ወደ ግጥም WEDE GITIM

  • Home
  • ወደ ግጥም WEDE GITIM

ወደ ግጥም WEDE GITIM Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወደ ግጥም WEDE GITIM, Digital creator, .

02/10/2024

ቡና
ለግጥም
ብዙ አስተዋፅዖ አበርክቷል!

  ( #ግርባብ) እየመጣ ነው። ለመስጠት የልቡ መዳፍ የተዘረጋለት ፡ ልቦናው በብርሐን የነጋለት ፡ ከቅጠል ከሣር ፡ ከተድላ ከአሳር ፡ በእኩል የሚነጋገር . . . ያ ደግ ሰው...ያ ደግ ሰ...
26/02/2024

( #ግርባብ) እየመጣ ነው።
ለመስጠት የልቡ መዳፍ የተዘረጋለት ፡ ልቦናው በብርሐን የነጋለት ፡ ከቅጠል ከሣር ፡ ከተድላ ከአሳር ፡ በእኩል የሚነጋገር . . . ያ ደግ ሰው...
ያ ደግ ሰው . . . ከሸክላ ገላ ላይ የሰውነትን ወዝ የሚመዝ ፡ ከነፋስ አካል ላይ የሰውነትን ኮቴ የሚመረምር ፡ ልብን በልቦና ፡ ልቦናን በልብ የሚያበጥር ፡ ሰው እና ጊዜን የሚያመሳጥር ፡ ያ ደግ ሰው እየመጣ ነው።
መለኪያ ተከትሎ ፡ በወል ዱካ ተግተልትሎ ፡ ሳይሆን . . . ከተባለው ፡ ከተመነዠከው ፡ ሳይሆን . . . ከጠራው ከምንጩ ቀድቶ ፡ የኅላዌን ዜማ ሊያንቆረቁር ፡ የውስጠትን ቅኝት ሊያንጎራጉር ፡ ከዝዑዝ አስመስሎ ከራስ ጋራ ሊያነጋግር ፡ እየመጣነው። ያ ደግ ሰው . . .
በቃላት ጠረን ፡ በፈገግታ መጠን ፡ በሰውነት ተመን ፡ በትህትና መጠን ፡ ስለማውቀው ... ለዓመታት ስለምናፍቀው ፡ ያ ደግ ሰው የፊደል ካቴውን በመስማቴ፡ የቀለም ጠረኑን በቅርብ ርቀት በማሽተቴ ፡ የደስ ደስ ልቤ ይፈነጥዝ ይዟል ።
ሆይ ፡ ቶሎ ና . . .
Fksh Ayelgn [[ ]]

  (2)
21/02/2024

(2)

«   ፤» «ሞት ለሟች ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» ሊቁ ቅዱስ ያሬድሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ"...
30/01/2024

«
፤»

«ሞት ለሟች ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ

"ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ምጡቀ ፤
በአእባነ ባሕርይ ዘተነድቀ ፤
ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ፤"

እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት .. ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡
ግንቦት 1 ቀን ሊባኖስ በምትባል ቦታ በብጽዓት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎት በአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ ወልድ ሆናለች፡፡
• እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣
• በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፣
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በድንግልና
• መድኃኔዓለምን በማኀጸንዋ ጸንሳ ዘጠኝ ወር ፤
• ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመት ከሦስት ወር፣
• ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር
ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

•፨ የእመቤታችን አስደናቂ ዕረፍትና ዕርገት ፨•

እመቤታችን ጥር 21 ቀን ዕረፍቷ በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሣሥተው “ቀድሞ ልጅዋን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል፡፡ እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጅዋ ተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን? ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት። ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው 'ታውፋኒያ' የተባለው አይሁዳዊ ተመርጦ ሄዶ የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ሽንኮር ያዘ፡፡

የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጁን እን ደ ቆረጠው

የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለት እጁን ስለ ቆረጣቸው ከአልጋው ሽንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ ታውፋንያ(ባውፍልያ) በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች ፡፡

የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፅ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እና ሰማዕታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ ንጉሥ ዳዊት “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት ፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እንዳለ፡፡ /መዝ 44፡9/

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፡፡ ሐዋርያት ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማ ሥጋዋም በታላቅ ክብር ማዕረጓን ነገራቸው፡፡

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ምጡቀ፤
በአእባነ ባሕርይ ዘተነድቀ ፤
ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ፤
እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡

[ መ/ር ]

Follow WEDE GITIM ወደ ግጥም
24/12/2023

Follow WEDE GITIM ወደ ግጥም

 #ዛሬ ከ8:30 ጀምሮ - በ #ካሳንቺስ  #ፈንድቃ የጥበብና የባሕል ማዕከል
23/12/2023

#ዛሬ ከ8:30 ጀምሮ - በ #ካሳንቺስ #ፈንድቃ የጥበብና የባሕል ማዕከል

22/12/2023

(5ኛው ዝግጅት) #በካሳንቺስ #ፈንድቃ የጥበብ እና የባሕል ማዕከል 13-2016 ዓ.ም ከ8፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ( #መግቢያው #በነፃ ነው! )
#የሰከኑ ግጥሞች
ፔጃችንን እና በማድረግ ለወዳጆች #አጋሩ!
Join WEDE GITIM (ወደ ግጥም) Facebook, Tiktok, Telegram and Instagram
Seifu Worku
Ethiopia

22/12/2023

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወደ ግጥም WEDE GITIM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share