Akiya Media

Akiya Media Akiya Media አኪያ ሚዲያ welcome to our YouTube Channel Subscribe now and gat more benefits.

23/09/2025

ምናየው ፎቶ የእውነት ጋብቻ ከሆነ እና ምንትላለህ? ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ

ምላሼ ሚከተለው ነው

እኔ የታየኝ ጋብቻው ሳይሆን የሙሽሪት ፊት እና እጅ አለመገናኘት ነው

እናንተ ግን የታያችሁን የተሰማችሁን የመግለፅ መብታችሁ የተጠበቀ ነው።

የመከላከያ ዩኒፎርም ለግል ጥቅም? 🚨በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ራሱን "ማስተር ጸጋዬ መንገሻ" ብሎ የሚጠራው ግለሰብ፣ የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ ለብሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክር...
23/09/2025

የመከላከያ ዩኒፎርም ለግል ጥቅም? 🚨

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ራሱን "ማስተር ጸጋዬ መንገሻ" ብሎ የሚጠራው ግለሰብ፣ የመከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብስ ለብሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበራዊ ሚዲያ አገልጋይ የሆነውን አቶ ነጋሽ በዳዳን በቪዲዮ ማስፈራራቱ ተሰማ።

ግለሰቡ በቪዲዮው ላይ "ፈንጅ ወረዳ ላይ ነህ"፣ "በአይናችን ስር ነህ" እና "እረፍ" የሚሉ የማስጠንቀቂያና የዛቻ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ተሰምቷል።

ይህ ቪዲዮ ከተለቀቀ ከጥቂት ሰዓታት በኋላም ከማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አጥፍቶታል።

ይህ ድርጊት የመንግስትን የፀጥታ አካል ዩኒፎርም ለግል ሃይማኖታዊ ጥቅም በማዋል በሌላው ወገን ላይ ማስፈራሪያ መተላለፉን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የደንብ ልብሱን ለዚህ ዓይነት ድርጊት የተጠቀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ እንዲያቀርብ ጥያቄ ቀርቧል።

ህግ የበላይነት ይከበር።

23/09/2025

ተደጋጋሚ የሚደርሱን መልዕክቶች ፖስፖርት ክፍያ ከፈፀምን ከአመት በፊት ቢሆንም እሰካሁን ምንም መልስ አላገኘንም የሚሉ በርካቶች ናቸው !!!

22/09/2025

"ፋይሉ ተዘግቷል" ሲል ሰማሁት I think ህግ ነው ተምሮ የተመረቀው መሰለኝ☹️

20/09/2025
ይህ ሃውልት የት አካባቢ ነበረ ?   Akiya Media Meta Newsroom Seifu fantahun on EBS tv show Commercial Bank of Ethiopia
19/09/2025

ይህ ሃውልት የት አካባቢ ነበረ ?

Akiya Media Meta Newsroom Seifu fantahun on EBS tv show Commercial Bank of Ethiopia

ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተሾሙ የብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ዶ/ር እዮብ ተካልኝ  በአገሪቱ ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋም መሪነት እንዲያገለግሉ ተሾመዋል።በተጨማሪ ወ/ሮ እናታለም መለስ ደግሞ የመንግሥ...
19/09/2025

ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተሾሙ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በአገሪቱ ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋም መሪነት እንዲያገለግሉ ተሾመዋል።

በተጨማሪ ወ/ሮ እናታለም መለስ ደግሞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ በኃላፊነት ማዕረግ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትን እንዲመሩ ተመድበዋል።

ህይወት እንደዚህ ናት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ከዚህ ደሰታ ወደዚህ አደጋ !በህይወታችን ለሰዎች መልካም ማደረግ መልካም ማሰብ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው እንደራስ መወደድ ለነገ ጉ...
18/09/2025

ህይወት እንደዚህ ናት

በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ከዚህ ደሰታ ወደዚህ አደጋ !

በህይወታችን ለሰዎች መልካም ማደረግ መልካም ማሰብ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው እንደራስ መወደድ ለነገ ጉዛችን ስንቅ ነው ። አለም ውሸታም ናት ቢልጭልጩን አሳይታን መንገድ የምታሰተን !!!

ወንድማችን ነብስህ ይማርልን ወጥቶ ከመቅረት ይጠብቀን 🙏

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ መቀመጧን ጥናት አመለከተኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረ...
17/09/2025

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋት ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ መቀመጧን ጥናት አመለከተ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በተደጋጋሚ በመዝጋትና የኢንተርኔትን ነጸነት በመገደብ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በብሉምስበሪ አሳታሚ ላይ የታተመ የጥናት መጽሐፍ አመላከተ።

“የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ” በሚል ርእስ በፊሊሽያ አንቶኒዮ እና ቶኒ ሮበርትስ የተጠናውና መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ባደረገው ብሉምስበሪ አሳታሚ ድርጅት ላይ በመጸሐፍ መልክ ታትሞ የወጣው ጥናት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 በአህጉረ አፍሪካ በሀገራት የተፈጸመውን የኢንተርኔት መዘጋት ገምግሟል።

በዚህም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2024 ባሉት በለፉት ዘጠኝ ዓመታት 193 የኢንተርኔት መዘጋት በአፍሪካ አህጉር መመዝገቡን ገልጿል።

በተጠቀሱት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ በተፈጸሙ የኢንተርኔት መዘጋት ድግግሞሽ መጠኖች ሀገራትን በደረጃ ያስቀመጠው ጥናቱ ኢትዮጵያን በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ሰላሳ ጊዜ ኢንትርኔት የዘጋች በሚል ከ55ቱ የአፍሪካ ሀገራት በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል።

Akiya Media

16/09/2025

በinbox አሁን ሰዓቱ 7:55 ከለሊቱ ነው !
ወይ ፖለቲካ በዚህ ሰዓት ለሰልፍ በመኪና ጥሩንባ እና በእድረተኛ ጥሩንባ ውጡ !!

እሁድ ጠዋት በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የህዳሴ ግድብ ምርቃት የሰልፍ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እና ትርዒት ለማቅረብ በዋዜማው ሲለማመዱ የነበሩ ታዳጊዎች የመድረክ መደርመስ አደጋ እንዳጋጠ...
16/09/2025

እሁድ ጠዋት በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የህዳሴ ግድብ ምርቃት የሰልፍ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እና ትርዒት ለማቅረብ በዋዜማው ሲለማመዱ የነበሩ ታዳጊዎች የመድረክ መደርመስ አደጋ እንዳጋጠማቸው መረጃ ማቅረባችን ይታወሳል።

አደጋው ከማጋጠሙ ጥቂት ቀደም ብሎ የዚህ ከእንጨት የተሰራ መድረክ ምስልን የሚያሳይ ፎቶ የደረሰን ሲሆን እስከ 18 ደረጃ ከፍ ብሎ የተሰራ መሆኑ ታውቋል። ምስሉን ይመልከቱ:።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በጥቁር አንበሳ ከሚሰሩ ዶክተሮች ለሚድያችን የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው በአደጋው የተጎዱ 80 ታዳጊዎች ወደ ተቋሙ ለህክምና በአምቡላንስ መወሰዳቸው ታውቋል።

"ይህ እኛ ጋር ያለው ብቻ ነው፣ 29 የሚሆኑት የአጥንት መሰንጠቅ ያጋጠማቸው ናቸው። ሌሎቹ ወደ አለርት ሆስፒታል እና ሌሎች የህክምና ተቋማት ሪፈር ተደርገዋል" በማለት አንድ የሆስፒታል ምንጫችን ጠቁመዋል።

በዘውዲቱ ሆስፒታልም ቁጥራቸው ከፍ ያለ ጉዳተኞች መወሰዳቸው የታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ በዕለቱ 240 ታዳጊዎች የተለያየ ደረጃ ያለው ጉዳት እንዳጋጠማቸው እና ህይወታቸው ያለፉም እንዳሉ ታውቋል።

"ይህ ብቻ ሳይሆን አደጋው እንደደረሰ ሰምተው ቅዳሜ ምሽት በየሆስፒታሉ ሲሯሯጡ የነበሩ ቤተሰቦች ከፍተኛ ማዋከብ ደርሶብናል፣ በፀጥታ አካላት ድብደባ የደረሰባቸውም ነበሩ" በማለት በዕለቱ ቤተሰብ ሲያፈላልግ የነበረ አንድ ግለሰብ ተናግሯል።

"ገና በለጋ እድሜያቸው ጎበዝ ጎበዝ ተማሪዎችን ከየትምህርት ቤታቸው በመምረጥ መንግስት ለጎበዝ ተማሪዎች ያዘጋጀው የጉብኝት ፕሮግራም አለ፣ ለሶስት ቀን ስለምትቆዩ ብርድ ልብስ እና አንሶላ ይዛችሁ ኑ ተብለው ስድስት ኪሎ ካምፓስ አስገብተዋቸው ነበር" ብለው ለሚድያችን ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የመረጃ ምንጫችን ናቸው።

ምንጩ አክለውም "ከዛ አምስት ቀን ትቆያላችሁ፣ ቀጥሎ አስር ቀን ትቆያላችሁ፣ ብሎም በቃ ጳጉሜ ትሄዳላችሁ ካሏቸው በኋላ መውጣት አትችሉም በማለት ለአባይ ግድብ ምርቃት ትርዒት ታቀርባላችሁ ብለው ስልጠና አስጀምረዋቸው ነበር" ይላሉ።

ለአዲስ ዓመት በዓል ጭምር ታዳጊዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሳይሄዱ ተነጥለው ማሳለፋቸው የታወቀ ሲሆን ላለፉት 15 ቀናት መስቀል አደባባይ ላይ በእንጨት እስከ 18 ደረጃ በተሰራ መድረክ ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸው ታውቋል።

በዚህ አደጋ ዙርያ እስካሁን በመንግስት አካላትም ሆነ ሚድያዎቻቸው የተባለ ነገር የለም።

Akiya Media Meta Newsroom Ethiopian Airlines Seifu fantahun on EBS tv show

Address


20036

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akiya Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share