
04/08/2025
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ መስክ አለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተባለ።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮሪ ጡሹኔ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ለማሳደግ ጥረቶች ቢኖሩም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በርካታ ስራዎች ይጠበቃሉ ብለዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ጉባኤው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት እያከበረ በሚገኝበት ወቅት መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የለውጥ ሐዋሪያ ናቸው ያሉት ፕሬዜዳንቱ በዚህ ረገድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብዙ ርቀት መጓዙን ይናገራሉ።
በቃል ኪዳን ቤተሰብ ዙሪያ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምርት ተቋማት የልምድ ልውውጥ መድረክ ተዘጋጅቶ የፋሲለደስ ስምምነት መፈራረማቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርም ዩኒቨርሲቲ በመባል ከፍተኛ ቦታ የያዘ ሲሆን ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው።
ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ ጠባይ አላቸው ከውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያለው አብሮ የመስራት ልምድ በሀገር ውስጥም መጠናከር
እንዳለበት ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለሚደረገው ሁለገብ የልምድ ልውውጥ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቂርጠኝነት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በአብነት ታምራት