11/06/2023
ለሸሂድ ቤተሰቦች አማናውን አድርሰናል
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
በሁለተኛ ጁመዓ መስጅዴን አታፍርሱብኝ በማለታቸው ብቻ በፀጥታ አካላት የተሰዉ ሶስት ወንድሞቻችን ኢብራሂም ደንበል፣ አንዋር ሱሩር ፣ ዙበይር ሙደሲር እና በመጀመሪያ ጁመዓ በጥይት ሆድ እቃውን ተመቶ የተሰዋው ጀሚል ሪድዋን በድምሩ ለአራቱ የመስጅድ ሹሀዳዎች በኮልፌ መካነ መቃብር በተገኙ ምዕመናን 245,154 ብር ተሰብስቧል።
ለአራቱ የመስጅድ ሹሀዳዎች የተሰበሰበውን ብር ከሶስት ቀናት በፊት ከኡስታዝ ናስር (አወሊያ) ጋር በመሆን ቤት ለቤት በመሄድ አድርሰናል።
✨ ለኢብራሂም ደንበል (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (አየር ጤና) አሳዳጊው ለሆነችው እህታችን ኑሪት 61,288.50 ብር አስረክበናል።
✨ ለዙበይር ሙደሲር (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (ሎሚ ሜዳ ) ለወላጅ አባቱ ሙደሲር 61,288.50 ብር አድርሰናል።
✨ለጀሚል ሪድዋን (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (7ተኛ ወረድ ብሎ) ለወላጅ እናቱ ሳዲያ ሙስጠፋ 61,288.50 ብር ሰጥተናል።
✨አንዋር ሱሩር (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰቡን በመዘየር እናቱን በመጠየቅ ለወንድሙ ጀሚል 61,288.50 ብር አድርሰናል።
በሁለቱ ቀን ጉዞ ከኡስታዝ ናስር (አወሊያ) ጋር አራቱም ቤት በመዘየር ያደረስን ሲሆን ቤተሰቦች መዘየርና ማገዝ ከጎናቸው መቆም መስጅዴን አታፍርሱብኝ የምንል ሁላ ድርሻ ነው።
ለመስጅዶቻችን ክብር ለተሰዉ ነፍሶች የአላህ ሰላምና እዝነት ምህረት ይስፈን!