Woldia Fortune

Woldia Fortune መረጃ አርነት ያወጣሀል

"ሰሜን ኮሪያ ወደ ጃፓን ባህር (Sea of Japan) አቅጣጫ 10 ያህል ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ተኮሰች።ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት በፒዮንግያንግ አቅራቢያ ከሚገኘው የሱናን (Sunan) አካባቢ ሲሆን...
14/03/2026

"ሰሜን ኮሪያ ወደ ጃፓን ባህር (Sea of Japan) አቅጣጫ 10 ያህል ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ተኮሰች።

ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት በፒዮንግያንግ አቅራቢያ ከሚገኘው የሱናን (Sunan) አካባቢ ሲሆን፣ ያረፉትም ከጃፓን የኢኮኖሚ ክልል (EEZ) ውጭ በሆነ የባህር ክፍል ላይ ነው። እስካሁን ባለው መረጃ በአደጋው የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም።

የካሜኔይ ልጅ ከግድ*ያ ተረፉ‼️እሁድ:የካቲት 29 ቀን 2018 ዓም(ወልዲያ ፎርቹን)የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አላ ካሜኔይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መሞታቸውን ተከትሎ ልጃቸው ሞጅታ...
08/03/2026

የካሜኔይ ልጅ ከግድ*ያ ተረፉ‼️

እሁድ:የካቲት 29 ቀን 2018 ዓም(ወልዲያ ፎርቹን)

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አላ ካሜኔይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መሞታቸውን ተከትሎ ልጃቸው ሞጅታባ ካሜኔ አባቱን ተክቶ የኢራን መሪ ይሆናል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት በእስራኤል አየር ኃይል በተፈፀመ ጥቃት ከግድያ መትረፉን ነገር ግን የመቁሰል አደጋ እንደደረሰበት እስራኤል ቻናል 12 እንዲሁም ኒውዮርክ ፖስት አስነብቧል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የእስራኤል ባለስልጣናት በይፋ ያሉት ነገር የለም።

በሰሜን ወሎ ራያ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። ሐሙስ:የካቲት 28 ቀን 2018 አም(ወልዲያ ፎርቹን)በሰሜን ወሎ ዞን  ቆቦ ከተማ  የመምረጥ እና የመመረጥ መብትን የሚጠይቅ ሕዝባዊ ...
07/03/2026

በሰሜን ወሎ ራያ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ሐሙስ:የካቲት 28 ቀን 2018 አም(ወልዲያ ፎርቹን)

በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የመምረጥ እና የመመረጥ መብትን የሚጠይቅ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ "የመምረጥ እና የመመረጥ መብት ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው" በሚል መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። በሰልፉ የአምስት ወረዳ ሕዝብ የተሳተፈ ነው።

በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ አላማጣ ከተማ፣ ኮረም ከተማ እና የኦፍላ ወረዳ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን"የመምረጥና የመመረጥ መብት ህገመንግስታዊ መብታችን ነው" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።(ወልቃይት ኮሙኒኬሽን)
05/03/2026

ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን"የመምረጥና የመመረጥ መብት ህገመንግስታዊ መብታችን ነው" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
(ወልቃይት ኮሙኒኬሽን)

የእስራኤል ጥቃት በሊባነን። ። ። ። ። ። ። ። እስራኤል በሊባኖስ ሃዝሚህ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ የቦምብ ድብደባ ማካሄዷን ዘገባዎች አመላክተዋል።የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ኤጀንሲ እ...
04/03/2026

የእስራኤል ጥቃት በሊባነን

። ። ። ። ። ። ። ።
እስራኤል በሊባኖስ ሃዝሚህ ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ የቦምብ ድብደባ ማካሄዷን ዘገባዎች አመላክተዋል።

የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ኤጀንሲ እስራኤል በቤሩት አቅራቢያ በሚገኝ ሃዝሚህ ሆቴል ላይ ጥቃት እንደፈጸመች ዘግቧል። አምቡላንስ ወደ ቦታው መላኩን አስታውቋል።

በአልጀዚራ የተረጋገጠ ቀረጻ የፈረሱ መስኮቶችና ግድግዳዎች እንዲሁም ፍርስራሾች በየቦታው ተበትነው አሳይቷል።

እንደ አልጀዚራ ዘገባ የእስራኤል ሀይሎች የፈፀሙት ጥቃት ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ሲሆን ምናልባትም የግድያ ሙከራ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።

ጥቃቱ የኮምፎርት ሆቴልን ኢላማ ያደረገ ሲሆን እስካሁን ድረስ በሰዎች ላይ ስለደረሰ አደጋ የተገለፀ ነገር የለም። የእስራኤል ጦር ማንን ወይም ምን ኢላማ ለማድረግ እንደሞከረ በትክክል እስካሁን አልተናገረም።

ሌሊቱን በተከሰቱ ጥቃቶች በአራሙን በአንድ የመኖሪያ ህንፃ ውስጥ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ የጤና ሚንስቴር ይፋ ሲያደርግ በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ላይ በምትገኘው ባልቤክ ሌላ የመኖሪያ ህንፃ ላይ አራት ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 11 ሰዎች ቆስለዋል።

የወልድያ ኤርፖርት ጥያቄ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል!   ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የወልድያ ተወላጅ እና ወዳጅ እንዲሁም የአላማጣ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ አራዱም፣ ሮቢት፣ ጎብዬ፣ ዶሮ ግብር፣ ድሬ ሮቃ፣...
03/08/2025

የወልድያ ኤርፖርት ጥያቄ ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል!



ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የወልድያ ተወላጅ እና ወዳጅ እንዲሁም የአላማጣ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ አራዱም፣ ሮቢት፣ ጎብዬ፣ ዶሮ ግብር፣ ድሬ ሮቃ፣ ሀሮ፣ ሀራ፣ ዶሮ ግብር፣ ስሪንቃ፣ መርሳ፣ መሀል አምባ፣ ሊብሶ፣ ጊራና፣ ውርጌሳ፣ ውጫሌ፣ ሳንቃ፣ እስታይሽ፣ ሙጃ ... እና አጎራባች ቀበሌዎች የተወለዳችሁ፣ የምትኖሩ እና ወዳጅ የሆናችሁ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ይመለከታል።

በዚህ የ10 ቀን ዘመቻ የምንሰራው የወልድያ ኤርፖርት እንዲፈቀድ እና ስራ እንዲጀመር ዘመቻውን በሚከተለው መንገድ መቀላቀል እና ማሳለጥ እንችላለን :-

1. የወልድያ ኤርፖርት ጥያቄን የተመለከቱ ማንኛውንም ፖስት ላይክ ማድረግ፣ ኮሜንት ማድረግ እና ሼር ማድረግ፣

2. እነዚህን ፖስቶች ቲክቶክ ላይ ወስደን መልቀቅ፣ የተለቀቁ ፖስቶችን ❤ ማድረግ፣ ኮሜንት እና Copy Link ማድረግ፣

3. በያንዳንዱ ፖስታችን ውስጥ እነዚህን ሀሽታጎች ወስደን መጠቀም፣ ኮሜንት ላይ እነዚህን ሀሽታጎች መጠቀም፣ ይሄም አንዱን ሀሽታግ የተጫነ ሰው ይሄን ሀሽታግ የተጠቀሙ ሰዎች ፖስቶችን ስለሚያመጣልን ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል።
የምንጠቀማቸው ሀሽታጎች እነዚህ ናቸው :-


















4. በየፖስታችሁ እና ኮሜንቱ Woldia_Times ን ኮሜንት ላይ ሜንሽን አድርጓት። ፖስታችሁን ሼር እናደርጋለን። ፅሁፎችን እና ፎቶዎችን በገፃችን ከዛሬ ጀምሮ እናቀርባለን። ይህ የ1 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ጥያቄ እስኪመለስ ከፊት ቆመን እናስተባብራለን!

ወልድያዎች፣ የአካባቢው ተወላጆች እና ወዳጆች የት ናችሁ? እስኪ እጃችሁን አሳዩን?

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እ...
25/06/2025

የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከዛሬ ጀምሮ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሆነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት የሚያደርግ አዲስ መመሪያን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ለማድረግ ሲደረግ የቆየው ጥረት የመጨረሻው ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰዱ ተገልጿል።

መመሪያ ቁጥር SBB/94/2025 ባለፉት አንድ ዓመት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ግብዓት ተደርጎበት የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

ይህ መመሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሰረት የወጣ ሲሆን፣ የሚያስፈልገውን የሕግ ማዕቀፍ ማሟላቱ ተገልጿል።

ይህ አዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ባለሀብቶች፣ ባንኮችን እና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ባለሀብቶችን ጨምሮ፣ በኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ ያስችላል ተብሏል።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣዉ መግለጫ መመሪያው የውጭ ተዋናዮች የባንክ ዘርፉን እንዲቀላቀሉባቸው በርካታ መንገዶችን ያቀርባል፤ ከእነዚህም መካከል ቅርንጫፍ ባንኮችን፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፎችን ወይም የወኪል ቢሮዎችን ማቋቋም ይገኙበታል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ተሳትፎ ክፍት መሆኑን የገለፀ ሲሆን የውጭ ባንኮች እና ባለሀብቶችም ማመልከቻዎቻቸውን ከዛሬ ጀምሮ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በ400% ሊጨምር እንደሚችል ተሰምቷል።ከሦስት ዓመታታ በኃላ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ታሪፍ በ400 ፐርሰንት እንደሚጨምር የዘገበው ሪፖርተር ነው::ከዚሁ ጋር በተ...
25/06/2025

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በ400% ሊጨምር እንደሚችል ተሰምቷል።

ከሦስት ዓመታታ በኃላ የኤሌክትሪክ አግልግሎት ታሪፍ በ400 ፐርሰንት እንደሚጨምር የዘገበው ሪፖርተር ነው::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመጭው መስከረም ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ:-
📌ለኤርትራ 42 ሜጋ ዋት
📌ለሶማሊያ 51 ሜጋ ዋት
📌ለሶማሌ ላንድ 7 ሜጋ ዋት
📌ለየመን 240 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የሚያስችል አዲስ መስመር ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ ነው ተብሏል።

የ25 ቀናት እስር ተወሰነበት‼በቅርቡ የትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም የመንግስት ስራተኛ የሆነ ግለሰብ የደበደበው ተከሳሽ ታማኝ አስማማው አንዳርጌ 3 ዓመት የተፈረደበት ሲሆን ነገር ግን:- ተከሳሽ...
25/06/2025

የ25 ቀናት እስር ተወሰነበት‼

በቅርቡ የትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም የመንግስት ስራተኛ የሆነ ግለሰብ የደበደበው ተከሳሽ ታማኝ አስማማው አንዳርጌ 3 ዓመት የተፈረደበት ሲሆን ነገር ግን:-

ተከሳሽ:-

1. አረንጓዴ አሽራ በችግኝ ተከላ አስተዋጽኦ ያደረገ ስለሆነ

2.የቤተሰብ አስተዳዳሪ ስለሆነ

3. ታማሚ ስለሆነ

4. ከዚህ በፊት ምንም አይነት የወንጀል ክስ የሌለበት እና ፀባዩ በጣም ጥሩ የሆነ ግለሰብ ስለሆነ ከሌላ የተዘርዘሩትን በሙሉ ታይተው
ከ3 ዓመት ወደ 25 ቀን ወርዶ ተከሳሽ " ታማኝ አስማማው አንዳርጌ " የ25 ቀን እስር እንዲታሰር ተፍርዶበታል::

የኢራን የኑክሌር ተቋማትና የትራምፕ እርግጠኝነት!? አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በኢራን የኒኩሌር ተቋማት  ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን  የኒኩክሌር ተቋሞቿን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ...
24/06/2025

የኢራን የኑክሌር ተቋማትና የትራምፕ እርግጠኝነት!?

አሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በኢራን የኒኩሌር ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን የኒኩክሌር ተቋሞቿን ለማደስ ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆኗን ያስታወቀች ሲሆን፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ግን ኢራን በደረሰባት አውዳሚ ጥቃት ሳቢያ ከዚህ በኋላ የኒኩሌር ተቋማቷን እንደማትገነባ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ "ኢራን መቼም ቢሆን የኒኩሌር ተቋሞቿን መልሳ አትገነባም" ብለዋል፡፡

የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ኃላፊ መሀመድ ኢስላሚ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሀገራቸው ጥቃት የደረሰባቸውን የኒኩሌር ተቋማት ወደ ስራ ለማስገባት ማቀዷን አስታውቀዋል፡፡

ዜና፡ በሳዑዲ_አረቢያ  37 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፁበሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ቢያንስ 37 ኢ...
20/06/2025

ዜና፡ በሳዑዲ_አረቢያ 37 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገለፁ

በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ቢያንስ 37 ኢትዮጵያውያን የሞት ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲሉ 31 የሲቪል ማህበረሰብ እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ዜጎችን ጨምሮ መቶዎች በሚቆጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሊደረግባቸው እንደሚችል ተገልጿል።

ደርጅቶቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ ከህገ ወጥ አደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት እየጨመረ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ፣ #ሶማሊያና #ግብፅ ዜጎች ህይወት "ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው" ገልጸዋል።

መግለጫው፤ በተያዘው ዓመት ሰባት ኢትዮጵያውያን እና 19 የሶማሊያ ዜጎች “ሃሺሽ በማዘዋወራቸው” ግድያ እንደተፈጸመባቸው ገልጿል። በተጨማሪም “ሰኔ 9 ፣ 2017 ዓ/ም ሶስት የኢትዮጵያ ዜጎች እንደተገደሉ" እና ሌሎች ደግሞ በማንኛውም ጊዜ ልንገደል እንችላለን በሚል ስጋት ውስጥ እንዳሉ አመላክተዋል።

Address

Woldia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woldia Fortune posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Woldia Fortune:

Share