Ethio Times Online

  • Home
  • Ethio Times Online

Ethio Times Online Provides information as much as a fastest source.

28/06/2025

ጥበብ ለሰነፍ ከፍ ብላ የራቀች ናት፤ በበርም አፉን አይከፍትም።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል ላይ በሚሠሩበት አግባብ ተወያዩ::የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ባሕር ኃይሎች በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክ...
14/03/2025

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል ላይ በሚሠሩበት አግባብ ተወያዩ::

የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ባሕር ኃይሎች በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላም፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በሚኖሩ ትብብሮች ዙሪያ ምክክር መደረጉን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ፤ ትብብሩ በስልጠናና ዐቅም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም አብሮ በመሥራት ተቋማችን የጀመረውን የባሕር ኃይል ግንባታ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ውኃ ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ዝግጁነታችንን የበለጠ ለማጠናከር መክረናል ብለዋል፡፡

በጋራ ባሕር ኃይልን በሚያጠናክሩና በቀጣይ ትብብሮችን ለማመቻቸት ከውይይቱ በኋላ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ከ FMC የተወደ

Foreign Policy በቀይ ባህር ዙሪያ ባስነበበው  ሰፋ ያለ ትንተናው መሰረት ኢትዮጵያና ሚጢጢዋ በሽፍታ ምትመራው ኤርትራ ቀጠናውን የሚያውክ   ጦርነት  ውስጥ ሊገቡ ነውና ከመግባታቸው ...
14/03/2025

Foreign Policy በቀይ ባህር ዙሪያ ባስነበበው ሰፋ ያለ ትንተናው መሰረት ኢትዮጵያና ሚጢጢዋ በሽፍታ ምትመራው ኤርትራ ቀጠናውን የሚያውክ ጦርነት ውስጥ ሊገቡ ነውና ከመግባታቸው በፊት መፍትሄ ሊፈለግ ይገባል ይለናል ።

ይህ ሁሉ ወከባ 130ሚሊየን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ34ዓመታት ዝምታ በውሃላ በሽፍቶች የተቀማውን ባህር በሩን መጠየቅ መጀመሩን ተከትሎ ነው ። ጦር አልሰበቀም ፣ በይፋ አሰብን በጉልበት ለመቀበል እንቅስቃሴ አልጀመረም... ነገር ግን ድምፁን ዝግ አርጎ "ባህር በሬን በሰላም መልሱልኝ " ማለት ከመጀመሩ ኢሳያስ ተሸብሯል ፣ ጀሌዎቹ እንቅልፍ አጥተዋል፣ በጉያችን አቅፈን የኖርነው ባንዳ ማንነቱ መገለጥ ጀምሯል፣ ምዕራባውያን ምን ይከሰት ይሁን በሚል አይናቸውን ጥለዋል፣ በሚሊዮን ሚቆጠሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና Main stream ሚዲያዎች የእለት አጀንዳ ሆኗል ።

ይህ የዚህ የዓለማቼን 10ኛው ታላቅ ህዝብ መጠነኛ ጉምጉምታ ያዘለ ስለ ባህር በር 34 የታመቀ ድምፅ... ያለ ጦርነት እንኳ ምድሩን ምን ያህል እንደሚንጥ ማሳያ ነው።

አዎ በእርግጥም ኢሳያስ በሰላም አሰብን ለባለቤቷ ኢትዮጵያ እንዲያስረክብ ግድ ነው ፤ ከዛ ውጭ አሁን በጀመረው መሰረት የኢትዮጵያ 130ሚሊየን ታላቅ ህዝብ "ሆ"ብሎ ከተነሳ ኢሳያስ የሚያስረክበው ሳይሆን ለምኖ የሚያገኘውን ባህር አይኖረውም ።

ለኢትዮጵያ አሰብን በሰላምም ሆነ በክንዳችን ማስመለስ ብንፈልግም ባንፈልግም የህልውና ጉዳያችን ስለሆነ አማራጭ የለም !

ለኤርትራ ትክክለኛ ሀገር ሆኖ ለመቆምም ሲባል አሰብን ለኢትዮጵያ መመለስ የኤርትራ ህልውና መሰረት ነው !



ከ ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawineት ገፅ

መቀመጫውን ሱዳን ውስጥ በቀይ ባህር የወደብ ከተማ በሆነችው ፖርት ሱዳን የሚያደረገው የራሽያ ፌድሬሽን ባህር ሃይል መቀመጫውን ራስ ዱሜራ ደሴት በማድረግ በቀይ ባህር ላይ ከሚገማሸረው የኢትዮ...
14/03/2025

መቀመጫውን ሱዳን ውስጥ በቀይ ባህር የወደብ ከተማ በሆነችው ፖርት ሱዳን የሚያደረገው የራሽያ ፌድሬሽን ባህር ሃይል መቀመጫውን ራስ ዱሜራ ደሴት በማድረግ በቀይ ባህር ላይ ከሚገማሸረው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ጋር በጋራ ለመስራት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል።

የጋራ ወታደራዊ ልምምድ፣ ስልጠና፣ የባህር ደህንነት መረጃ ልውውጥ፣ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ስርፀት እንዲሁም በጋራ የባህር ላይ ወንበዴዎችን (Pirates) መከላከል ሥምምነት ከታሰረባቸው ውስጥ ቀዳሚ ጉዳዮች ናቸው።

⚓️

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ቀጠና አስተማማኝ የሰላም ምንጭ!

የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ያለውን አድናቆት ገለፀ። በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የአድናቆት መልዕክት "ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ሆይ ፈጣሪ ካንተ ጋር...
14/03/2025

የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ያለውን አድናቆት ገለፀ። በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የአድናቆት መልዕክት "ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ሆይ ፈጣሪ ካንተ ጋር ነውና ሀገር ወዳድ ልበቀና በሳል እና ጥበበኛ መሪ እንደሆንክ ገና አለም ይመሰክርልሀል እየመሰከርልህም ነው የሀገሬ የኢትዮጵያ መሪ በመሆንህ እኮራብሃለሁ" ብሏል።

በመጨረሻም እውነት ካንተ ጋር ነው ሲል ገልጿል።

ግብጽ ለውስጥ አማጺ ቡድኖች ድጋፍ እያደረገች ነውግብጽ በብዙ ዛቻ ማስቆም ያልቻለችውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ የውስጥ ባንዳዎችን በገንዘብ ገዝታ ፍላጎቷን ለማሳካት የዘመነ ካሴን ቡድን እና ፅ...
14/03/2025

ግብጽ ለውስጥ አማጺ ቡድኖች ድጋፍ እያደረገች ነው
ግብጽ በብዙ ዛቻ ማስቆም ያልቻለችውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ የውስጥ ባንዳዎችን በገንዘብ ገዝታ ፍላጎቷን ለማሳካት የዘመነ ካሴን ቡድን እና ፅንፈኛው ህወሃትን ኤጀንት ማድረጓ እና እነርሱም ለሆዳቸው ሲሉ ለመሸጥ እንደተስማሙ ከወደ ሱዳን የተሰማ መረጃ አመላክቷል።
እነዚህ ሁለት ህገ ውጥ ቡድኖች በሚወረወርላቸው ሳንቲም ፤የግብፅ ተላላኪ በመሆን እና የውስጥ ግጭትን እንዲያጋግሉ ከቻሉም ግድቡ ላይ ጥቃት እንዲያደሩሱ ከግብፅ ተልእኮ እንደተሰጣቸው፤ በተሰጣቸውም ተልዕኮ እንደተስማሙ ተረጋግጧል ።

የልጁን ፍቅረኛ ቀምቶ ያገባው ቻይናዊ መጨረሻው አላማረም::የቀድሞ ፍቅረኛው እንጀራ እናቱ የሆነችበት ልጅ በደረሰበት የአዕምሮ ጭንቀት ሆስፒታል ገብቷል::የልጁን ፍቅረኛ የነጠቀው አባት በባን...
03/01/2025

የልጁን ፍቅረኛ ቀምቶ ያገባው ቻይናዊ መጨረሻው አላማረም::

የቀድሞ ፍቅረኛው እንጀራ እናቱ የሆነችበት ልጅ በደረሰበት የአዕምሮ ጭንቀት ሆስፒታል ገብቷል::

የልጁን ፍቅረኛ የነጠቀው አባት በባንክ ሃላፊነት ላይ በነበረበት ጊዜ በሰራው የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ውሏል

የቀድሞ የባንክ ኦፍ ቻይና ሊቀመንበር የነበረው የ63 አመቱ ሊዩ ሊያንግ ለወጣት ሴቶች በሚያሳየው መማረክ አካባቢው ባሉ ሰዎች እና በጓደኞቹ ይታወቃል፡፡

የመጀመሪያ የትዳር አጋሩን ከፈታ በኋላ ከሶስት የተለያዩ ሴቶች ጋር ትዳር መስርቶ የነበረ ቢሆንም ሚስት የማይበረክትለት ግለሰቡ ከሁሉም ጋር ፍቺ ፈጽሟል፡፡

ግለሰቡ በየጊዜው አግብቶ የሚፈታው ለወጣት ሴቶች ካለው ፍቅር ጋር እንደሚያያዝ የሚጠቅሰው ኦዲቲ ሴንትራል ሁሉም ሴቶች ሊያንግ ከሚገኝበት እድሜ ጋር የማይቀራረቡ ወጣቶች መሆናቸውን ዘግቧል፡፡

በወጣት ሴቶች ከመጠን በላይ መሳቡ ለማንም የተደበቀ ባይሆንም የልጁን እጮኛ እስከመቀማት ያደርሰዋል ብሎ የገመተ ግን አልነበረም፡፡

አንድ ቀን ሊያንግ በቤት ውስጥ በተቀመጠበት ልጁ ከአንድ ወጣት ሴት ጋር ጎራ በማለት ትዳር ለመመስረት የወሰነባት እጮኛው መሆኗን ነግሮት ከአባቱ ጋር ያስተዋውቃቸዋል፡፡

በዚሁ ቅጽበት በልጁ እጮኛ የተማረከው አባት ጥንዶቹን ሰለሚለያይበት እና ልጅቷን የራሱ ስለሚያደርግበት እቅድ መወጠን ይጀምራል፡፡

ከትውውቁ ጥቂት ቀናት በኋላ ልጁ ያስተዋወቀው ሴት እጮኛው ልትሆን እንደማትችል በልጁ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተያያዘው፡፡

የልጅቷ ቤተሰቦች ጥሩ ሰዎች ስላልሆኑ ለልጁ እንደማትገባው በመንገርም ልጁን ለማሳመን ጥረት ማድረጉን ቀጠለ፡፡

ከአባቱ በተደጋጋሚ የሚቀርብብት የአትሆንህም ውትወታ የበረታበት ልጅ በመጨረሻም ከእጮኛው ጋር ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ ይወስናል፡፡

በዚህ እቅዱ የተሳካላት አባት የልጁን የቀድሞ ፍቅረኛ አድራሻ በማፈላለግ ውድ ስጦታዎችን እና ጌጣጌጦችን በመላክ ትኩረቷን ማግኝት ቻለ፤ በጊዜ ሂደትም በትዳር ለመጣመር ይስማማሉ፡፡

አባት አዲስ በጀመረው የፍቅር ግንኙነት ላይ ልጁ እንቅፋት እንዳይሆንበት ከአንድ ጓደኛው ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዲጀምሩ በማድረግ ትኩረቱን ለማስቀየር ሞክሯል፡፡

ከእጮኛው ጋር ከተለያየ ከስድስት ወራት በኋላ የቀድሞ ፍቅረኛው በቅርቡ ሶስተኛ የእንጀራ እናቱ እንደምትሆን የተረዳው ልጅ በድንጋጤ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል፡፡

ከዜናው አስደንጋጭነት የተነሳም በአንድ ወቅት ህመሙ ተባብሶ ሆስፒታል ተኝቶ እንዲታከም ተገዷል፡፡

ከልጁ የቀድሞ እጮኛ ጋር ትዳር የመሰረተው ሊዩ ሊያንግ በባንክ ሃላፊነት ላይ በነበረበት ጊዜ በሰራው የሙስና ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ለአራተኛ ጊዜ የመሰረተው ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል፡፡

በባንክ ኦፍ ቻይና በነበረው የሊቀመንበር ሀላፊነት 3.32 ቢሊየን የን (450 ሚሊየን ዶላር) ህገ ወጥ ብድር በመፍቀድ በቀረበበት ክስ በፍርድ ቤት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

Via Alain News

ምሽት 6:18 ላይ በደንብ ወዝወዝ የሚያደርግ መንቀጥቀጥ በደንብ ተሰምቶኛል!! እናንተ አከባቢስ ኮሜንት ላይ ያስቀምጡ!!Strong mag. 5.0 Earthquake - 63 km NNE of Āw...
02/01/2025

ምሽት 6:18 ላይ በደንብ ወዝወዝ የሚያደርግ መንቀጥቀጥ በደንብ ተሰምቶኛል!! እናንተ አከባቢስ ኮሜንት ላይ ያስቀምጡ!!

Strong mag. 5.0 Earthquake - 63 km NNE of Āwash, Ethiopia, on Friday, Jan 3, 2025, at 12:18 am (Addis Ababa time) - 35 minutes ago

20/12/2024

ችሎታ ማለት ይህ ነው!

Clean and Beautiful Capital city of Ethiopia, Addis Abeba.
15/12/2024

Clean and Beautiful Capital city of Ethiopia, Addis Abeba.

‹‹የበጋው መብረቅ›› ሌተና ጄኔራል ጃገማ ኬሎየጣሊያን ተስፋፊ ኃይል በ1888 ዓ.ም. ዓድዋ ላይ ድል በተመታ በ40 ዓመቱ  ኢትዮጵያን ዳግም ሲወር፣ ዱር ቤቴ ብለው ከዘመቱት እርመኛ አርበኞ...
15/12/2024

‹‹የበጋው መብረቅ›› ሌተና ጄኔራል ጃገማ ኬሎ

የጣሊያን ተስፋፊ ኃይል በ1888 ዓ.ም. ዓድዋ ላይ ድል በተመታ በ40 ዓመቱ ኢትዮጵያን ዳግም ሲወር፣ ዱር ቤቴ ብለው ከዘመቱት እርመኛ አርበኞች ከግንባር ቀደምቱ ጎራ ይሰለፋሉ፡፡ ‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካ ኧረ ጥራኝ ዱሩ…..›› ብለው በተለይ ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት ከፍልሚያው ጎራ በተለይ በምዕራብ ኢትጵያ ከገነኑት የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ ነበሩ፡፡ ሌተና ጄኔራል ጃግማ ኬሎ፡፡ በሽምቅ (ጎሬላ) ውጊያ የተካኑት ‹‹የበጋው መብረቅ›› ጃገማ ገጸ ታሪካቸው እንዲህ ያዘክራል፡፡

ፋሺስቱ የጣሊያን መንግሥት በ1928 ዓ.ም. አገሪቷን በመውረር አዲስ አበባን ሚያዚያ 27 ቀን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ምዕራቡ የአገሪቷ ክፍሎች በመስፋፋት ጭልሞና ጋጂ አካባቢን ተቆጣጥሮ ይዞታውን ለማስፋፋትና ለሚያደርገው ሙከራ የመሸጋገሪያ ምሽግ ጊንጪ አካባቢ በመሥራት ለመጠቀም ሙከራ ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም፣ ሌተና ጄኔራል ጃግማ ኬሎ የመሸጋገሪያ መሥመሮችን በመዝጋትና የደፈጣ ውጊያ በማድረግ የጠላትን ጦር በእንቅስቃሴ ሲገቱ ቆይተዋል፡፡
የበጋው መብረቅ በጦር ሜዳ ውሏቸው በፋሺስቱ የጣሊያን ወራሪ ጦር ላይ ካገኙት አንፀባራቂ ድል አንዱ በኅዳር ወር 1933 ዓ.ም. የተገኘው ነው፡፡ ይህም የአዲስ ዓለምን ጽዮን ማርያም ምሽግ በመሰበር 70 የጣሊያን ወታደሮችን በመግደል፣ 1,500 ጠመንጃ በመማረክ፣ እንዲሁም 80 የወገን እስረኞችን በማስፈታት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

በመጋቢት 1933 ዓ.ም. በጭልሞ ምሽግና ጊንጪ አካባቢ በተደረገ ከፍተኛ ውጊያም የጠላት ጦር ቅስሙ ስለተመታ መኪና ያገኙት ወደ አምቦ ሲሸሹ ሌሎች ወደ አዲስ ዓለም የሸሹ ሲሆን የሸሹትን እግር በእግር መከታተል፣ በየመንገዱ በመቁረጥና በመበተን የጠላት ጦር ከጥቅም ውጭ እንዳደሩ ራሳቸው የጻፉት የግል የሕይወት ታሪካቸው ያትታል፡፡

የሌተና ጄኔራል የጦር ሜዳ ድል አድራጊነት ዝነኝነት በአገር ሁሉ እየናኘ የመጣ ሲሆን፣ በዚሁ በ1933 ዓ.ም. ወደ ጅማ ከዘመተው የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ጦር ጋርም ወታደራዊ ቅንጅት በመፍጠር በደቡብ ምዕራብ የመሸገውን የፋሽስት ጦርን መውጪያና መግቢያ አሳጥተዋል፡፡

በገጸ ታሪካቸው እንደተወሳው፣ በፋሺስት ላይ የፈጸሙት የላቀ ጀብዱና ታላቅ ገድላቸው ‹‹የበጋው መብረቅ›› የሚል የጀግንነት ስያሜ የተሰጣቸው ጄኔራል ጃገማ አገሪቷ ነፃ ከወጣች በኋላና አፄ ኃይለሥላሴ ከእንግሊዝ ስደት እንደተመለሱ ከፍተኛውን ሚና ከተጫወቱት ድንቅ አርበኞች መካከል ስማቸው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጄኔራልን ለማየት ካረፉበት ቦታ ሲደርሱ ሠራዊታቸውን በማሰለፍ ብቻ አልተቀበሏቸውም፡፡
‹‹ገዳይ በልጅነቱ
ዶቃ ሳይወጣ ከአንገቱ
ጃጌ ጃገማቸው
እንደገጠመ የሚፈጃቸው
በአባት በእናቱ ኦሮሞ
ፍዳውን አስቆጠረ ከምሮ ከምሮ!›› በማለት በመፎከር ጭምር እንጂ፡፡

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ከተረጋገጠ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥታቸውን ዳግም በየዘርፉ ሲያደራጁ፣ ፍጡነ ረድኤት ሆነው ከተሰለፉት መካከል ጄኔራል ጃገማ አንዱ ነበሩ፡፡ በውትድርናው ዓለም በተለያዩ ክፍለ ጦሮች በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች በመሥራት እስከ ሌተና ጄኔራልነት ደርሰዋል፡፡

በወቅቱ አጠራር ከሐረርጌ ተነጥሎ ራሱን የቻለው የባሌ ጠቅላይ ግዛት፣ እንዲሁም የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ገዢና የግርማዊነታቸው እንደራሴ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከአራት አሠርታት አገራዊ አገልግሎት በኋላ በ1998 ዓ.ም. ጡረታ ቢወጡም በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ተግባራት ውስጥ ከመሳተፍ ወደኋላ አላሉም።

በቀድሞው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ በጅባትና ሜጫ አውራጃ በደንዲ ወረዳ ዩብዶ በሚባል ሥፍራ፣ ከአባታቸው ከአቶ ኬሎ ገሮና ከእናታቸው ከወ/ሮ ደላንዱ እናቱ ጥር 20 ቀን 1913 ዓ.ም. የተወለዱት ሌተና ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፣ በአካባቢው በሚገኘው የቄስ ትምህርት ቤት ፊደል ከቆጠሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ጄኔራል ጃገማ ለአገራቸው ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ከንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና ከተለያዩ አገሮች ኒሻንና ሜዳዮችን ተሸልመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የአንገት ኒሻን፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጦር ሜዳ ጀግና ሜዳይ ባለ ሁለት ዘንባባ፣ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን ከአገር ውስጥ ሲጠቀሱ፣ ከውጭ አገሮችም ከእንግሊዝ፣ ከዩጎዝላቪያና ከላይቤሪያ የተለያዩ ኒሻኖችን አግኝተዋል፡፡

ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሕክምና ሲከታተሉ የቆዩት ጄኔራል ጃገማ በተወለዱ በ96 ዓመታቸው ዓርብ መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በወታደራዊ ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ ለክብራቸውም 21 ጊዜ ሲተኮስ አርበኞችና ወጣት ከያንያን ሽለላና ቀረርት ፉከራም አሰምተዋል፡፡

ጄኔራል ጃገማ የአንድ ወንድ ልጅና የአምስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
Jemal Abdulaziz

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Times Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Times Online:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share