Mr. Teddy

Mr. Teddy Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mr. Teddy, South, .
(2)

‎Arsenal FC Fan Page in Ethiopia
⚪ ‎🔴 ⚽ 🇪🇹 ⚽ 🔴⚪
‎
‎ትኩስ ፣ ፈጣን እና ታማኝ የአርሰናል መረጃዎች!
‎ዜናዎች | ዝውውሮች | ትንታኔዎች | ቀልዶች 😁
‎
‎👇 Follow በማድረግ የቤታችን አባል ይሁኑ!

‎🔴⚪"Once a Gunner, always a Gunner" 🔴⚪
‎

እንደ እኔ የአልቫረዝ ዝውውር የሚሳካልን ከሆነ የዞሊስ ተጠባባቂ ለመሆን ማርቲነሊ ቆይቶ ሃቫርተዝ እና ጅሱሰ ደግሞ ክለቡን ቢለቁ ደስ ይለኝ ነበር ግን   የለም  የማርቲነሊ ጉዳይ አብቅቶለታ...
26/08/2026

እንደ እኔ የአልቫረዝ ዝውውር የሚሳካልን ከሆነ የዞሊስ ተጠባባቂ ለመሆን ማርቲነሊ ቆይቶ ሃቫርተዝ እና ጅሱሰ ደግሞ ክለቡን ቢለቁ ደስ ይለኝ ነበር ግን የለም የማርቲነሊ ጉዳይ አብቅቶለታል 😭

‎እውነቱን እንነጋገር ከተባለ 130 ማሊዮን ፓውንድ ከአልቫረዝ ይልቅ ለክርስቶስ ዞሊስ ነው የሚገባው!‎‎የዘመኑ የዝውውር ገበያ በስም እና በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በእውነተኛ የሜዳ ላይ ብቃት የ...
26/08/2026

‎እውነቱን እንነጋገር ከተባለ 130 ማሊዮን ፓውንድ ከአልቫረዝ ይልቅ ለክርስቶስ ዞሊስ ነው የሚገባው!
‎
‎የዘመኑ የዝውውር ገበያ በስም እና በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በእውነተኛ የሜዳ ላይ ብቃት የሚመዘን ከሆነ፣ እንደ ክሪስቶስ ዞሊስ ያሉ ድንቅ አጥቂዎች ለእንደዚህ አይነት ግዙፍ የገንዘብ ተመን ቀዳሚ ተገቢዎች ናቸው።
‎
‎እውነቱን ተናግሮ በመሸበት ማደር ይሻለኛል ብየ ነው 🙏

‎ጁሊያን አልቫሬዝ  በሆድ ህመም አሳብቦ ዛሬ ጠዋት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ልምምድ አልሰራም ❌‎‎‎
26/08/2026

‎ጁሊያን አልቫሬዝ በሆድ ህመም አሳብቦ ዛሬ ጠዋት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ልምምድ አልሰራም ❌
‎
‎
‎

ክርስቶስ ዞሊስ  ሊጉን እየተለማመደ አደገኛ እና አለም ላይ የሚፈለገ  ተጽዕኖ ፈጣሪ  ተጫዋች ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ሃሳባቸውን እያጋሩት ይገኛሉ።
26/08/2026

ክርስቶስ ዞሊስ ሊጉን እየተለማመደ አደገኛ እና አለም ላይ የሚፈለገ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተጫዋች ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ሃሳባቸውን እያጋሩት ይገኛሉ።

‎ሪዮ ፈርዲናንድ አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን እንደሚያስጠብቅ ሙሉ እምነት እንዳለው ገለጸ።‎‎የቀድሞው የካራባኦ ጽዋ እና የፕሪሚየር ሊግ አፈ ታሪክ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ፣ መድፈኞቹ...
26/08/2026

‎ሪዮ ፈርዲናንድ አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫውን እንደሚያስጠብቅ ሙሉ እምነት እንዳለው ገለጸ።
‎
‎የቀድሞው የካራባኦ ጽዋ እና የፕሪሚየር ሊግ አፈ ታሪክ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ፣ መድፈኞቹ በያዘው የውድድር ዘመን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ደግመው ስለማንሳታቸው ምንም አይነት ጥርጥር እንደሌለው ተናገረ።
‎
‎ፈርዲናንድ ቡድኑ ያሳየውን ድንቅ ብቃት አድንቆ እንደገለጸው፤ አርሰናል በሜዳ ላይ ያለው ጥንካሬ እና ስልታዊ ብስለት ለተፎካካሪዎቹ እጅግ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል። "ከአርሰናል የጠበቅኩት ነገር ነበር። ጠንካራ፣ ለመግጠም የሚከብዱ፣ የተፎካካሪ እንቅስቃሴ የሚያስቆሙ እና ከተፎካካሪዎች የሚሰሩ ስህተቶችን በመጠቀም የሚቀጡ ነበሩ" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
‎
‎"እንደ ሻምፒዮን ነው የተጫወቱት በዚህ የውድድር ዘመን አርሰናልን መፈታተን የሚችል ቡድን አይታየኝም።
ብቸኛው መረጋጋት ያለው ቡድን እነሱ ናቸው፤ ከእነሱ ውጪ ያሉት በሙሉ ትልልቅ ለውጦችን አድርገዋል" ግን እነሱን የሚያክል የለም በማለት የሰሜን ለንደኑን ክለብ የዋንጫ እድል አጠናክሯል።
‎
‎ Sun football
‎

‎ቤን ዋይት ወይስ ዩሪየን ቲምበር?" ‎የአርሰናል ቀኝ መስመር ፍልሚያ‎‎በአርሰናል ደጋፊዎች ዘንድ "ሙሉ ጤንነት ላይ ያለ ቤን ዋይት በማጥቃትም ሆነ በመከላከል ከዩሪየን ቲምበር ይበልጣል" ...
26/08/2026

‎ቤን ዋይት ወይስ ዩሪየን ቲምበር?"
‎የአርሰናል ቀኝ መስመር ፍልሚያ
‎
‎በአርሰናል ደጋፊዎች ዘንድ "ሙሉ ጤንነት ላይ ያለ ቤን ዋይት በማጥቃትም ሆነ በመከላከል ከዩሪየን ቲምበር ይበልጣል" የሚለው አስተያየት ትልቅ ክርክር አስነስቷል። ሁለቱ ተጫዋቾች ለአርቴታ ስብስብ ያላቸው ንፅፅራዊ ብቃት እንደሚከተለው ይቀርባል።
‎
‎የቤን ዋይት ጥንካሬዎች
‎
‎የጥምረት ብቃት፦ ከቡካዮ ሳካ ጋር ያለው ጥልቅ መግባባት እና የሚያደርጋቸው የማጥቃት ሩጫዎች ለአርሰናል ዋነኛ የግብ እድል መፍጠሪያ ናቸው።
‎
‎ልምድ እና ዘውታሪነት፦ ቦታን ጠብቆ በመከላከል እና ቋሚ ወጥ ብቃት በማሳየት ረገድ አስተማማኝ ነው።
‎
‎የዩሪየን ቲምበር ጥንካሬዎች
‎
‎ቴክኒክ እና ኳስ መያዝ፦ ከኋላ ተነስቶ ኳስ ወደ ፊት በመግፋት እና የመሃል ክፍሉን በማጠናከር ረገድ ልዩ ብቃት አለው።
‎
‎አንድ ለአንድ መከላከል፦ ከአጥቂዎች ጋር በሚደረጉ የፍጥነት እና የአካላዊ ፍልሚያዎች ላይ ፈጣንና አጥቂ ነው።
‎
‎ማጠቃለያ
‎ቤን ዋይት በስ Tactically የተረጋጋ እና በማጥቃት ረገድ ከሳካ ጋር የተሟላ ጥምረት ያለው ሲሆን፣ ቲምበር ደግሞ በቴክኒክ ብቃቱ እና በአንድ ለአንድ ፍልሚያው ይበልጣል። የሁለቱ ጤናማ ውድድር ግን የአርሰናልን ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።

‎የአስቶንቪላ እና የአርሰናል ጨዋታ ዋና ዳኛ ታወቀ‎!!‎በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ  መጭው ሰኞ ማታ 4:00 ሰዓት በአስቶንቪላ እና በአርሰናል መካከል ለሚደረገው ታላቅ...
26/08/2026

‎የአስቶንቪላ እና የአርሰናል ጨዋታ ዋና ዳኛ ታወቀ
‎!!
‎በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ መጭው ሰኞ ማታ 4:00 ሰዓት በአስቶንቪላ እና በአርሰናል መካከል ለሚደረገው ታላቅ ፍልሚያ ዳኛ Jarred Gillett በዋና ዳኝነት እንዲያገለግሉ መመደባቸው ተረጋገጠ።
‎
‎በተጨማሪም የVAR በመሆን ጨዋታውን በቴክኖሎጂ የሚመሩት James Bell መሆናቸው ታውቋል።
‎
‎ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉት ይህ ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘ ሲሆን፣ የዳኞች ምደባም የእግር ኳስ አፍቃሪያን አበይት የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።
‎

እነዚህ ሰዎች በሁሉም ነገር እንዳይጎዱ በማሰብ የPFA  ሽልማት የሚገባው ለራይስ ነበር  ግን ብሩኖ እንዲያሸንፍ አስደርገናል።     እንኳን ደስ አላችሁ የብሩኖ ቤተሰቦች  🙏
25/08/2026

እነዚህ ሰዎች በሁሉም ነገር እንዳይጎዱ በማሰብ የPFA ሽልማት የሚገባው ለራይስ ነበር ግን ብሩኖ እንዲያሸንፍ አስደርገናል።
እንኳን ደስ አላችሁ የብሩኖ ቤተሰቦች 🙏

UPDATE ቀን ላይ ማርቲኔሊ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ  ወደ ሳዑዲ አረቢያ  ሪያድ ከተማ በሰላም እንደደረሰ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ  ምንጩ ሀሰተኛ ነው ለዚህ ይቅርታ እንጠይቃለን ።ተጫዋቹ ዛሬ...
25/08/2026

UPDATE
ቀን ላይ ማርቲኔሊ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በሰላም እንደደረሰ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ምንጩ ሀሰተኛ ነው ለዚህ ይቅርታ እንጠይቃለን ።

ተጫዋቹ ዛሬ ከቡድኑ ጋር ሙሉ ልምምድ ሰርቶ የዋሌ ቢሆንም ወደ አል ሂላል የሚያደረገው ዝውውር ግን እጅግ በጣም መቃረቡን Fabrizio Romanoን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ጋዜጠኞች አሁን ላይ እየዘገቡት ይገኛሉ።

ይቅናህ ትንሹ ጋቢ ❤

ብሩኖ ፈርናንዴዝ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማንን መረጥክ ተብሎ ተጠይቆአንድ የአርሰናል ተጫዋች ስሙን ግን አልናገረም ብሏል።ማንን አስቦ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ?
25/08/2026

ብሩኖ ፈርናንዴዝ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማንን መረጥክ ተብሎ ተጠይቆ
አንድ የአርሰናል ተጫዋች ስሙን ግን አልናገረም ብሏል።

ማንን አስቦ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ?

Address

South

Telephone

+251928401799

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mr. Teddy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed media company?

Share