኀብረ ብሔራዊ ማንነታችንን ማየት ይቻላል። የክት የተባለው የባህል ልብሳችን ይወጣል፤ ታይተው የማያውቁ ጌጣጌጦች ብቅ ይላሉ፤ በጥምቀት የኢትዮጵያን መልከ ብዙ ገጽታ ማየት ይቻላል።

እነዚህን የመሰሉ ዕሴቶቻችንን ስላስረከቡን ቀደምቶቻችንን እናመሰግናቸዋለን። ጥምቀት ከተማን ከገጠር ያገናኛል። ብዙዎች ወገኖቻቸውን ለማግኘት ገጠር ይወርዳሉ። የውጭውንም ከሀገር ቤት ያስተሣሥራል። ሚልዮን ወገኖቻችን ጥምቀትን አብረውን ለማክበር ከውጭ ገብተዋል። ይሄም ኅብረ ብሔራዊ ትሥሥራችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

የጥምቀትን አስተምህሮ ለሀገር ግንባታ በመጠቀም፤ ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት እና ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር በዓሉን እንድናከብር አደራ እላለሁ።

በድጋሚ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን።


ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥር 10፣ 2017 ዓ.ም

18/01/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ጥምቀት ፍጥረታትን የፈጠረው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከዮሐንስ ዘንድ የተጠመቀበት የትህትና መገለጫ በዓል ነው።

ኃይማኖታዊ እሴቱንና ትውፊቱን ጠብቆ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፤ ከከተራው ጀምሮ አብሮነት፤ አንድነት፣ ፍቅር እና ትህትና የሚንፀባረቅበት ደማቅ በዓል ነው።

ብርሃነ ጥምቀቱ ክርስቶስ የትህትናን ኃያልነት በተግባር ያስተማረበት በመሆኑ፤ በዓሉን ስናከበር በአስተምሮው መሰረት ትህትናን ተላብሰን ዝቅ ብለን ለማገልገል፤ ለመተባበር እንዲሁም ለአንድነትና ለሰላም ለመትጋት ራሳችንን በማዘጋጀት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በመሆኑም እኛ የክርስቶስን የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌትነት በመከተል፤ መተሳሰብንና በጎነትን ይበልጥ በማጎልበት፤ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲሁም በአንድነት ለሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻችንን ለመወጣት ቃል በመግባት ማክበር ይገባናል፡፡

በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የሆነዉ ጥምቀት ከኃይማኖታዊ ይዘቱና ሥርዓት በተጨማሪ በዓለም የሰው ልጅ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ የጋራ ሀብታችን በመሆኑ፤ በዓሉ ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡

በዓሉ የሀገራችንን መልካም ገፅታ ለዓለም የምናሳይበት በመሆኑ፤ መላው የሀገራችን ብሎም የክልላችን ህዝቦች በዓሉን ለመታደም ከተለያየ የዓለም ጫፍ የሚመጡ እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በፍቅር በመቀበል፤ በትህትና እንድታስተናግዱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

ፈጣሪ ሀገራችን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

18/01/2025

አቶ አደም ፋራህ ለከተራ እና ጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለከተራ እና ጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ አደም በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

18/01/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ የከተራና ጥምቀት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጥምቀት በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢያት የወደቀውን የሰው ልጅ ለማንፃት በባህረ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀበትና በጥምቀቱም ድህነት ያገኘንበት ታላቅ በዓል ነዉ።

በዓሉ በዓለም በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የወድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነ የአደባባይ በዓል ነዉ።

ይህን መነሻ በማድረግም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፤ የሳይንስና የባሕል ተቋም «UNESCO» በዓሉን ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች መካከል እንደመዘገበዉ ይታወቃል።

ይህ ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል ከሕዝቡ ባህላዊ እሴት ጋር ጥብቅ ትስስር ያለው በመሆኑ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውም በዚያዉ ልክ የጎላ ነዉ።

በመላው የሀገራችን ክፍሎች በድምቀት የሚከበረው የከተራ እና የጥምቀት በዓል ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ትዉፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ወጣቱ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።

በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ፣ የመቻቻልና የአብሮነት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን ይበልጥ የምናጠናክርበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

በድጋሜ መልካም የከተራና የጥምቀት በዓል !

አቶ አለማየሁ ባዉዲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

17/01/2025

Address

Arada
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alemayehu Bawud posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share