Wollo herald

Wollo herald We speak what we see, we testify what we hear!

ሀገር ወዳዱ የፅናት ተምሳሌት የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
17/08/2025

ሀገር ወዳዱ የፅናት ተምሳሌት የጥበብ ሰው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ከ645 ሚለዬን ብር በላይ በጀት የተያዘለት የቦሩ አጠቃላይ ሆስፒታል የሱስ ማገገሚያ ማዕከል  ግንባታው የደረሰበት አፈፃፀም፦የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአሜሪካ ሚሲዮናውያን  1947 የተመ...
12/08/2025

ከ645 ሚለዬን ብር በላይ በጀት የተያዘለት የቦሩ አጠቃላይ ሆስፒታል የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታው የደረሰበት አፈፃፀም፦

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአሜሪካ ሚሲዮናውያን 1947 የተመሠረተ ሲሆን ለስጋ ደዌ፣ የቆዳና የአይን ህክምና ለመስጠት ታልሞ በልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃ/ስላሴ ተመርቆ የተከፈተ መሆኑ ይታወቃል።

ሆስፒታሉ በአገራችን ካሉ ዝነኛና የህዝብ እምነትን ካተረፉ የጤና ተቋማት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን ለአካባቢያችን ማህበረሰብም ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ ጊዜ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ እውቅናና ሽልማት ያገኘ ተቋም ነው።

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአማራ ክልል መድሃኒት የተላመደ ቲቪን በማከም የመጀሪያው ሆስፒታል ሲሆን የተሻለ ማይክሮ ባዮሎጂካል ላብራቶሪ ያለው በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ላብራቶሪው መድሃኒት የተለማመደን ቲቪ በተሻለ መንገድ ለመለዬት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።

ሆስፒታሉ እየሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ የሱስ ማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታ እየተገነባ ያለ ሲሆን ሲጠናቀቅ በ120 አልጋዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የአዕምሮ ህሙማን ማከም ያስችላል ተብሏል።

ለፋኖ ሕክምና አልሰጠንም - ዓይደር ሆስፒታል (መቐለ)-------"ለፋኖ ቁስለኞች ህክምና አልሰጠንም" ሲል አይደር ሆስፒታል ገለፀ፡፡ በሰሞኑን በአማራ ክልል ቆቦ ውስጥ በፋኖ ታጣቂዎችና በመ...
12/08/2025

ለፋኖ ሕክምና አልሰጠንም - ዓይደር ሆስፒታል (መቐለ)
-------
"ለፋኖ ቁስለኞች ህክምና አልሰጠንም" ሲል አይደር ሆስፒታል ገለፀ፡፡ በሰሞኑን በአማራ ክልል ቆቦ ውስጥ በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት ሀይሎች መካከል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ ቁስለኛ ታጣቂዎችን መቀሌ የሚገኘው አይደር ሆስፒታል እንዳከመ ሲገለፅ መቆየቱን ወጋህታ ፋክትስ አውስቷል፡፡
እንደዘገባው ቅዳሜ ነሀሴ 3 ቀን 2017 በቆቦ ከተማ በተፋላሚዎቹ መካከል ከፍተኛ ውጊያ የተከናወነ ሲሆን ይህንን ተከትሎ በውጊያው የቆሰሉ ታጣቂዎች በመቀሌ አይደር ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ስለመሆኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት ተገልጿል፡፡
ስለጉዳዩ የአይደር አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ህዝብ ግንኙነት ቢሮን ማነጋገሩን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ቢሮው በሰጠው መልስም ‹‹ሰሞኑን በአማራ ክልል ከተከናነው ውጊያ ጋር በተያያዘ እኛ ጋር ተኝቶ የታከመ አንድም ቁስለኛ የለም›› ብሏል፡፡ የዜና ምንጩ እንዳለው የሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል ሰራተኞችም እንዲህ አይነት ታካሚ እንዳላዩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንትይህን መረጃ የርሳቸው ዘመድ ያደረሰኝ ሲሆን እኔም አቶ ናስር ሀሰንን በስልክ አግኝቼ አው...
11/08/2025

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ታዋቂ አርማ ዲዛይን ያደረጉት አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንት

ይህን መረጃ የርሳቸው ዘመድ ያደረሰኝ ሲሆን እኔም አቶ ናስር ሀሰንን በስልክ አግኝቼ አውርቻቼዋለሁ። በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ነው ። ከሳምንት በኋላም እንደምንገናኝ ተቀጣጥረናል። እስከዛው ድረስ የባንኩ አርማ ሲሰራ የነበረውን ሂደት በተመለከተ ያላቸውን ትዝታ እንዲህ በማለት አካፍለውኛል


የቀድሞውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርማ (ሎጎ) ሙያዬና ሥራዬ ባይሆንም ማንም ሳይጠይቀኝና ሳያዘኝ በራሴ ተነሣሽነት አንዲት ሣንቲም ሳይከፈለኝ ዲዛይን አድርጌና ክሊሼውን እንግሊዝ ሀገር በነፃ አሰርቼ ለወቅቱ የባንኩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ለአቶ አለሙ አበራ አቅርቤ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎ ላለፋት 50 ዓመታት አገልግሏል።

በመሆኑም አርማው በቼኮች በቁጠባ ሒሣብ ደብተሮችና በበንኩ የፅህፈት መሣሪያዎች ላይ እንዲታተም አስደረግኩ ።

በወቅቱ የባንኩ የሒሣብና የኢንቬስትሜንት (መዋዕለ ንዋይ) መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ነበርኩ ።

በወቅቱ ለዚህ ሥራዬ የቃል ምስጋና እንኳን አላገኘሁም ነበር። አሁን ያን ወርቃማና ሽክርክር አርማ ለመተካት ግማሽ ቢሊዮን ብር ከማስወጣቱም በላይ በየሕንፃዎቹ ላይ ያሉትን አርማዎች አፍርሶ አዲሱን መተካት ፣ ያሉትን የጽህፈት መሣሪያዎች የቼክና የቁጠባ ደብተሮች ፣ የኮምፒዩተር ሶፍትዌሮችና ወዘተ ለመቀየር የሚወጣው ወጪ የትየሌሌ ነው።

በዚያ ላይ አዲሱን አርማ በመላ ዓለም ላሉ ባንኮች የፋይናንስ ድርጅቶች ለባንኩ ደምበኞች ሀ ብሎ ለማስተዋወቅ ሚሊዮኖች ያስወጣልና ትርፍና ኪሣራው በሚገባ ታስቦበታል ወይ ያሰኛል ? በማለት ይገልጻሉ አቶ ናሥር ሐሰን የቀድሞው የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት

አቶ ናሥር ሐሰን በትጋት በታማኝነት፣በቅንነት ከነበረባቸው ሃላፊነት በተጨማሪ ያሳዩት ትጋት የሚያስደንቅ እና የሚያስተምር ነው ።
በቀጣይ በአካል አግኝቻቸው ታሪካቸውን ያካፍሉናል ብየ እገምታለሁ ። መረጃውን ላደርስከኝ፣ከርሳቸው ጋር ላገናኘኸኝ አዲስ ምስጋናየ ይድረስህ

(አብዱረሂም አህመድ )
Abdurahim ahmed page
Abdurehim Mohammed

የልጅ እያሱ በሃር ዛፍ ~~~~~~~~~~የልጅ እያሱ ባህር ዛፍ በኦሮሞ ብ/ዞን አስተዳደር  ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ ከተማ በሚገኘው ትልቁ ገበያ የሚገኝ ሲሆን ረጅም እድሜ ያስቆጠረ እና ትል...
11/08/2025

የልጅ እያሱ በሃር ዛፍ
~~~~~~~~~~
የልጅ እያሱ ባህር ዛፍ በኦሮሞ ብ/ዞን አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ ከተማ በሚገኘው ትልቁ ገበያ የሚገኝ ሲሆን ረጅም እድሜ ያስቆጠረ እና ትልቅ ታሪክ ያለዉ ባህር ዛፍ ነው ።

በዛን ዘመን ንጉስ ልጅ እያሱ ወደ አዲስ አበባ በሚሄድበት ወቅት በእጁ የተከለው ባህር ዛፍ እንደሆነ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ ::

ይህ ረጅም እድሜ ያስቆጠረው እና ታሪካዊ ባህር ዛፍ ሃምሌ 30/2017 በሰንበቴ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብና ወድቋል ።

አውሮፕላን ጣቢያ ለወልዲያና አካባቢውበፌድራል ትራንሰፖርትና ሎጂስትክ ሚኒስተር መሪ ዕቅድ መሠረት በቅርቡ መገንባት አለባቸው ተብለው ከሚጠበቁ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መካከል ወልዲያና አካባቢው...
04/08/2025

አውሮፕላን ጣቢያ ለወልዲያና አካባቢው

በፌድራል ትራንሰፖርትና ሎጂስትክ ሚኒስተር መሪ ዕቅድ መሠረት በቅርቡ መገንባት አለባቸው ተብለው ከሚጠበቁ የአውሮፕላን ጣቢያዎች መካከል ወልዲያና አካባቢውን የሚያስተናግደው ጣቢያ ቀዳሚው ነው። ነገር ግን አስካሁን ግንባታውን ለማስጀመር ምንም ዓይነት ምልክት የለም። ከበጀት እጥረት ወይስ ሌላ ፍላጎት እንደሆነ ግልጽ አይደለም።

አውሮፕላን ጣቢያ የሚገነባው ከአትራፊነት አንጻር ከሆነ ከወልዲያና አካባቢው በላይ ተመራጭ ማን ሊሆን ይችላል?

👉 በዛሬው የብር ዋጋ ቢተመን በቢሊዮን ብሮች ወጭ ተደርጎ በወልዲያ ከተማ የተገነባው ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ፤ በ2029(ጊዜውን እርግጠኛ ባልሆንም) ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ አገልግሎት እንዲሠጥ ከተፈለገ የአውሮፕላን ጣቢያው አሁኑኑ ግንባታው መጀመር ይገባዋል። መቼም የአዘጋጅነቱን ጥያቄ አገራችን ያቀረበችው እንደ ወልዲያው ዓይነት ስቲዲየምን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ግልጽ ነው።

👉 ብዙዎች ስለ ወልዲያ ሲያስቡ የሚታያቸው የሰሜን ወሎ ዞን ብቻ ነው። ነገር ግን ወልዲያና አካባቢው ላይ የሚገነባው አውሮፕላን አገልግሎት የሚሠጠው ለምዕራባዊ የአፋር ክልል እና ለደቡባዊ የትግራይ አካባቢዎች ጭምር እንዲሁም ለደቡብ ወሎና ዋግኽምራ ዞኖች በከፊል ነው። ለምሳሌ

ከአፋር ክልል አካባቢወች ብንወስድ
👉 ጭፍራ
👉 ቴሩ
👉 ያሎ ወረዳ ወ.ዘ.ተ.
ከትግራይ ክልል አካባቢወች ብንወስድ
👉 ማይጨው
👉 መሆኒ
👉 እንዳ መሆኒ
👉 ራያ አዘቦ
ከሰሜን ወሎ ዞን ብንወስድ
👉 ራያ አላማጣ ወረዳ
👉 ባላ ወረዳ
👉 አላማጣ፣ ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ ባላ ከተሞች
👉 ራያ ቆቦ ወረዳ
👉 ቆቦ፣ ሮቢት፣ ጎብዬ ወዘተ ከተሞች
👉 ጉባላፍቶ ወረዳ
👉 ሐራ፣ ሳንቃ ከተሞች
👉 ሀብሩ ወረዳ
👉 መርሳ፣ ሲሪንቃ፣ ውርጌሳ፣ ድሬሮቃ፣ ጊራና ወዘተ
👉 ግዳን ወረዳ
👉 ሙጃ፣ ዴንሳ፣ ወንዳች፣ አስቂት ወዘተ ከተሞች
👉 አንጎት ወረዳ
👉 አሁን ተገኝ፣ ቀበሮ ሜዳ ወዘተ ከተሞች
👉 ጋዞ ወረዳ
👉 ስታይሽና ወዘተ ከተሞች
👉 ሌሎቹ ለላልይበላ ይቀርባሉ በሚል ነው

ከዋግ ኸምራ ዞን ብንወስድ
👉 ወፍላ ወረዳ
👉 ኮረም ከተማ
👉 ዛታ ወረዳ ወዘተ አካባቢዎች
👉 ሌሎቹ ለላልይበላ ይቀርባሉ በሚል ነው

ከደቡብ ወሎ ዞን ብንወስድ
👉 አምባሰል ወረዳ
👉 ውጫሌና ጢስአባሊማ ከተሞች
👉 ሌሎቹ ለኮምቦልቻ ይቀርባሉ በሚል ነው

👉 ከየትኛውም አካባቢ በላይ የማዳም ቅመምች የሚባሉትን ወደ መካከለኛው ምስራቅ በመላክ እና ከፍተኛ የሆነ የሰው ፍሰት ያለበት አካባቢ ነው። በተጠቀሱት አካባቢዎች በእያንዳንዱ ቤተሠብ ውስጥ ከ 1-2 ሰው በአማካይ የቤተሠብ አባሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ያልሄደበት ሰው የለም። በዚህ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ የአየር ትራንስፖርትን የሚጠቀም አካባቢ ነው። አውሮፕላን ጣቢያው ቢከፈት በአንጻራዊነት ከቀድሞዎቹ በላይ ከፍተኛ የተጠቃሚ ፍሰት እንደሚያገኝ በቅደመ ዳሰሳ ጥናት ማረጋገጥ ይቻላል።

👉 ያለፉትን 7 ዓመታት የአገራችንን ሁኔታ ስናስተውል ከአገር ደህንነትም አንጻር ወልዲያ ከተማ የነበራትን ቀጠናዊ

የዑጋንዳን ኘሬዚዳንት ፎቶ አንስቶ ያለፊልተር የፖሰተው ኬኒያዊ ጋዜጠኛ እየተፈለገ ነውጋዜጠኛው ያለበትን ለጠቆመ መቶ ሺህ ዶላር እንደሚሰጡ የዑጋንዳ መንግሥት ተናግሯል ጋዜጠኛው ከተያዘ የእድ...
03/08/2025

የዑጋንዳን ኘሬዚዳንት ፎቶ አንስቶ ያለፊልተር የፖሰተው ኬኒያዊ ጋዜጠኛ እየተፈለገ ነው
ጋዜጠኛው ያለበትን ለጠቆመ መቶ ሺህ ዶላር እንደሚሰጡ የዑጋንዳ መንግሥት ተናግሯል ጋዜጠኛው ከተያዘ የእድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል

በመኪና አደጋ የሰው ህይወት አለፈ ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ  ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ  መኪና በተለምዶ ሀረጎ ተብሎ በሚጠራ ቦታ  ላይ በዛሬው እለት ከቀኑ 7:00 ሰአት  በደረሰበት የመገልበጥ አደ...
30/07/2025

በመኪና አደጋ የሰው ህይወት አለፈ

ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ መኪና በተለምዶ ሀረጎ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በዛሬው እለት ከቀኑ 7:00 ሰአት በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የሰው ህይወት አልፏል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፍሪክ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና ክፍል ሀላፊው ኮ/ር ብርሀኑ ተሾመ ለፔጃችን እንደተናገሩት በአደጋ አሸከርካሪውና ረዳቱን ጨምሮ የ3 ስዎች ህይወት ማለፉን አንስዋል።

የአደጋው ምክንያት ምርመራ ላይ መሆኑን ተነስቷል።

ኢትዮጵያ አንድ ቢሊየነር አስመዘገበች።ቢሊየነርስ አፍሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ 10 እጅግ የናጠጡ ሀብታሞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡መፅሔቱ ግብፅ፣ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀ...
30/07/2025

ኢትዮጵያ አንድ ቢሊየነር አስመዘገበች።

ቢሊየነርስ አፍሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ 10 እጅግ የናጠጡ ሀብታሞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

መፅሔቱ ግብፅ፣ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ያላቸው ባለሀብቶችን ማፍራት የቻሉ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን ያላት ቢሊየነር አንድ ብቻ ነው፡፡ እሳቸውም ሼክ መሀመድ አልአሙዲ ናቸው፡፡

በመከተል በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉ በርካታ ሚሊየነሮች በኢትዮጵያ እንዳሉ ዘገባው አስረድቷል፡፡

አልአሙዲ በቁጥር አንድነት የተቀመጡ ሲሆን፣ የሀብታቸው መጠን 9.56 ቢሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡ በሁለተኛ የተቀመጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩትና የሳንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ ናቸው፡፡

በቢሊየነርስ አፍሪካ ዝርዝር በሶስተኛነት የተቀመጡት የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ናቸው፡፡

በአራተኛ ደረጃ የተቀመጡት ደግሞ ከሀይል አቅርቦት እስከ ሸቀጣ ሸቀጥና ሪል ስቴት ዘርፍ ባሉ ስራዎች ላይ የተሰማሩት አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ ናቸው፡፡

መፅሄቱ በአምስተኛ ደረጃ ያስቀመጣቸው በዋሽንግተን ዲሲና ኒውዮርክ ከተሞች በርካታ የነዳጅ ማደያዎች ያላቸውና በቨርጂኒያ የሪል ስቴት ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን አቶ ኢዮብ ማሞ ነው፡፡

አቶ ከተማ ከበደ ስድስተኛ፣ አቶ አለማየሁ ከተማ ሰባተኛ፣ አቶ ብዙአየሁ ቢዘኑ ስምንተኛ፣ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ዘጠነኛ እንዲሁም የአቪየሽን ባለሙያው አቶ ግርማ ዋቄ አስረኛ ሁነው አጠናቀዋል፡፡

20/07/2025

ቀድመን ለመከላከል የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት!!

ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ከማይታወቁ ግለሰቦች ስልክ ጥሪ እየደረሳቸው እንደሆነና ስልክ ቁጥሮቹም፣
Tel: +375602605281
Tel: +37127913091
Tel: +37178565072
Tel: +56322553736
Tel: +37052529259
Tel: +255901130460
ወይም ማንኛውም ቁጥር በ+371,+375,+381 የሚጀምሩ እንደሆነ ለመንግስት አካላት አሳውቀዋል።
እነዚህን ስልክ ቁጥሮች የሚጠቀሙት ግለሰቦች ሲደውሉ አንዴ ብቻ ከጠራ በኋላ ይዘጉታል።

እርስዎ መልሰው ሲደውሉ የርስዎን Contact List በ 3sec ውስጥ ወደ ራሳቸው ኮፒ በማድረግ እንዲሁም ሞባዬልዎ ላይ ስለ እርስዎ ባንክ ወይም ክሬዲት ካርድ መረጃ በአንዴ በመጥለፍ የማጭበርበር ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።

ከላይ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥር ከተደወለሎት አይመልሱ ፡ወይም መልሰው አይደውሉ።እንዲሁም በማንኛውም ደዋይ #90 or #09 በመስመር እንዲነኩ ከተጠየቁ አይንኩ።

ምክንያቱም በቀላሉ ሲማችሁን አክሰስ በማድረግ በናንተ ስም የፈለጉት ወንጀል በመስራት እራሳቸውን ስለሚሸሽጉ ነው።
ይህንን መልዕክት ለቻላችሁ ሰው ፎርዋርድ በማድረግ ህዝባችንን ከዚህ መሰል ማጭበርበሮች እንታደግ።
ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት

🔸ኢትዮጵያ ትቅደም፤በሽታ ይውደም፤1967 ዓ.ም
18/07/2025

🔸ኢትዮጵያ ትቅደም፤በሽታ ይውደም፤1967 ዓ.ም

ሰበር ዜናየቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሕወሓት እና የፌዴራል መንግስቱን ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡እየተባባሰ የሄደውን የሕወሓት እና ፌዴራል መንግስቱን ውጥረት ተከትሎ...
18/07/2025

ሰበር ዜና

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሕወሓት እና የፌዴራል መንግስቱን ለማነጋገር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

እየተባባሰ የሄደውን የሕወሓት እና ፌዴራል መንግስቱን ውጥረት ተከትሎ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች ስብሰባ ለመጥራት ማቀዳቸውን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይሁንና ግን ይህ የንግግር ጥሪ ከማዕከላዊ መንግስቱ ተቃውሞ እንደገጠመው ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው እለት ከትግራይ ከተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ጋር መነጋገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

Address

Woldia
26

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo herald posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share