28/08/2025
ጥቆማ ...
ለወልድያ አስቀያሚ ገፅታ የፈጠሩ ህንፃዎች !
በመንገድ ስራው ምክንያት ከፊል የህንፃው ክፍል የፈረሰባቸው ፣ ካሳ ተከፍሏቸው አሁንም ለከተማው አስቀያሚ መልክ ያለውን የገጠጠ ፍራሽ ህንፃቸውን አቁመው የሚገኙ ባለሀብቶች ሀዬ ሊባሉ ግድ ነው።
እነዚህ የህንፃ ባለቤቶች ካሳ የተቀበሉበትን እና በመንገድ ስራው የፈረሰውን ህንፃቸውን አፍርሰው ከተማችንን የሚመጥን ህንፃ መገንባት ግዴታቸው እንደሆነ ይታወቃል። ሁሉም ለመገንባት የአቅም ችግር እንደሌለባቸው የከተማው ኗሪ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጉዳይ ሆኖ ሳለ አሁን እየተዘጋጁ ያሉት ግን የፈረሰውን ህንፃቸውን ጠጋግነው የኮንቴነር በር በመግጠም የማስቀጠል ፍላጎት ነው እያየን ያለነው።
እነዚህ ለከተማችን የተሻለ ኢንቨስትመንት ሰርተው እንዲያሳዩ የምንጠብቃቸው ባለሀብቶች፣ ለከተማችን አስቀያሚ ገፅታ የሚፈጥር ኮተት ደርድረው ማየት አንሻም። ይሄ እድገቷን ቀን ከሌት የምንከታተልላትን ከተማችንን ወደ ዃላ የሚጎትት ተግባር ነው።
ከተማችን ለ 2035 ዓ.ም አስቦ የሚገነባ እንጂ ወደ 1995 የሚመልሳት ባለ ሀብት አትፈልግም!
ይሄ ካሳ የተከፈለበት የፈራረሰ ህንፃ ከነ አስቀያሚ ገፅታው ሙሉ በሙሉ መነሳት ያለበት ሲሆን በምትኩም ከተማቸንን የሚመጥን ግንባታ እንዲሰራ እንጠይቃለን።
ይሄን ጉዳይ ወደፊት ሂደቱን እየተከታተልን በሰፊው እንመለስበታለን!