Ethio 24

Ethio 24 ፈጣን እለታዊ ዜና እና ስፖርት ያገኛሉ

በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በስፋት ለማምረት እየተሰራ ነው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በአገር ውስጥ በስፋት ለማምረት እየተሰራ ...
10/04/2020

በኢትዮጵያ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በስፋት ለማምረት እየተሰራ ነው

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ደረጃቸውን የጠበቁ የፊት ጭንብሎች በአገር ውስጥ በስፋት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

በሥራቸው ባህሪ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የፊት ጭንብልና ጓንት አዘውትረው እንዲጠቀሙ ሚኒስትሯ ምክረ ሃሳብ ለግሰዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ደረጃቸውን የጠበቀ የፊት ጭንብል በአገር ውስጥ እንዲመረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው።

10/04/2020
 በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,232• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 442• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - ...
10/04/2020



በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,232
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 442
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 9
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 57
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• ያገገሙ - 4
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 65

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸውበኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን...
10/04/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው።

ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።

አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።

የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።

ኢ/ር ታከለ ኡማና ዶ/ር ሊያ ታደሰ  ከኮሮና ቫይረስ ህክምና ጋር በተያያዘ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ማገገሚያ ማእከላትን ጎበኙየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ  ኢ/ር ታከለ ከጤና ሚ...
10/04/2020

ኢ/ር ታከለ ኡማና ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከኮሮና ቫይረስ ህክምና ጋር በተያያዘ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ማገገሚያ ማእከላትን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ከበደ ጋር በመሆን በማገገሚያ ማእከላቱ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ የጤና ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል።

የኮሮና ቨይረስ ህክምና በሚሰጥበት ማእከላት በመሄድ የጤና ባለሙያዎቹን ያነጋገሩት ኢ/ር ታከለ፣ የጤና ባለሙያዎቹ ሙሉ ኑሮአቸውን በማእከላቱ በማድረግ እየሰጡ ላለው አገልግሎት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ወደ ውጪ ሳይወጡ ሙሉ ኑሮአቸውን በማእከላቱ በማድረጋቸው የተለያዩ አገልግሎቶችና ግብአቶች ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አንስተዋል።

የተነሱት ችግሮች በትብብር እንደሚፈቱ የገለፁት ኢ/ር ታከለ፣ የከተማ አስተዳደሩ የራሱን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለጤና ባለሙያዎቹ የጄኔሬተር፣ የምግብ ግብአቶችንና ጊዜ ማሳለፊያ ቁሳቁሶች አበርክቷል።

በባንኮክ መጠጥ ከመታገዱ በፊት ብዙዎች ለመሸመት ሩጫ ላይ ናቸውበታይላንዷ መዲና ባንኮክ ከዛሬ ሚያዝያ 2፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት የሚቆይ የመጠጥ ሽያጭ እግድ ውሳኔ መተላለፉን ተ...
10/04/2020

በባንኮክ መጠጥ ከመታገዱ በፊት ብዙዎች ለመሸመት ሩጫ ላይ ናቸው

በታይላንዷ መዲና ባንኮክ ከዛሬ ሚያዝያ 2፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት የሚቆይ የመጠጥ ሽያጭ እግድ ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ ብዙዎች ለመሸመት ሲሯሯጡ ታይተዋል።
ባለስልጣናቱ ይህንን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተገደዱት ከሶስት ቀናት በኋላ ለሚከበረው የታይላንድ አዲስ አመትን አስመልከቶ የሚደረጉ ጭፈራዎችን ለመቀነስና በአሁኑ ሰአት የሚደረጉ ንክኪዎችን በማስወገድ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ ነው ብለዋል።
የእግዱም ውሳኔንም ተከትሎ በትላልቅ መደብሮች ላይ ረዣዥም ሰልፎች የታዩ ሲሆን፤ ብዙዎችም እግዱ ተፈፃሚ ከመሆኑ በፊት መጠጣቸውን ለመሸመት ሲሯሯጡ ነበር። ይህም ሁኔታ በብዙዎች ዘንድ ትችትን አስተናግዷል።

ምንጭ፦ቢቢሲ አማረኛ

የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለህክምና ባለሙ...
10/04/2020

የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ

(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለህክምና ባለሙያዎች ልብስ መግዣ የሚሆን የ500 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ።

የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ለህክምና ባለሙያዎች ልብስ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ለመግዛት የገንዘብ ድጋፉ መደረጉን ገልጸዋል።

ሀኪሞች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በቀጥታ ከህሙማን እና ተጠርጣሪዎች ጋር የሚገናኙ እና ለህሙማን ምግብ የሚያቀርቡ እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለእነርሱ በመስጠት ቁሳቀሱን ማሟላት ማስፈለጉን ነው የገለፁት።

ምክር ቤቱ ከክልል እስከ ቀበሌዎች ባለው መዋቅር ህብረተሠቡ ከኮሮና ቫይርስ ራሱን እንዲጠብቅ በተዳራጀና በተቀናጀ አግባብ የግንዛቤ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን አፈጉባዔው አንስተዋል።

በቀጣይም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ምክር ቤቱ አሁን የጀመረውን ስራ በቅንጅት ከማህበረሰቡ ጋር አጠናክሮ ይሰራል ብለዋል።

በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕርግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሙልነሽ አበበ ድጋፉን ከአፈጉባኤ ወርቅሰው ማሞ ተረክበዋል።
ችግር እየሆነ ያለው የጤና ባለሙያዎች የመከላከያ ጋዎንና ጭንብል እንደሆነ በማንሳት ምክር ቤቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በተጨማሪም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቫይረሱን በመከላከሉ ከፊት ሆነው እየሰሩ ላሉት ሀኪሞች መከላከያ የሚሆን ጋውንና ጭንብል ማምረት በመቻሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ኤፍ ቢ ሲ

ቻይና በአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ላይ የተከፈተውን የዘረኝነት ጥቃት እንደምታወግዝ  ገለጸችቻይና በአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የተከፈተውን ግለ...
10/04/2020

ቻይና በአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ላይ የተከፈተውን የዘረኝነት ጥቃት እንደምታወግዝ ገለጸች

ቻይና በአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የተከፈተውን ግለሰብ ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ጥቃት አጥብቃ እንደምታወግዝ አስታወቀች።

በአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ የተከፈተውን የዘረኝነት ጥቃት ዘመቻ ቻይና አጥብቃ እንደምታወግዝ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣዎ ሊጂያን ተናግረዋል።

እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ከታይዋን ይሄ ዘረኝነትን መሰረት ያደረገ የጥቃት ዘመቻ ላይ የተከፈተባቸውን ዘመቻ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረጉ ማናቸውንም ሙከራዎች ቻይና አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።

በዶ/ር ቴድሮስ የአመራር ዘመን የአለም የጤና ድርጅት የሃገራትን የጤና ስርዓት የሚያሻሽሉ ስራዎችን በመተግበር፣ ከባድ አለም አቀፍ ወረርሽኞችን ለመከላከል ፈጣን ምላሽ በመስጠትና ለጤና ዘርፉ አለም አቀፍ ትብብሮችን ለማሳደግ እየሰሩ ስለመሆኑም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ሳይንስንተከትሎ ኃላፊነቶቹን በሚገባ በመወጣት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በሰፊው የታወቀ እንዲሁም ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈበትን ፣ እና ሁልጊዜም ለሁኔታዎች የሚያሳየውን ያልተዛባ አቋምና ገለልተኝነት ቻይና እንደምትደግፍ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ቻይና በዓለም አቀፉ ወረርሽኞችንየማጥፋት ትብብሮች ግንባር ቀደም ሚና መጫወቷን እንደምትቀጥል ገልጸው፤ የታይዋን ዲሞክራቲክ ፕሮግሬሲቭ ፓርቲ ባለስልጣናት ጉዳዩን ፖለቲካዊ መልክ እንዲይዝ ሊያደርጉት እንደቻሉ ገልጸዋል።

እውነተኛው ዓላማቸው የተከሰተውን ወረርሽኝ ተመርኩዘው ከቻይና መገንጠል መሆኑን ያነሱት ቃል አቀባዩ ይሄ አይነቱን እንቅስቃሴ ቻይና በጥብቃ የምትቃወመውና በፍጹም ሊሳካ የማይችል ነው ማለታቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።

ሩቅ ምስራቃዊት አገር ታይዋን የዓለም የጤና ድርጅት አባል አለመሆኗ ይታወሳል።

ምንጭ፦ኢዜአ

የኒው ዮርክ ከተማ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ ሀገራት ቀዳሚ ሆናለች በአሜሪካ ካሉ ከተሞች ውስጥ ኒው ዮርክ የቫይረሱ ወረርሽኝ ማዕከል ሆናለች። ከተማዋ በአሜሪካ ብቻ አይደለም በኮሮናቫይረስ ተያ...
10/04/2020

የኒው ዮርክ ከተማ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁ ሀገራት ቀዳሚ ሆናለች

በአሜሪካ ካሉ ከተሞች ውስጥ ኒው ዮርክ የቫይረሱ ወረርሽኝ ማዕከል ሆናለች። ከተማዋ በአሜሪካ ብቻ አይደለም በኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከየትኞቹም አገራት በልጣ ቀዳሚ ሆናለች።
በቅርብ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በትናንትናው ዕለት በቫይረሱ የተያዙ ተጨማሪ 10 ሺህ ሰዎች ከመገኘታቸው ጋር ተያይዞ ቁጥሩን 159, 937 አድርሶታል።
ይህም ቁጥር በስፔን ከተያዙት 153 ሺህና በጣልያን 143 ሺህ ሰዎች በላይ ሆኖ ቀዳሚ አድርጓታል።
የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ቻይና በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 82 ሺህ ሲሆን 3,300 ሰዎች ሞተዋል።
በአጠቃላይ በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 462 ሺህ ሲሆን 16,500 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል።
በዓለም ላይ ያለውንም አሃዝ በምናይበት ወቅት 1.6 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 95 ሺህ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።
ኒው ዮርክ በቫይረሱ ክፉኛ የተጠቁ አገራትን በቁጥር ብትቀድምም፤ የሟቾችን ቁጥር ግን 7 ሺህ ነው የተመዘገበው። በስፔን 15,500 ሰዎች ሞተዋል፤ ከፍተኛ የሟች ቁጥር በተመዘገበባት ጣልያንም የ18 ሺህ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።

ዘመን ባስ በአዲስ አበባ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀበአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቅረፍ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ዘመን ባስ አገር አቋራ...
10/04/2020

ዘመን ባስ በአዲስ አበባ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት መጨናነቅን ለመቅረፍ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ዘመን ባስ አገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለዉ ዘመን ባስ፣ የጎልደን ባስ፣ የሀበሻ ባስ እና የኛ ባስ አክሲዬን ማህበራት አውቶብሶቻቸውን በመመደብ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።

ዘመን ባስ አገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በአዲስ አበባ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት እርቀትን ጠብቆ ለመጓጓዝ የሚፈጠረውን የትራንስፖርት እጥረትና መጨናነቅ ለመቀነስ በማሰብ "ነፃ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ለአሳደገን ህዝብ" በሚል መሪ ቃል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

✅ መነሻ መስቀል አደባባይ ስታድየም ዙሪያ።
✅ መዳረሻ ቦታዎች>
🚍 ጦር ሀይሎች፣አየርጤና
🚍 ሳር ቤት፣መካኒሳ፣ጀሞ፤ተመላሽ በሃና ማሪያም ቃሊቲ።ከቃሊቲ
ሳሪስአቦ፣ቦሌ፣ሜክሲኮ
🚍 መገናኛ፣ወሰን፣ካራ፣የካ አባዶ፤ተመላሽ በመገናኛ፤ቦሌ፤ሳሪስ ቃሊቲ። ከቃሊቲ
በሳሪስ፤እስታዲየም፤ሜክሲኮ
🚍 ሳሪስ፣ቃልቲ።ተመላሽ እስከ ሜክሲኮ
🚍 አራት ኪሎ፣ስድስት ኪሎ፣ሽሮ ሜዳ
🚍 ፒያሳ አዲሱ ገበያ።
🚍 አስኮ መንገድ መድኃኒዓለም እነዚህን ዋና ዋና መንገዶችን መነሻና መድረሻ በማድረግ ስምሪቱ እንደ አካባቢው ትራንስፖርት እጥረት የሚስተካከል ከ01/08/12 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናቶች በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጠት አክሲዮን ማህበሩ መግለፁን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ebc

ዓለም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም በግል ሳይቀር የተለያዩ ጫናዎች እየገጠሟቸው መሆኑን ከተና...
10/04/2020

ዓለም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት የሚመራው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም በግል ሳይቀር የተለያዩ ጫናዎች እየገጠሟቸው መሆኑን ከተናገሩ በኋላ የታይዋን ፕሬዝደንት ምላሽ ሰጡ።

የታይዋን ፕሬዝዳንት ሳይ ኢንግ-ዌን አገራቸው ከማንም በላይ መገለልን ስለምትረዳው ማንኛውንም አይነት ዘርን መሰረት ያደረገ ልዩነትን እንደምትቃወም ገልጸዋል።
በዓለም የጤና ድርጅትና በታይዋን መካከል ያለው ውጥረት አዲስ እንዳልሆነ የተነገረ ሲሆን፤ ዋነኛ ምክንያቱ ቻይና የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትላት ታይዋን ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ ነው።

የዓለም የጤና ድርጅት አባል መሆን የሚችሉት አገራት የተባበሩት መንግሥታት አባላት ብቻ ሲሆኑ፤ ታይዋን ግን በድርጅቱ ውስጥ እውቅና ስለሌላት አባል ለመሆን አልበቃችም።
በዚህም የዓለም ጤና ድርጅት በሚጠራቸው አስቸኳይ ስብሰባዎችና ማብራሪያዎች ላይ እንድትሳተፍ አትጋበዝም፤ ይህ ነው ለውጥረቱ ምክንያት እንደሆነ የተጠቀሰው።
የታይዋን ፕሬዝዳንት እንዳሉት "ለዓመታት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተገለን በመቆየታችን፤ መገለልንና መነጠልን ከማንም በተሻለ ሁኔታ እናውቀዋለን” ሲሉ በዶክተር ቴድሮስ ላይ ያጋጠመውን ጥቃት እንደማይደግፉት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሌላኛው ደግነት ከአዳማ አቶ ፀጋዬ ሁንዴና ወ/ሮ ኤልሳቤት አዱኛ አቶ ፀጋዬ ሁንዴና ወ/ሮ ኤልሳቤት አዱኛ በአዳማ ከተማ በሚገኘው የሳራ የንግድ ማዕከል ተከራይተው ለሚሰሩ ኢትዮጵያውን የሁለት...
10/04/2020

ሌላኛው ደግነት ከአዳማ አቶ ፀጋዬ ሁንዴና ወ/ሮ ኤልሳቤት አዱኛ

አቶ ፀጋዬ ሁንዴና ወ/ሮ ኤልሳቤት አዱኛ
በአዳማ ከተማ በሚገኘው የሳራ የንግድ ማዕከል ተከራይተው ለሚሰሩ ኢትዮጵያውን የሁለት (2) ወር ኪራይ ነፃ አድርገውላቸዋል።

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio 24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share