Yeju Standard

Yeju Standard መረጃ መሠረታዊ ፍጆታ ነው

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እ...
25/06/2025

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።

መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።

ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ከዛሬ ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በ400% ሊጨምር እንደሚችል ተሰምቷል።ከሦስት ዓመታታ በኃላ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ታሪፍ በ400 ፐርሰንት እንደሚጨምር የዘገበው ሪፖርተር ነው::ከዚሁ ጋር በተ...
25/06/2025

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በ400% ሊጨምር እንደሚችል ተሰምቷል።

ከሦስት ዓመታታ በኃላ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ታሪፍ በ400 ፐርሰንት እንደሚጨምር የዘገበው ሪፖርተር ነው::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመጭው መስከረም ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ:-
📌ለኤርትራ 42 ሜጋ ዋት
📌ለሶማሊያ 51 ሜጋ ዋት
📌ለሶማሌ ላንድ 7 ሜጋ ዋት
📌ለየመን 240 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የሚያስችል አዲስ መስመር ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ ነው ተብሏል።

የኢራን የኑክሌር ተቋማትና የትራምፕ እርግጠኝነት!? አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በኢራን የኒኩሌር ተቋማት  ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን  የኒኩክሌር ተቋሞቿን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ...
24/06/2025

የኢራን የኑክሌር ተቋማትና የትራምፕ እርግጠኝነት!?

አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በኢራን የኒኩሌር ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን የኒኩክሌር ተቋሞቿን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኗን ያስታወቀች ሲሆን፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ግን ኢራን በደረሰባት አውዳሚ ጥቃት ሳቢያ ከዚህ በኋላ የኒኩሌር ተቋማቷን እንደማትገነባ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ "ኢራን መቼም ቢሆን የኒኩሌር ተቋሞቿን መልሳ አትገነባም" ብለዋል፡፡

የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ መሀመድ ኢስላሚ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራቸው ጥቃት የደረሰባቸውን የኒኩሌር ተቋማት ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዷን አስታውቀዋል፡፡

የኢራንን የበቀል ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ፍንዳታዎች ተሰሙ*************************ኢራን የአሜሪካን ጥቃት እንደምትበቀል ማስጠንቀቋን ተከትሎ በኳታር ዋና ከ...
23/06/2025

የኢራንን የበቀል ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ፍንዳታዎች ተሰሙ
*************************

ኢራን የአሜሪካን ጥቃት እንደምትበቀል ማስጠንቀቋን ተከትሎ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢራን ኳታር በሚገኘው የአሜሪካን የጦር ሰፈር ላይ 6 ሚሳኤሎችን ተኩሳለች ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ኳታር የአየር ክልሏን ከዘጋች ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ከኢራን የሚሳኤል ጥቃት ማስተናገዷን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዜና፡ በሳዑዲ_አረቢያ  37 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፁበሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ቢያንስ 37 ኢ...
20/06/2025

ዜና፡ በሳዑዲ_አረቢያ 37 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፁ

በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ቢያንስ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲሉ 31 የሲቪል ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ መቶዎች በሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግባቸው እንደሚችል ተገልጿል።

ደርጅቶቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ከህገ ወጥ አደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት እየጨመረ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ፣ #ሶማሊያና #ግብፅ ዜጎች ህይወት "ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው" ገልጸዋል።

መግለጫው፤ በተያዘው ዓመት ሰባት ኢትዮጵያውያን እና 19 የሶማሊያ ዜጎች “ሃሺሽ በማዘዋወራቸው” ግድያ እንደተፈጸመባቸው ገልጿል። በተጨማሪም “ሰኔ 9 ፣ 2017 ዓ/ም ሶስት የኢትዮጵያ ዜጎች እንደተገደሉ" እና ሌሎች ደግሞ በማንኛውም ጊዜ ልንገደል እንችላለን በሚል ስጋት ውስጥ እንዳሉ አመላክተዋል።

 #ከ10ሺ ብር በላይ ካሽ መያዝ ያስቀጣል ተባለ‼️በግብይት ወቅት ከ 10 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም፣ለከፋዩ በወጪነት፣ለተቀባዩ ደግሞ አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልበት ያደርጋል ተባ...
12/06/2025

#ከ10ሺ ብር በላይ ካሽ መያዝ ያስቀጣል ተባለ‼️

በግብይት ወቅት ከ 10 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብን መጠቀም፣ለከፋዩ በወጪነት፣ለተቀባዩ ደግሞ አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልበት ያደርጋል ተባለ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው አቶ ተወዳጅ መሐመድ እንዳሉት አዋጁ ተግባራዊ የሚደረገው በጥሬ ገንዘብ የሚፈፀም ግብይትን መገደብን ታሳቢ አድርጎ ነው።

በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ሲጸድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈጸም እንደሚማስቀጣ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል።

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን ሽንኩርት መያዙን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።   በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን ሽንኩርት መያዙን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ንግድና ገበ...
13/04/2025

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን ሽንኩርት መያዙን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን ሽንኩርት መያዙን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ አዲሱ ወንድሙ ሁለት አይሱዙ መኪና ሽንኩርት በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግረዋል። ሽንኩርቱ በቁጥጥር ሥር የዋለው ለጅምላ ንግድ ባልተፈቀደ እና ከሽንኩርት ንግድ ጋር ባልተገናኘ የንግድ ፈቃድ ሲንቀሳቀስ መኾኑንም ገልጸዋል።

በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘው ሽንኩርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለኅብረተሰቡ እንደሚቀርብም አስታውቀዋል።

"በህገ ወጥ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው" - አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋበአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ...
03/04/2025

"በህገ ወጥ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው" - አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአምባሳደሩ ኤርቪን ማሲንጋ አማካኝነት መልዕክት አስተላልፏል።

በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባት፣ ቪዛ ለማግኘት መዋሸት፣ ያለ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ስራ መስራትና የቪዛ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ መቆየት ከባድ ቅጣት ያስከትላል።

ቅጣቶቹ እስርን፣ ወደ ሃገር መመለስን እና ዳግም ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መከልከልን እንደሚያካትት ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።

አክለውም፥ "በህገ ወጥ መልኩ በአሜሪካ የሚኖር ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ካላችሁ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የምትነግሩበት ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

መልዕክቱ፥ የአሜሪካ መንግስት ሌሎች በህገወጥ መንገድ እንዲገቡ የሚተባበሩት ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

አሜሪካ በቅርቡም ህገወጥ ስደትን መከላከል አልቻሉም ባለቻቸው የሃገራት ባለስልጣናት ላይ የቪዛ ገደብ መጣሏን አስታውሰዋል።

በህገወጥ መንገድ መግባት ከሚያስገኘው ጥቅም በላይ ጉዳቱ ያመዝናል ያለው ኤምባሲው ዜጎች የወደፊት ህይወታችን ከመጉዳት እንዲታጠቀቡ እና በህገወጥ መንገድ በአሜሪካ ያሉ ቤተሰቦቻቸውንም በጊዜ እንዲመለሱ ጥሪ እንዲያደርጉ አምባሳደሩ አሳስበዋል::

ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከ...
29/03/2025

ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል

የሸዋል ወር ጨረቃ ዛሬ ቅዳሜ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዘንድሮው የረመዷን ጾም ፍቅርና አብሮነትን የሚያሳዩ የጋራ የኢፍጣር መርሐ-ግብሮች የታዩበት እንደነበረም ገልጸዋል።

የምትመለከቷቸው ሁለት ደሴቶች በሚገርም ሁኔታ የተቀራረቡ ናቸው በመካከላቸው ያለው እርቀት 5 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው፣ እጅግ የተቀራረቡ ከመሆናቸው የተነሳ በክረምት ወራት በመካከላቸው ያለው ባህ...
29/03/2025

የምትመለከቷቸው ሁለት ደሴቶች በሚገርም ሁኔታ የተቀራረቡ ናቸው በመካከላቸው ያለው እርቀት 5 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው፣ እጅግ የተቀራረቡ ከመሆናቸው የተነሳ በክረምት ወራት በመካከላቸው ያለው ባህር በረዶ ሲሰራ የደሴቶቹ ነዋሪዎች ከአንዱ ደሴት ወደ ሌላኛው በእርምጃ ይንቀሳቀሳሉ።

አስቡት ጠዋት 4 ሰአት ከአንዱ ደሴት ተነስታችሁ የአንድ ሰአት ጉዞ አድርጋችሁ አንደኛው ደሴት ጋር ስትደርሱ የእጃችሁ ሰአት 5 ሰአት ማለት ሲገባው የተጋነነ ልዩነት ያሳያችዋል።
ምክንያቱም በሁለቱ ደሴቶች በተለያዩ ንፍቀ ክበቦች በምስራቅ ጫፍና በምዕራብ ጫፍ የሚገኙ በመሆናቸው በመካከላቸው ያለው የሰአት ልዩነት የ22 ሰአት በመሆኑ ጠዋት 4 ሰአት ላይ ጉዞውን የጀመረ ሰው 5 ሰአት ላይ መድረስ ሲገባው ጉዞውን ከጀመሩበት ከአንድ ቀን በዋላ ነው በሌላኛው ደሴት ላይ የሚደርሰው።
እነዚህ ሁለት ደሴቶች በአሜሪካና በሩሲያ የሚገኙ ሲሆን የትላንትናዋ ትንሿ ዳይሜድና የነገዋ ትልቅ ዳንሜድ ደሴት በመባል ይጠራሉ። በሁለቱም ደሴቶች ላይ ያሉ ሰዎች አዲስ አመትን ሁለት ጊዜ ነው የሚያከብሩት።
ተፈጥሮ ድንቅ ናት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረመዷን ወርን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት  መርሃ- ግብር አካሄደ።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት 1446ኛውን የረመዷን ወርን ምክን...
28/03/2025

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የረመዷን ወርን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት መርሃ- ግብር አካሄደ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልድያ ዲስትሪክት 1446ኛውን የረመዷን ወርን ምክንያት በማድረግ “አብሮነት ለበጎነት ፣ በረመዷን” በሚል መሪ ቃል የማዕድ ማጋራት መርሃ -ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩም በወልድያ ከተማ ለሚኖሩ 120 አቅመ ደካሞች 384,000 ብር ወጭ በማድረግ የአይነት ድጋፍ አድርጎል ።

ባንኩ የረመዷን ወርን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ያደረገው የማዕድ ማጋራት (ሶደቃ) አበረታች እና በአላህ ዘንድ ተወዳጅ ነው ያሉት የወልድያ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሟህሙድ ኑርየ ሳኒ በቀጣይም ባንኩ ከማህበረሰቡ ጎን በመቆም ይህን መሰል ማህበራዊ ሀላፊነትን የመወጣት እንቅስቃሴን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ለተደረገው ማዕድ ማጋራትም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ስም ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ብለዋል።

የወልድያ ዲስትሪክት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ይልማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመደበኛው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በዚህ በተቀደሰ እና የአብሮነት መገለጫ በሆነው የረመዷን ወር በወልድያ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ ማጋራት መርሃግብር ሲያከናውን ባንኩ ለማህበረሰቡ ያለውን አጋርነት እና ጥብቅ ቁርኝነት የበለጠ ከፍ እንደሚያደርግ በማመን ነው ብለዋል፡፡

በማዕድ ማጋራት (ሶደቃ) ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ለባንኩ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

የወንድ ዘር ፈሳሽ ልገሳን ሊጀመር ነው።በኢትዮጵያ ኩላሊት እና የወንድ ዘር ፈሳሽን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ልገሳን ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ...
27/03/2025

የወንድ ዘር ፈሳሽ ልገሳን ሊጀመር ነው።

በኢትዮጵያ ኩላሊት እና የወንድ ዘር ፈሳሽን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ልገሳን ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።

የወንድ ዘር ፍሳሽ እና የሰውነት አካል ልገሳን እንዲሁም መዳን በማይችል በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሐኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደውን ሕግ ጨምሮ አዳዲስ የጤና አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ ሕጎችን የያዘው የጤና አገልግሎትና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ጤናዬ ደምሴ ለአሐዱ ሬዲዬ ሲናገሩ እንደተሰማው ከሆነ ተቋሙ ከዚህ ቀደም የደም አገልግሎትን ብቻ ይሰጥ እንደነበር አስታውሰው፤ በ2015 ዓ.ም. ጀምሮ የዓይን ብሌን ልገሳን በማካተት እየሰራበት ይገኛል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ህብረ-ህዋስን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት አካል ልገሳን ለማከናወን አዲስ ኃላፊነት መቀበሉንም ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት ሂደቱ እንደ ዓይን ብሌን ልገሳ ሁሉ በፈቃደኝነት የተመሰረተና ሰዎች በሕይወት እያሉ በሚገቡት ቃልና ፊርማ መሠረት የሚከናወን ሲሆን፤ "ኩላሊትን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ክፍሎችን ያጠቃለለ ነው" ብለዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ ተቋሙ የደምና የአይን ብሌን ልገሳ ላይ በደንብ እየሰራበት እንደሚገኝ በማንሳት፤ የሰውነት አካል ልገሳን ለማስጀመር እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝና በቀጣይም በደንብ በተጠናከረ መንገድ እንደሚሰራበት ገልጸዋል።

አክለውም ይህ የሰውነት አካል ልገሳን የሚፈቅደው ሕግ እንደተቋሙም ሆነ እንደ ሀገር አዲስ በመሆኑ፤ ኅብረተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሮለት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት ምናልባትም ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ድረስ ሊወስድ እንደሚችል ም/ ዋና ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

Address

Al Amudin
Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeju Standard posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yeju Standard:

Share