
12/08/2025
ከ645 ሚለዬን ብር በላይ በጀት የተያዘለት የቦሩ አጠቃላይ ሆስፒታል የሱስ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታው የደረሰበት አፈፃፀም፦
የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአሜሪካ ሚሲዮናውያን 1947 የተመሠረተ ሲሆን ለስጋ ደዌ፣ የቆዳና የአይን ህክምና ለመስጠት ታልሞ በልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃ/ስላሴ ተመርቆ የተከፈተ መሆኑ ይታወቃል።
ሆስፒታሉ በአገራችን ካሉ ዝነኛና የህዝብ እምነትን ካተረፉ የጤና ተቋማት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን ለአካባቢያችን ማህበረሰብም ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ ጊዜ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ እውቅናና ሽልማት ያገኘ ተቋም ነው።
የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል በአማራ ክልል መድሃኒት የተላመደ ቲቪን በማከም የመጀሪያው ሆስፒታል ሲሆን የተሻለ ማይክሮ ባዮሎጂካል ላብራቶሪ ያለው በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል። ላብራቶሪው መድሃኒት የተለማመደን ቲቪ በተሻለ መንገድ ለመለዬት ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።
ሆስፒታሉ እየሰጠ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ የሱስ ማገገሚያ ህክምና ማዕከል ግንባታ እየተገነባ ያለ ሲሆን ሲጠናቀቅ በ120 አልጋዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የአዕምሮ ህሙማን ማከም ያስችላል ተብሏል።