ADDIS ZEMEN

ADDIS ZEMEN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ADDIS ZEMEN, Publisher, Tarch'a Sodo.

21/03/2026

የኢሠራ ወረዳ መንግስትና ብልፅግና ፓርቲ በወላድ እናት ላይ እየቀለዱ እንደሆነ ሕዝብ ይወቅ !
በቀን 11/07/2018 በዳሊ ጤና ጣቢያ አንድት ወላድ እናት በምጥ ተያይዛ ወደ 5:00 ሰዓት አከባቢ ገብታለች, ይህች እናት በምጥ ሥርዓት ወይም ሂደት ላይ ችግር ስለነበረባት እስከ ምሽቱ 4: 00 ድረስ ክትትል ተደርጎላት መውለድ ባለመቻሏ ጤና ባለሙያዎች ወደ ሆስፕታል ሪፌር አድርጓታል, ለአምቡላንስ ስደወል የወረዳ አመራሮች ነዳጅ የለንም በማለት ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ ለችግሩ መፍትሔ ከማመቻት ይልቅ ስልክ ዘግቶ ተኝቷል /የወረዳ አስተዳዳሪ,የጤና ኃላፊ, የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ,የፓርቲ አመራሮች ናቸው/ እጅግ ያሳዝናል በእናት እንድህ አይጨከንም, ነዳጅ ልጠፋ ይችላል ግን መፍትሔ ማበጀት ስገባቸው ስልክ መዝጋት የመንግስትና የሕዝብን ሐላፍነት መዘንጋት ነው ,ግን እንደነሱ ያልጨከነ ፈጣሪ ቤተሰብ ተስፋ ቆርጦ እያለቀሰ እያለ ከብዙ ስቃይ በኋላ በቀን 12/07/2018 ጧት 2:00 ሰዓት ገደማ ህይወቷ ተርፎ በሠላም ተገላግላለች, ለስልጠና ለስብሰባ ስሆን የማይጠፋ ነዳጅ ለእናት ስሆን ይጠፋል ወይ? ሕዝብን እየመራው ነው የሚል መንግስት እንደት መጠባበቂያ አንድ በርሜል ነዳጅ ያጣል? ይህን ካጣ ደግሞ ሕዝብን እየመራን ነው ማለት ይቻላል ወይ? ይህንን ሕዝብ ይፍረድ !!!

15/03/2026

ኢሶዴፓ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለምርጫ መዘጋጀቱን አስታወቀ
++++++++++++++++++++

| የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ በምርጫ በመሳተፍ ለሕዝብ አማራጭ ለመሆን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የፓርቲው ሰብሳቢ ራሄል ባፌ (ዶ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ኢሶዴፓ በዘንድሮው ምርጫ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ በመወዳደር ለሕዝብ የተሻለ አማራጭ ይዞ ለመቅረብ እየሠራ ይገኛል።

ፓርቲው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካወጣው የጊዜ ሰሌዳ ጋር በመናበብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወነ ሲሆን፣ ቦርዱ ለውድድር ክፍት ናቸው በሚላቸው አካባቢዎች ሁሉ እንደሚሳተፍ አረጋግጠዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያለፈውን ምርጫ በመገምገም ለዘንድሮው ውድድር ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውና ፓርቲያቸውም ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ወደ ምርጫው ለመግባት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ምርጫው ፍትሐዊና ተዓማኒ እንዲሆን መሬት ላይ አንጻራዊ አስቻይ ሁኔታዎች መፈጠር እንዳለባቸው የጠቀሱት ሰብሳቢዋ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ ግልጽና ቅቡልነት ያለው ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ጽሕፈት ቤቶች እንዲከፈቱ፣ የታሰሩ አባላት እንዲፈቱና ነፃ የምህዳር ሁኔታ እንዲኖር ከሎጀስቲክስ ጋር ተያይዞ ውይይት መደረጉንም ራሄል (ዶ/ር) ጠቁመዋል።
የሰላምና ደኅንነት ጉዳይ የሁሉንም ተሳትፎ የሚፈልግ መሆኑንና መንግሥት የአንበሳውን ድርሻ ቢይዝም፣ ፓርቲያቸውም የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል።

ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለምርጫው ስኬት አስቻይ ሁኔታን ለመፍጠር መሥራት እንዳለባቸው ገልጸው፤ ሕዝቡ የምርጫ ድምፅ መስጫ ካርዱን በመውሰድ በምርጫው ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በማርቆስ በላይ
++++++++++++++++++++

#ምርጫ #ኢሶዴፓ #ፖለቲካ #ኢትዮጵያ #ዴሞክራሲ

17/07/2024
ይህን ያውቃሏ፦....?????የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ከዓለም መንደሮች ለድንጋይ ከሰል ምርት ማስፋፊያነት እንዲፈርሱ ከተደረጉት መንደሮች አንዱዋ ይሆናለች ተብሎ ይጠበቃል ።።።፣፣  ምክንያቱ...
14/06/2024

ይህን ያውቃሏ፦....?????
የዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ከዓለም መንደሮች ለድንጋይ ከሰል ምርት ማስፋፊያነት እንዲፈርሱ ከተደረጉት መንደሮች አንዱዋ ይሆናለች ተብሎ ይጠበቃል ።።።፣፣
ምክንያቱም
ድንጋይ ከሰል የሚሠጠው ጥቅም ከፍተኛ ቢሆንም በአገባቡ ከልተመረተ በአከባቢው እና በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰው ጉዳት የከፉ ስለሆነ ነው።።።
People who are indirectly exposed to coal may be affected by chronic obstructive pulmonary disease (COPD), asthma, lung cancer, and respiratory infection. These diseases may occur due to inhalation of a diversity of environmental air pollutants...

Address

Tarch'a S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ADDIS ZEMEN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category