ኦርቶድክስ መልስም ጥያቄም አላት

ኦርቶድክስ መልስም ጥያቄም አላት ተዋህዶ ለዘለዓለም ትኑር 🙏🙏🙏 በዝህ ፐጅ ለተለያዩ የኑፋቀ ጥያቀዎችን ኦርቶዶክሳዊ መልስ እንሰጣለን እርሶም ይቀላቀሉን።

26/04/2024

ሆሣዕና በህንድ ቤተክርስቲያን 🙏

ሚያዝያን ለመቄዶንያ!በዚህ ወር የኢትዮ ቴሌኮምን ማኅበራዊ ትስስር ገፆች በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር...
25/04/2024

ሚያዝያን ለመቄዶንያ!

በዚህ ወር የኢትዮ ቴሌኮምን ማኅበራዊ ትስስር ገፆች በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለመቄዶንያ ለመለገስ ቃል ስለገቡ!

ስለዚህ እርስዎም የኢትዮ ቴሌኮም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆችን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለመቄዶንያ ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም (https://t.me/ethio_telecom)
ፌስቡክ (https://www.facebook.com/ethiotelecom)
ኢንስታግራም (https://www.instagram.com/ethiotelecom/)
ሊንክዲን (https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom)
ዩትዩብ (https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH)
ቲክቶክ (http://www.tiktok.com/?lang=en)
ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!

ዠToday's best picture ❤❤❤                        #ዘማሪትመልካምስማቸው                   #ሲሎንዲስቲዩብ
25/04/2024

ዠToday's best picture
❤❤❤












#ዘማሪትመልካምስማቸው
















#ሲሎንዲስቲዩብ

የቀዳሜ ሰማዕት ወ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን።🙏🙏🙏
27/10/2023

የቀዳሜ ሰማዕት ወ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን።🙏🙏🙏

"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ፤ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
26/10/2023

"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ፤ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ...
25/10/2023

ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።

መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።

"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና...
25/10/2023

"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
ቅዱስ ባስልዮስ

ሰው ሆይ! ጻድቅ መሆንን ትወዳለህን? አዎን ትለኝ እንደሆነ፥ እንግዲያውስ ለራስህ ንፉግ ለሌላው ግን ቸር ሁን፡፡
21/10/2023

ሰው ሆይ! ጻድቅ መሆንን ትወዳለህን? አዎን ትለኝ እንደሆነ፥ እንግዲያውስ ለራስህ ንፉግ ለሌላው ግን ቸር ሁን፡፡

"እጅግ ምርጡ ጸሎት 'ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ።' ማለት ነው።"(ባሕታዊ ቴዎፋን)
20/10/2023

"እጅግ ምርጡ ጸሎት 'ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ።' ማለት ነው።"

(ባሕታዊ ቴዎፋን)

ክርስቲያን እግዚአብሔርን በእምነት ይፈልገዋል።  ከእእምሮ ይልቅ በልቡ ያምነዋል። በእምነት እግዚአብሔርን ያገኘ ክርስቲያን አካባቢውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ያያል ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን በሌሊ...
19/10/2023

ክርስቲያን እግዚአብሔርን በእምነት ይፈልገዋል። ከእእምሮ ይልቅ በልቡ ያምነዋል። በእምነት እግዚአብሔርን ያገኘ ክርስቲያን አካባቢውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ያያል ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን በሌሊት በገሊላ ባህር በእግሩ ሲመጣ አየው "ጌታ ሆይ በባህር ላይ በእግሬ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው ጌታችንም ፈቀደለት። ቅዱስ ጴጥሮስ በባህሩ ላይ በባዶ እግሩ ሄደ ነገር ግን የባህሩን ኃይል አይቶ ፈራ ይሰጥምም ጀመረ። ማቴ 14፣22-33 ቅዱስ ጴጥሮስ የሰመጠው ጌታችንን ማየት ትቶ ባህሩን በመመልከት ስለፈራ ነው። ዓለምንና መከራዋን የምናይ ከሆነ እንፈራለን። የምንጠቀመው ስሌታዊ አእምሯችንን ከሆነ እንፈራለን። የምናምነው ከልብ ከሆነ ግን ክርስቶስን እያየን ባህር መከራውን እንሻገራለን።

+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++ ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ...
17/10/2023

+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

የአባታችን በረከታቸው ይደርብን።
16/10/2023

የአባታችን በረከታቸው ይደርብን።

በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታች...
14/10/2023

በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታችን ሰይጣን ያገኘው፣ በኃጢአት የጣለው ሰውም ኃጢአቱን በመናዘዝ የንስሐን መድኃኒት ተቀብሎ መዳንን ማፈር የለበትም፡፡

ቆስሎ ቁስሉን መናገር ያፈረና በቶሎ መድኃኒት ያልተደረገለት ወታደር ቁስሉ ወደ ካንሰር ይለወጥና አመርቅዞ መላ ሰውነቱን በመምታት ይጎዳዋል፡፡ ጉዳቱን ቶሎ የተናገረ ታማሚ ግን ታክሞ በመዳን ወደ ጦር ሜዳው ይመለሳል፡፡ ቁስሉን ባለመታከሙ ወደ ካንሰር የተለወጠበትና ያመረቀዘበት ሰው ግን ሊድን አይችልምና ወደ ጦር ሜዳው ሊመለስ አይችልም፡፡

እንደዚሁ ሁሉ በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው እንደ ወታደር ነው። በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው በኃጢአት ወድቆ "በኃጢአት ወድቄአለሁ" ብሎ የተናዘዘ የንስሓን መድኃኒት ያገኛል፡፡ ኃጢአቱን የደበቀ ግን ሊድን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ታማሚው መድኃኒት አግኝቶ ከቍስሉ ሁሉ ይድን ዘንድ በሽታውን ሁለት ዲናር ወስዶ ለሚያክመው ባለ መድኃኒት አልተናገረምና።"

(ቅዱስ አፍርሐት ዘሶርያ - በእንተ ንስሐ ገጽ 52)

🔮 ምክረ ቃል 🔮🔅 አንድ አባት ልጆቹን ሲመክር እንዲህ አለ። "ክፉ ሀሳብና ስለ ጊዜያዊ ስኬቶች ወይም ኃላፊነቶች አብዝቶ የሚጨነቅ ሰው በነፍሱ ለስንፍና ይዳረጋል። ለነፍሱ የሚጠቅመውን ለማድ...
13/10/2023

🔮 ምክረ ቃል 🔮

🔅 አንድ አባት ልጆቹን ሲመክር እንዲህ አለ። "ክፉ ሀሳብና ስለ ጊዜያዊ ስኬቶች ወይም ኃላፊነቶች አብዝቶ የሚጨነቅ ሰው በነፍሱ ለስንፍና ይዳረጋል። ለነፍሱ የሚጠቅመውን ለማድረግ ቸልተኛ ይሆናል። ሥርዓተ አምልኮን በመከታተል ጠንካራ የሆኑ አማኞች ላይም ወደ ክርስቶስ ፍቅር ለመድረስ ወሳኝ በሆኑ የሕይወት ልምምዶች ላይ ሰንፈው ልታዩዋቸው ትችላላችሁ። ስንፍና በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተጠላ ነው፤ ኃጢአትም ነው። ከዚያም በላይ "ከዚህ በላይ ከእኔ ምን ይፈለጋል?" የሚል ትዕቢትም ነው:: ልጆቼ ከሰነፍ ኃጢአተኛ ይሻላል። ኃጢአተኛ የንስሐ ተስፋ አለው፡፡ ለሰነፍ ተሰፋው ምንድር ነው ?"
✨💧✨💧✨💧✨💧✨

✍ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር

ጥቅምት 2፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ የበዛለት፤የቅዳሴ ማርያም ደራሲ፤ የሀገረ የብሕንሳው ኤጲስ ቆጶስ የ አባ ሕርያቆስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ዕለት ነው። የአባታችን በረከት...
13/10/2023

ጥቅምት 2፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅሯ የበዛለት፤የቅዳሴ ማርያም ደራሲ፤ የሀገረ የብሕንሳው ኤጲስ ቆጶስ የ አባ ሕርያቆስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ዕለት ነው።
የአባታችን በረከት በሁላችን ላይ ይደር 🙏🙏🙏

"ጸሎት ለመጸለይ ስታስብ ረጅም ንግግር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም:: እጅን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እንዲህ ማለት ብቻ በቂ ነው "ጌታ ሆይ እንደ ፈቀድህና እንዳወቅህ ይቅር በለኝ":: ነገር ግን ...
12/10/2023

"ጸሎት ለመጸለይ ስታስብ ረጅም ንግግር ማድረግ አስፈላጊ አይደለም:: እጅን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እንዲህ ማለት ብቻ በቂ ነው "ጌታ ሆይ እንደ ፈቀድህና እንዳወቅህ ይቅር በለኝ":: ነገር ግን ፈተናው እየተጋጋለ ከመጣ እንዲህ በል "ጌታ ሆይ እርዳኝ" እግዚአብሔር ምን እንደምንፈልግ ያውቀልና ምህረቱን ይገልፅልናል:: " (አባ መቃርዮስ)

12/10/2023
"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገ...
11/10/2023

"በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልሆነ ነገር ደርሶብህ እንደሆነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልሆነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Address

Tarch'a S**o

Telephone

+251932484366

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶድክስ መልስም ጥያቄም አላት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኦርቶድክስ መልስም ጥያቄም አላት:

Share