24/09/2026
የቀቤና ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት በሃገር አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ውጤታማ፣ አካታች እና ወቅቱን የዋጀ እንዲሆን የመመሪያ ማሻሻያ ማድረጉ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተገለጸ።
(ወልቂጤ) መስከረም 14/2019 ዓ.ም
የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር የብሄረሰቡን ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት (Ooggati) መመሪያ ለማሻሻል የተጀመረውን ሂደት ቀልጣፋ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድአሚን በደዊ ኦገት ከዚህ በፊት የነበሩ ማነቆዎችን ተቋቁሞ የመጣበት ሂደት አበረታች ነው ያሉ ሲሆን በልዩ ወረዳው ደረጃ ለማህበረሰቡ ፍትህ መስፈን እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ካለው ህገ መንግስት ጋር በማጣጣም ለዜጎች ቀልጣፋና ዘመናዊ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ምክር ቤቱ አቅም በመፍጠር የራሱን ቢሮ እና የኢኮኖሚ ምንጭ የሚሆኑ አማራጮችን በማመቻቸት የማቋቋም ሥራ መስራት እንደሚገባ ተነስቷል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ካፉ አረቦ ከስር መሰረት ይዘን የመጣነውን ቅርስ ለማስቀጠል አሁን ላይ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም መስራት እንደሚገባ አመላክተው ኦገትን በኢኮኖሚ የበለጸገ በማድረግ ለህዝቡ ፍትሓዊ ልማት በአረኣያነት መቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅናው ለማሳደግ ብሎም የሚሰጠው አገልግሎት እንዲጠናከር ህግና መመሪያን በመከተል ማስፈጸም እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀሚድ አስፋው የመመሪያ ማሻሻያው ተግባራዊ ለማድረግ ህገ ደንቡን መነሻ ያደረገ ከኦገት ምክርቤት አባላት ውይይት በማድረግ ለግብአት የሚሆን ሃሳብ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
በመድረኩ እንደ ፍትህ ጽህፈት ቤት የተዘጋጀው የስራ አፈጻጸም እና የኦገት የመቅጫ ስርዓት መመሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከውይይቱ የተገኘው ሃሳብ በግብአትነት በመውሰድ ቀጣይ ለኦገት ምክርቤት ቀርቦ በማጽደቅ ስራ ለይ የሚውል ይሆናል ብለዋል።
በመድረኩ ከትንሽ እስከ ትልቅ የሰው እና የንብረት ያሉ የወንጀል ድርጊቶች ተነስተው ሊወሰድ የሚገባ የእርምጃ አይነቶች ተብራርተዋል።
የኦገት አባላት በሰጡት አስተያየት መመሪያው ላይ የሚደረገው ማሻሻያ ወቅቱን የዋጀ እና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በመሆኑ እንደ አጠቃላይ የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ከምሁራኑ ጋር በመናበብ ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ይህ የምክክር መድረክ የቀቤና ብሄረሰብን የፍትህ ስርዓት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ማህበራዊ ሰላምን ለማስፈን ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ምክር ቤቱ በሚያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በሙሉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል።
****
በጃፋር ሁሴን
****
#ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ ለልማት !
ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ‼️
👉Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100072292788562&mibextid=ZbWKwL
👉ቀቤንሲና ቋንቋ ገፅ https://www.facebook.com/share/1K88DQfp6y/
👉Instagram https://www.instagram.com/qebena_sp_woreda_gov_com_affai?igsh=NHRiZjFybHk4dmRn
👉Twitter https://x.com/qebena39136?s=09
👉Telegram channel
https://t.me/Qebena1
👉youtube
htt