
03/08/2025
የወልድያ ኤርፖርት ጥያቄ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል!
ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የወልድያ ተወላጅ እና ወዳጅ እንዲሁም የአላማጣ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ አራዱም፣ ሮቢት፣ ጎብዬ፣ ዶሮ ግብር፣ ድሬ ሮቃ፣ ሀሮ፣ ሀራ፣ ዶሮ ግብር፣ ስሪንቃ፣ መርሳ፣ መሀል አምባ፣ ሊብሶ፣ ጊራና፣ ውርጌሳ፣ ውጫሌ፣ ሳንቃ፣ እስታይሽ፣ ሙጃ ... እና አጎራባች ቀበሌዎች የተወለዳችሁ፣ የምትኖሩ እና ወዳጅ የሆናችሁ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ይመለከታል።
በዚህ የ10 ቀን ዘመቻ የምንሰራው የወልድያ ኤርፖርት እንዲፈቀድ እና ስራ እንዲጀመር ዘመቻውን በሚከተለው መንገድ መቀላቀል እና ማሳለጥ እንችላለን :-
1. የወልድያ ኤርፖርት ጥያቄን የተመለከቱ ማንኛውንም ፖስት ላይክ ማድረግ፣ ኮሜንት ማድረግ እና ሼር ማድረግ፣
2. እነዚህን ፖስቶች ቲክቶክ ላይ ወስደን መልቀቅ፣ የተለቀቁ ፖስቶችን ❤ ማድረግ፣ ኮሜንት እና Copy Link ማድረግ፣
3. በያንዳንዱ ፖስታችን ውስጥ እነዚህን ሀሽታጎች ወስደን መጠቀም፣ ኮሜንት ላይ እነዚህን ሀሽታጎች መጠቀም፣ ይሄም አንዱን ሀሽታግ የተጫነ ሰው ይሄን ሀሽታግ የተጠቀሙ ሰዎች ፖስቶችን ስለሚያመጣልን ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል።
የምንጠቀማቸው ሀሽታጎች እነዚህ ናቸው :-
4. በየፖስታችሁ እና ኮሜንቱ Woldia_Times ን ኮሜንት ላይ ሜንሽን አድርጓት። ፖስታችሁን ሼር እናደርጋለን። ፅሁፎችን እና ፎቶዎችን በገፃችን ከዛሬ ጀምሮ እናቀርባለን። ይህ የ1 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ጥያቄ እስኪመለስ ከፊት ቆመን እናስተባብራለን!
ወልድያዎች፣ የአካባቢው ተወላጆች እና ወዳጆች የት ናችሁ? እስኪ እጃችሁን አሳዩን?