23/03/2026
ተጨማሪ የነዳጅ መያዣ የገጠሙ 13 አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼
በግልገል በለስ ከተማ ህገወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በተደረገ ክትትል፣ ከፋብሪካ ስሪት ውጭ ተጨማሪ የነዳጅ መያዣ (ሳልቫቶ) የገጠሙ 13 የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
የከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ጉርሜሳ እንደገለጹት፤ ተሽከርካሪዎቹ እስከ 600 ሊትር የሚይዝ ተጨማሪ ታንከር በሕገወጥ መንገድ የተገጠመላቸው ናቸው ብለዋል።
በዕለቱ በተደረገ ቁጥጥር 16 ሳልቫቶዎች ከተሽከርካሪው ላይ ተፈቶ ገቢ የተደረጉ ሲሆን፣ በነዳጅ ማደያዎችና በኬላዎች ላይ የሚደረገው ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኃላፊው ተናግረዋል።
ሰልቫቲዮ ተፈቶ የተወሰደባቸው ተሽከርካሪዎች ቆመው እንደሚገኙ ተሰምቷል።