Press Fact Check/የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ

Press Fact Check/የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Press Fact Check/የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ, Media/News Company, Addis Ababa.

"ማንኛውም ዜጋ ዐሻራ ሳይሰጥ ፓስፖርት ማግኘት አይችልም"- የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት+++++++++++++ | በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ዐሻራ ሳይሰጡ ፓስፖርት እየተሰጠ ነ...
01/11/2025

"ማንኛውም ዜጋ ዐሻራ ሳይሰጥ ፓስፖርት ማግኘት አይችልም"
- የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
+++++++++++++

| በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ዐሻራ ሳይሰጡ ፓስፖርት እየተሰጠ ነው በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ፡፡

ተቋሙ ያለዐሻራ ፓስፖርት እየሰጠ ነው መባሉንም አስተባብሏል፡፡

https://gateway.press.et/am-digital-content/share/am-stories/4xv5pr01za7wm06hy33cbswxw

#ፖስፖርት #ሐሰተኛመረጃ FDRE Immigration and Citizenship Service

 #ለጥንቃቄ‼️ | ካናዳን ጨምሮ ወደየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ህጋዊ ስምሪት እለመኖሩን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እናደርግዎታለን፣ ገንዘብ ላኩ በሚ...
19/10/2025

#ለጥንቃቄ‼️

| ካናዳን ጨምሮ ወደየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ህጋዊ ስምሪት እለመኖሩን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እናደርግዎታለን፣ ገንዘብ ላኩ በሚሉ አጭበርባሪዎች እንዳይታለሉ ሲልም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አሳስቧል። ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ህጋዊ መንገዶችን ብቻ እንዲጠቀሙ አመላክቷል።

📌 ይልቁንም መረጃውን በአቅራቢያዎ ለሚገኙ መዋቅሮቻችንና ለህግ አስከባሪ አካላት ያሳውቁ።

📌 ከደወሉም ሆነ መልዕክት ከላኩ እነሱ አጭበርባሪዎች ናቸውና ምንም አይነት ምላሽ አይስጡ።

#መረጃ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል +++++++++++++++   ¶ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ...
13/09/2025

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል
+++++++++++++++

¶ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአርባምንጭ ከተማም ሆነ ከዙሪያው ለሚመጡ ታካሚዎች የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አብደላ ከማል (ዶ/ር) አስታወቁ።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆስፒታሉ እስካሁን ምንም አይነት አገልግሎት አየሰጠ አይደለም በሚል ከተሰራጨው መረጃ ጋር ተያያዞ የፕሬሰ መረጃ ማጣሪያ ያናገራናቸው የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አብደላ ከማል (ዶ/ር)፤ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው። ሆስቲታሉ ከተመረቀ አንድ አመት የሞላው ቢሆንም የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት በጥሩ ሁኔታ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሆስፒታሉ ሙሉ አገልግሎት ያልጀመረው የቀዶጥገና መስጫ፣ የጽኑ ህክምና ክፍሎችና ተኝቶ ህክምና ክፍሎች የማስተካከያ ስራዎችን እየሰራን ነው ያሉቱ ፕሬዚዳንቱ አብዛኞቹን ተጠናቀዋል። የተወሰኑ ስራዎችን እንደጨረስን ሙሉ አገልግሎት የምንጀምር ይሆናል ብለዋል፡፡

ሆስፒታሉ በቀዶ ሕክምና፣ በውስጥ ደዌ፣ በማህጸንና ጽንስ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል። በክልሉና በአጎራባች ክልሎች ለሚገኙ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች አገልግሎት መስጠት የሚያሰችል አቅም እንዳለው ተገልጿል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል።

በገነት ኃይለማሪያም

#መረጃ

ዓባይ ግድብ ተጠናቋል ++++++++  ¶ ኢትዮጵያ የዓባይ ግድብን ለመገደብ የመሠረት ድንጋይ ካስቀመጠችበት ዕለት ጀምሮ በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች። ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎችን ተሻግራ የዓ...
04/09/2025

ዓባይ ግድብ ተጠናቋል
++++++++

¶ ኢትዮጵያ የዓባይ ግድብን ለመገደብ የመሠረት ድንጋይ ካስቀመጠችበት ዕለት ጀምሮ በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች።

ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎችን ተሻግራ የዓባይ ግድብን ሙሉ ለሙሉ አጠናቃለች፤ ለምረቃውም ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ይሁን እንጂ ሲጂቲኤን አፍሪካ ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ በሰራው ዘገባ የተጠቀመው ፎቶግራፍ ትክክለኛውን የዓባይ ግድብ አሁናዊ ገፅታን የሚያሳይ ፎቶ አይደለም።

ከዘገባው ጋር የተለቀቀው ፎቶ በግንባታ ሂደት የነበረ ፎቶ እንጂ አሁን ላይ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የዓባይ ግድብ የተጠናቀቀውን የሚያሳይ ምስል አለመሆኑን የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ ተመልክቷል።

የህዳሴ ግድብ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። የግድቡን አሁናዊ ገጽታ የሚያሳየውን ፎቶ ከታች ይመልከቱ።

በገነት ኃይለማሪያም

#መረጃ

ከሦስት ዓመት በፊት የተጋራን ምሰል ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰራ አስመስሎ የቀረበው ምስል የተሳሳተ ነው+++++++++++++++  ¶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሦስት ዓመት በፊት የተጋራን የሌላ ሀገ...
18/08/2025

ከሦስት ዓመት በፊት የተጋራን ምሰል ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰራ አስመስሎ የቀረበው ምስል የተሳሳተ ነው
+++++++++++++++

¶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሦስት ዓመት በፊት የተጋራን የሌላ ሀገር ፎቶና ምሰል በመውሰድ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰራ አስመስለው ሲያቀርቡት ተስተውሏል።

ይህ ምስል በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት መብራቶች ያሳያል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ ነው።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ የሚገኘው ምስል የአዲስ አበባ ከተማን መብራቶች ያሳያል በሚል እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ ነው።

ይህ ምስል ከ3 ዓመታት በፊት በሌላ አገር የተቀረፀ መሆን የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ ጉልግል ኢሜጀ ሪቨርስ እና ጉግል ኢሜጅሌንስን በመጠቀም በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ምስል ሀሰተኛ ምሰል መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ ምስል ከዚህ በፊት በሌሎች አከባቢዎች ጥቅም ላይ የዋለ እንጂ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነው አለመሆኑን የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ ጎግል ሌንስ ተጠቅሞ ባደረገው የማጣራት ስራ አረጋግጧል።

#መረጃ

ህጋዊ ሥራ ስምሪት የሚሰጥባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው⁉️ ++++++++++++ | የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ህጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለመዘርጋት ባደረገው ጥረት ከዚ...
15/08/2025

ህጋዊ ሥራ ስምሪት የሚሰጥባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው⁉️
++++++++++++

| የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ህጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለመዘርጋት ባደረገው ጥረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሀገራት ጋር ሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

👉 ሳዑዲ አረቢያ🇸🇦
👉 የተባበሩት አረብ ኤሚሬት🇦🇪
👉 ዮርዳኖስ🇯🇴
👉 ሊባኖስ🇱🇧
👉 ኳታር🇶🇦
👉 ኩዌት 🇰🇼

ህጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ለማግኘት፤ በየትኛውም ሀገር ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን በመጀመሪያ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት lmis.gov.et በመመዝገብና የሚሰጠውን ስልጠና በመውሰድና ብቃትዎን በምዘና ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።

የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ ሲልም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በነፃነት አለሙ

#ጥንቃቄ

በተያዘው በጀት አመት ኬንያ፣ ጅቡቲና ሶማሌላንድን በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት ታቅዷል++++++++++++++++  ¶ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ባረኦ ሀሰን መቀመጫው...
13/08/2025

በተያዘው በጀት አመት ኬንያ፣ ጅቡቲና ሶማሌላንድን በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት ታቅዷል
++++++++++++++++

¶ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ባረኦ ሀሰን መቀመጫውን ኬኒያ ናይሮቢ ያደረገው አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች ባለቤትና ማኔጅመንት አባላት ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

ከናይሮቢ- አዲስአበባ በአውቶብስ የህዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእውቅናው ውጪ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

ሚኒስትር ዴኤታው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በተያዘው በጀት አመት ኬንያ፣ ጅቡቲና ሶማሌላንድ በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት ማቀዱን ገልጸዋል። የመንግስትና ግሉን ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ያለውን ዝግጁነት በውይይቱ አረጋግጠዋል።

በመሆኑም እንደሚኒስቴር መስሪያቤት በሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ የህግ ማዕቀፎችን ለማዘጋጀት በትኩረት እንደሚሰራና በድርጅቱ በኩል አስፈላጊውን ሂደት አሟልተው እንዲመጡ ከስምምነት ተደርሷል።

የአቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች ባለቤት አቶ ሚካኤል ጀምስ በበኩላቸው፣ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ለማመላለስ ፍላጎቱን እንዳለው ገልፀው አገልግሎቱን የሚሰጡ አውቶቢሶችን ማሰባሰብ ጀምሯል።

ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በቅንጅት ለመስራት ፍላጎት ማሳየቱን የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስሩ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት መግለጹን የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ ተመልክታለች።

#ኢፕድ #መረጃማጣሪያ

በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ ይጠንቀቁ ✍️ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አልተሰጠም ++++++++++++++++  ...
13/08/2025

በሀሰተኛ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ማስታወቂያዎች እንዳይታለሉ ይጠንቀቁ

✍️ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አልተሰጠም
++++++++++++++++

|ለህጋዊ የሥራ ስምሪት የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተገባባቸው የተለያዩ ሀገራት ለሥራ እንልካለን የሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተዘዋወሩ ይገኛል፡፡

ይህ ገንዘብ ከማጭበርበር ባለፈ ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የጉልበት ብዝበዛ፣ ለከፋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለፕሬስ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛው አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን እየገለጽን ዜጎቻችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ እናሳስባለን ብሏል።

ኢትዮጵያ ካናዳን ጨምሮ ከየትኛው የአውሮፓ ሀገር ጋር የሁለትዮሽ የሥራ ስምሪት ስምምነት የላትም ሲልም ገልጿል።

ለየትኛውም የጉዞ ወኪል ወይም ኤጀንሲ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት ዜጎችን ለሥራ እንዲያሰማራ የሰጠው ውክልናም ሆነ ፍቃድ እንደሌለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት አስታውቋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

በነፃነት አለሙ

#ጥንቃቄ

08/08/2025

የውጭ ምንዛሬ ግኝት ይቀንሳል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አሰታወቀ
++++++++++++++
(ኢ ፕ ድ )

|የውጭ ምንዛሬ ሪፎርምን በሚመለከት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች አሳሳችና ሀሰተኛ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። እነዚህ መረጃዎች በህብረተሰቡና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ የተሳሳቱ ዕይታዎችን ፈጥረዋል።

ከሪፎርሙ የመጀመሪያ አመት በኋላ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ይቀንሳል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛና መሰረተ ቢስ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከሰጡት ማብራሪያ የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ አረጋግጣለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በሰጡት ማብራሪያ፣ የማክሮ ኢኮኖሚም ሆነ የውጭ ምንዛሪ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። ህብረተሰቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን ጠብቆ መደበኛውን የንግድ እንቅስቃሴ ያለምንም ስጋት እንዲያካሂድ አሳስበዋል።

የአለም የገንዘብ ድርጅት ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ያለው ዕይታ እጅግ አዎንታዊ፤በሁሉም የማክሮ አውዶች የተገኘው ውጤት ከግምት በላይ እንደሆነና የሚደነቅ ስለመሆኑ ከድርጅቱ ድህረገጽ ማንብብና መረዳት ይቻላል።

ተቋሙ በሚያውጣቸው ዘገባዎች ሀገራት ሊያጋጥማቸው ስለሚችለው ስጋት አስተያየት ይሰጣል። እኛም ሆን ሌሎች ሀገራት የሚያጋጥማቸው ስጋቶች መኖራቸው ይታወቃል። የተሰጠው አስተያየት የተለመደና ለእኛ የተለየ አይደለም።

የአለም የገንዘብ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ሪፎርም አልነቀፈም፤ በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ላይም ችግር መኖሩን አላነሳም። ይልቁን የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን በ4 ነጥብ 5 በመቶ ከዋጋው በታች እንደሆነ አሳይቷል።

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና የግል ካፒታል ፍሰት ጨምሯል። ከልማት አጋሮች የሚገኘው ድጋፍ ቀጥሏል። የብሔራዊ ባንክም ሆነ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግኝት እየተሸሻለ እንደሚሄድ ይጠበቃል።

ባንኮች የንግዱን ማህበረሰብና የግለሰቦችን የውጭ ምንዛሬ ፍልጎት እያሟሉ ሲሆን ብሔራዊ ባንክም ይህን ጥረት መደገፉን ይቀጥላል። የንግድ ማህበረሰብ ኢ-መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ትቶ በመደበኛ የውጭ ምንዛሬ መጠቀም እንዳለበት አሳስበዋል።

ኢኮኖሚው በፍጥነት እያደገ፤ የዋጋ ግሽበቱ እየረገበ፤ የፊሲካል ሁኔታው እየተሸሻለ፤ የምንዛሬ ፍሰት እየጨመረና ለግሉ ዘርፍ አቅርቦት ከፍ እያለ መምጣቱ ሪፎርሙ በትክክለኛው ጎዳና ላይ እንደምንገኝ አመላካች ነው ተብሏል።

በገነት ኃይለማሪያም

#መረጃማጣሪያ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Press Fact Check/የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Press Fact Check/የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ:

Share