20/05/2025
የባንክ ሹፌሮቹ ከህዝቡ 4 ሚልየን ብር የሚያወጣ የባንክ አካውንት እንዲያስከፍቱ እስከ ሰኔ አጋማሽ ድረስ ቀነ ገደብ ተሰጣቸው! Meseret Media
_________________________________________________________________
በዚህ አስተያየት ላይ....
"የግል ባንኮች ሰራተኞች ላይ ከዲስትሪክት ጀምሮ በየቀኑ እየተደወለ አንዳንዴም ወደ ቅርንጫፎች እየመጡ ሰራተኞቹ ማድረግ የማይችሉትን ትዕዛዝ በመሥጠት ያን ካላደረጉ ደግሞ ከደሞዛቸው ጀምሮ ብዙ ቅጣቶች እንደሚጠብቃቸው እያስፈራሩ ብቻም ሳይሆን እያደረጉትም ይገኛሉ" የሚል አስተያየት በፀሀፊው አቶ ፍቃዱ ኤርሱሞ ተንፀባርቋል።
_____________________________________________________________________
መሠረት ሚድያ Reports
በርካታ የግል ባንኮች ሰራተኞቻቸውን በአስገዳጅነት ህብረተሰቡን የባንክ አካውንት እንዲያስከፍቱ ተልዕኮ እየተሰጡ መሆናቸውን የሚገልፅ አንድ አስተያየት በትናንትናው እለት ማስነበባችን ይታወሳል።
ዛሬ የምናስነብባችሁ ደግሞ ባንኮች ውስጥ በሹፌርነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች እያንዳንዳቸው በድምሩ 4 ሚልየን ብር የሚሆን የባንክ አካውንት እንዲያስከፍቱ ስለታዘዙ ሹፌሮች ነው።
ጉዳዩ እንዲህ ነው፣
አዋሽ ባንክ Awash Bank እንደሌሎቹ ባንኮች ሁሉ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሰራተኞቹን በከተማው ከማሰማራቱ ውጪ ሹፌሮቹም እያንዳንዳቸው 4 ሚልየን ብር deposit አስደርጉ መባላቸውን ሰማን።
"ሹፌሩ መኪናውን በአግባቡ መንዳት ትቶ ስለ ገንዘብ ማሰባሰብ ሲያስብ እና ሲጨነቅ ነው የሚውለው" ያሉን አንድ የተቋሙ ሰራተኛ ሁሉም ሹፌሮች እስከ ሰኔ አጋማሽ ግባቸውን እንዲመቱ (4 ሚልየን ብር ከህዝቡ deposit እንዲያስደርጉ) መታዘዛቸውን ተናግረዋል።
መሠረት ሚድያ የተመለከው አንድ የባንኩ ሰራተኞች የመልዕክት መለዋወጫ ግሩፕ ላይ የተፃፈ መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሲሆን "እያንዳንዱ የባንኩ አሽከርካሪ መኪና መንዳት ብቻ ሳይሆን ሀብት በማሰባሰብ ዘመዶቹን እና ጓደኞቹን ቡክ በማስከፈት አዳዲስ ደንበኞችን ማምጣት አለበት" ይላል።
መልዕክቱ አክሎም "አንድ አሽከርካሪ 4 ሚልዮን ብር ቢያመጣ የታለመውን እቅድ በቀላሉ ከግብ እናደርሳለን፣ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ አጋማሽ ድረስ በተሰጣችሁ እቅድ መሰረት እያንዳንዳችሁ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እንድትተባበሩ" ይላል።
ደህና ኑሮ ይኖራሉ የሚባሉትን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍል ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ በሆነበት በዚህ ወቅት አንድ ሹፌር በምን መልኩ 4 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ቡክ ማስከፈት እንደሚችል ለበርካቶች ጭንቀትን ብቻ ሳይሆን አስደማሚ ሆኗል።
በዚህ ዙርያ ከባንኩ መረጃ ከደረሰን እናቀርባለን።
መረጃን ከመሠረት!
(መሠረት ሚድያ)- በርካታ የግል ባንኮች ሰራተኞቻቸውን በአስገዳጅነት ህብረተሰቡን የባንክ አካውንት እንዲያስከፍቱ ተልዕኮ እየተሰጡ መሆናቸውን የሚገልፅ አንድ አስተያየት በትናንትና....