10/11/2025
የመምህራን አድማ ተጀምሯል!
የሲዳማና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ሌሎች ክልሎች ስር ባሉ ከተሞች የሚገኙ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ ጀምረዋል።
"የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል" በሚል የፍጆታ እቃዎች ዋጋ እንዲንሩ ያደረገው የብልጽግና አገዛዝ እስካሁን ምንም አይነት ጭማሪ ሊያደርልን ባለመቻሉ ከፍ ያለ ችግር ላይ ወድቀናል ያሉት መምህራኑ፤ ጥያቄያቸው እስኪመለስ ድረስ በአድማቸው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
ይሕን ተከትሎ በበርካታ ከተሞች ያሉ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ዝግ መሆናቸውን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል።
ቃል የተገባው የደመወዝ ጭማሪ ስላልተገበረ፤ አድማው ወደሌሎች አካባቢዎችና የመንግስት ሠራተኞች ይዛመታል ተብሎ ይጠበቃል።