05/12/2025
የወጣቶችን ስራ አጥነት በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ቃዋቆቶ ህዳር 26/2018 አልቾ ኮሙኒኬሽን
በአልቾ ውሪሮ ወረዳ የወጣቶችን ስራ አጥነት በመቀነስና በተለያዩ የስራ መስኮች በማደራጀት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በወረዳው በተደራጁ ማህበራት የተሰሩ ተግባራትን የዞን እና የወረዳ አመራር አካላት የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመስክ ምልከታው የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህድያ ሀሰን የስልጤ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ምክትል እና የገጠር ዘርፍ ሃላፊው አቶ አብዱልመናን ሁሴን የመምሪያው ምክትል እና የከተማ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ናስር ጀማል የመምሪያው ምክትል እና የማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዘምዘም መሀመድ የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል እና እንስሳት ዘርፍ አቶ ነጃ የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሱልጣን በርጋ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙዘይን መሀመድ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙባረክ አሊ እና ሌሎች የጽ/ቤት ሃላፊዎች እና የተደራጁ ማህበራት ተገኝተዋል፡፡