Andromeda Ethiopia

  • Home
  • Andromeda Ethiopia

Andromeda Ethiopia እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችን ፊደል የራሳችን ባህል የራሳችን ጥበብ በተፈጥሮ እግዚአብሔር ሁሉን የቸረን ነን

ይቤላ ሕጻን ለእሙ ኢትፍርሒ እም ነበልባለ እሳት ከመ ንረስ መንግሥተ ሰማያት፣ሀብሩ ሃይማኖተ ወኮኑ ሰማዕተ።ሕጻኑ እናቱን እናቴ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ የእሳቱን ነበልባል አትፍሪ ...
26/07/2025

ይቤላ ሕጻን ለእሙ ኢትፍርሒ እም ነበልባለ እሳት ከመ ንረስ መንግሥተ ሰማያት፣ሀብሩ ሃይማኖተ ወኮኑ ሰማዕተ።

ሕጻኑ እናቱን እናቴ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ የእሳቱን ነበልባል አትፍሪ አላት። በሃይማኖት ተባብረው ሰማዕት ሆኑ።

ቅዱስ ያሬድ

እንኳን አደረሳችሁ።

በረከተ ሰማዕታቱን ያድለን!

"ሥላሴን" "ቅድስት ሥላሴ" እያልን የመጥራታችን ምስጢር እንደምን ነው ቢሉ፡-አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም...
14/07/2025

"ሥላሴን" "ቅድስት ሥላሴ" እያልን የመጥራታችን ምስጢር እንደምን ነው ቢሉ፡-

አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብሎ አይጠረጠሩም፡፡

አንድም ሴት በባህሪዋ ልጅን ታስገኛለች፣ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ፡፡

አንድም ሴት አዛኝ ናት፣ለታናሹም ሆነ ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፣ ይራራሉ፣ ምህረትን ይሰጣሉ፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ”ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንጻር ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ የምህረት ወንዶች ሥላሴ" በማለት ያመሰጥራል፡፡ ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፣ ርህራሄያቸውና፣ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡

አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፣ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያቢሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም፣ አይፈቅዱም በመሆኑም “ቅድስት” ይባላሉ፡፡

አንድም ሴት የልጇን ነውር አትጸየፍም ልጄ ቆሽሿል፣ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም፣ ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይጸየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ይህንን የጽድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንጻር ቅድስት እንላቸዋለን፡፡

አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ፡፡ ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንጻር ቅድስት ይባላሉ፡፡

በዚህ ምክንያት ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን በፍቅር እንጠራለን፡፡

የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት አይለየን፡፡

telegram: https://t.me/apostolic_succession_eotc

አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ...
11/07/2025

አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም።
ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ። ይህች የንስሓ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሓም ትመራሃለች።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ሰላም ወንድሞችና እኅቶች እንደሚታወቀው ብዙ የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት በግእዝ ቋንቋ በብራና ተጽፈው ይገኛሉ እናም ብራና መጻሕፍቱ በቀላሉ ስለማይገኙ ቢገኙም ለማንበብ ስለማይመቹ ግሩፕ መሥ...
10/07/2025

ሰላም ወንድሞችና እኅቶች እንደሚታወቀው ብዙ የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት በግእዝ ቋንቋ በብራና ተጽፈው ይገኛሉ እናም ብራና መጻሕፍቱ በቀላሉ ስለማይገኙ ቢገኙም ለማንበብ ስለማይመቹ ግሩፕ መሥርተን ወደ ፒዲኤፍ (pdf) ለመቀየር እና በዚህ ሐሳብ ለመሥራት ፍላጎቱ ያላችሁ telegram ላይ በዚህ user name አናግሩኝ

አመ ፳ወ፰ ለሰኔ(፩) በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አመ ፳ወ፰ ለሰኔ በዛቲ ዕለት አዕረፈ ኣብ ቅዱስ አባ ታውዳስዮስ ሊቀ ጳጳሳት ዘሀገረ እስክንድርያ ወውእቱ እምኍልቆሙ ለአ...
05/07/2025

አመ ፳ወ፰ ለሰኔ

(፩) በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አመ ፳ወ፰ ለሰኔ በዛቲ ዕለት አዕረፈ ኣብ ቅዱስ አባ ታውዳስዮስ ሊቀ ጳጳሳት ዘሀገረ እስክንድርያ ወውእቱ እምኍልቆሙ ለአበው ሊቃነ ጳጳሳት ፴ወ፫ቱ።

1 (፩) አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ ስምንት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ የሆነው ቅዱስ አባ ቴዎዶስዮስ የእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ ።

(፪) ወዝንቱ ውእቱ ዘተሰምዩ በስሙ ታውዳስዮሳውያነ እለ ብሔረ ግብፅ።

2 (፪) በዚህም ቅዱስ በስሙ በግብጽ ምድር ውስጥ ምእመናን ቴዎዶስዮሳውያን ተብለው ተጠርተውበታል ።

✝እንኳን አደረሰን☞ወርኀ ሰኔ ቡሩክ፤ ወአመ ፳ወ፯፦✝ተዝካረ በዓለ ስቅለቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ (አምላክነ፥ ወመድኀኒነ)✝ወቅዱስ መስቀል (ዕጸ መድኀኒት)✝ቅድስት ጾመ ሐዋርያት (ንጹሐ...
04/07/2025

✝እንኳን አደረሰን

☞ወርኀ ሰኔ ቡሩክ፤ ወአመ ፳ወ፯፦

✝ተዝካረ በዓለ ስቅለቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ (አምላክነ፥ ወመድኀኒነ)
✝ወቅዱስ መስቀል (ዕጸ መድኀኒት)
✝ቅድስት ጾመ ሐዋርያት (ንጹሐን)

✝ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦

✿ሐናንያ ሐዋርያ፥ እምውስተ አርድእት ኅሩያን (መጥምቁ ለጳውሎስ)
✿አልዓዛር ነዳይ ወጻድቅ (ዘወደሶ እግዚእነ በወንጌል)
✿ቶማስ ሰማዕት ክቡር (ዘሃገረ ሰንደላት)
✿፯፻ እደው፥ ወ፱ አንስት (ማኅበራኒሁ)
✿ያዕቆብ ሊቅ ወጻድቅ (ኤጲስ ቆጶስ ዘስሩግ)
✿፳ወ፬ቱ ሰማዕታት
✿ተዝካረ ማማስ ወሲላስ

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

ምንጭ ከ
https://t.me/zikirekdusn

*"ፈተና ሲገጥመን* ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት...
03/07/2025

*"ፈተና ሲገጥመን* ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም
የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

# *ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ*
ወደ ኦሎምፒያስ መጽሐፍ

+ መጾም የከበደው ጿሚ +የአባ ሲልቫነስ ደቀ መዝሙር የነበሩት ተዓምረኛው ጻዲቁ አባ ዜኖ፥ በሲና በረሃ ይኖሩ የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው። በብሕትውናቸው፥ በታዛዥነታቸው እና በትሕትናቸው የሚ...
02/07/2025

+ መጾም የከበደው ጿሚ +

የአባ ሲልቫነስ ደቀ መዝሙር የነበሩት ተዓምረኛው ጻዲቁ አባ ዜኖ፥ በሲና በረሃ ይኖሩ የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው። በብሕትውናቸው፥ በታዛዥነታቸው እና በትሕትናቸው የሚታወቁ ሲሆኑ፥ በጌታ ስም ታላላቅ ተዓምራትን እስከማድረግ የደረሱም ነበሩ። ከእርሳቸው ትምህርት መካከል ለወቅቱ ተስማሚ የሆነውን ተርጉሜ እንዲሚከተለው አቅርቤላችኋለሁ፦

በአንዲት መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው እጅግ በጣም ከመጾሙ የተነሳ የአካባቢው ሰዎች ‘ጿሚው’ እያሉ ይጠሩት ነበር። ጻዲቁ አባ ዜኖ ስለዚህ ሰው ሰሙና ልከው አስጠሩት፤ ያም ሰው ደስ እያለው ሄደ። ጸሎት ካደረጉም በኋላ አብረው ተቀመጡ። አረጋዊው ጻዲቁ አባ ዜኖም በዝምታ ሆነው ሥራቸውን መሥራት ጀመሩ። ጿሚው ግን ከአባ ዜኖ ጋር መነጋገር ስላልቻለ መሰላቸት ጀመረ፤ ለአረጋዊውም “አባቴ፥ ልሄድ እፈልጋለሁና ይጸልዩልኝ” አላቸው። አረጋዊው አባ ዜኖም “ለምን?” ብለው ጠየቁት። ጿሚውም “ልቤ በእሳት ተያይዞ የተቃጠለ ያህል ይሰማኛል፥ ምን እንደነካኝ አላውቅም። በመንደሬ ውስጥ እያለሁ እስከ ማታ ድረስ እጾም ነበር፤ እንዲህ ያለ ነገርም ገጥሞኝ አያውቅም።” አላቸው። አረጋዊውም “በመንደርህ እያልህ ራስህን በጆሮህ በኩል [የሰዎችን ወሬ] ትመግብ ነበር። በል ሂድ፥ እስከ ዘጠነኛው ሰዓት ድረስም ጹም። የምታደርገውንም ነገር ሁሉ በስውር አድርግ።” ብለው መከሩት።

ይህ ሰው የአረጋዊውን ምክር መተግበር ጀመረ፤ እስከ ዘጠነኛው ሰዓት ድረስ መታገስም ከበደው። እርሱን የሚያውቁት ሰዎችም “ጿሚው ሰይጣን አደረበት” አሉ። እርሱም ይህንን ሄዶ ለአረጋዊው ነገራቸው። እርሳቸውም “ይህ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነው” ብለው መለሱለት።

ከ መ/ር ፍሬሰንበት
2017 ዓ.ም

01/07/2025
"ተክለሃይማኖት" ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡ አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘአብ፤ እናታቸው እግዚእ ኃርያ ይባላሉ።   ቅዱሳን ከሆኑት...
01/07/2025

"ተክለሃይማኖት" ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡

አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘአብ፤ እናታቸው እግዚእ ኃርያ ይባላሉ።

ቅዱሳን ከሆኑት ጸጋ ዘአብ እና እግዚእ ኃርያ ቅዱስ ጋብቻ አቡነ ተክለ ሐይማኖት መጋቢት 29 ተፀንሰው ታህሳስ 24 ተወለዱ።

በወላጆቻቸው የወጣላቸው ስም ፍስሐ ጽዮን ነው። ትርጓሜውም የጽዮን ደስታ፣ ተድላ ማለት ነው።
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምልጃ አይለየን።

ኦ ፍጡነ ረድኤት በብዙኅ ፆታ፣ከመ እግዝእትከ ርግበ ኤፍራታ፣በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታህታ፣አምህለከ ጊዮርጊስ በስመ እምከ ቴዎብስታ፣ሞገሰ ስም ሀበኒ ከመ ስምከ መንታ።
30/06/2025

ኦ ፍጡነ ረድኤት በብዙኅ ፆታ፣
ከመ እግዝእትከ ርግበ ኤፍራታ፣
በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታህታ፣
አምህለከ ጊዮርጊስ በስመ እምከ ቴዎብስታ፣
ሞገሰ ስም ሀበኒ ከመ ስምከ መንታ።

23/08/2023

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Andromeda Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share