Mamma Media

Mamma Media ማማ ሚዲያ የዐማራውን ህዝብ ወደ ከፍታ ማምጣት እና እራሱንም ?

ወንድሜ ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው! ማረፍህን ሰምቼ ወደ አገር ቤት ደወልሁ ። የሰማሁት ነገር እውነት መሆኑን አረጋገጡልኝ። አስደንጋጭ  ሀዘን።በጥበብ ውስጥ በግሽ አባይ የባህል ቡድን " አንቱየ...
15/06/2026

ወንድሜ ድምፃዊ ሰማኸኝ በለው!

ማረፍህን ሰምቼ ወደ አገር ቤት ደወልሁ ። የሰማሁት ነገር እውነት መሆኑን አረጋገጡልኝ። አስደንጋጭ ሀዘን።

በጥበብ ውስጥ በግሽ አባይ የባህል ቡድን " አንቱየዋ " በተሰኘው ዝግጅት የጥበብ ታላቅ ችሎታህን በማሳየት ከዚያም በተከታታይ አመታት ድንቅ የሙያ ስራዎችህን ለህዝብ በማቅረብ አድናቆት ሲቸርህ ቆይቷል።

ዛሬ ከዚህ ዓለም ተለይተህናል። እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገንት ያሳርፍልን!!!

ለመላው ቤተሰቡ ፣ ለሙያ ባልደረቦቹ ፣ ለጓደኛ እና ለአድናቂዎቹ እግዚአብሔር መፅናናቱን ይስጣችሁ!!!

እሱባለው ጫኔ

01/06/2026

Check out Esu’s video.

31/05/2026

የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በዛሬው ቀን ያስተላለፈው መለኣክት !!!

21/05/2026

የአማራ ህዝብ ፍላጎት ፣ ምርጫው እና ሰኔ ፣ የፋኖ ዝግጅት ጉዳይ

04/05/2026

6 likes. "አርበኛ አረፈአይኔ ተጎድ ማማ ሚዲያ ( Mamma media ) 04 05 2026"

የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) በሳተላይት ቴሌቪዥን ምስረታ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ተቋማት፣ የ...
03/05/2026

የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) በሳተላይት ቴሌቪዥን ምስረታ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!

በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ተቋማት፣ የሕዝባችንን የህልውና ትግል፣ ሰብዓዊ መብትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማስከበር የአማራ ሚዲያ ካውንስልን (AMC) በማቋቋም ላለፉት ሁለት አመታት በጋራ ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመሥረት ባለፉት ሁለት ወራት በጠንካራ ዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንገጽ በታላቅ ኩራት ነው።

ይህ ካውንስል ከሁለት ዓመት በፊት ሲመሠረት በተበታተነ መልኩ የሚደረጉ የሚዲያ ሥራዎችን ወደ አንድ ወጥና ጠንካራ የጋራ አጀንዳ (Unified Narrative) ለማምጣት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎችንና ተቋማትን አቅም በማቀናጀት የሕዝብን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የመረጃ አፈና ለመስበር፣ በጨለማው ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ እና ድምፅ ለሌላቸው ኢትዮጲያዊያን ድምፅ ለመሆን፣ በዲጂታልና በሳተላይት አማራጮች አማካኝነት እውነቱን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ የተቋቋመ የሙያና የትግል መድረክ ይሆናል።

ካውንስሉ ካቀዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች መካከል ቀዳሚው፣ የኢንተርኔት መቆራረጥና ሳንሱር የማያግደው፣ ኢንተርኔት በማይደርሰበትና አገዛዙ ኢንተርኔት ለዘጋበት ሕዝብና አካባቢ ለመድረስ፣ በመላው ኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሚሆን "የሕዝብ ድምፅ" የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ መመሥረት ነው። ይህ ጣቢያ የአባል ሚዲያዎችን ሰፊ የሕዝብ መሠረትና አቅም በማቀናጀት፣ የሕዝባችንን የታሪክ፣ የባህል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍላጎቶች የሚወክል ቀዳሚ ተቋም ይሆናል።

ይህ ታላቅ ተቋም በምስረታ ላይ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት አብረውን እንዲቆሙና እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፦

• ለሚዲያ ባለሙያዎችና ተቋማት፦ በካውንስሉ ውስጥ ያልታቀፋችሁ ሚዲያዎች የካውንስሉን አቅም በማጠናከርና የጋራ አጀንዳን በመገንባት ሂደት ውስጥ በሙያችሁ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።

• ⁠በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እየተሳተፋችሁ ላላችሁ የህልውና ታጋዮች አብረን እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን።

• ለሲቪል ማህበረሰብና ሙያ ማህበራት፦ በዚህ አመራር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ የጣቢያውን ገለልተኝነትና ሕዝባዊነት እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን።

• ለባለሀብቶችና ለደጋፊዎች፦ ይህንን የመረጃ አፈና የሚሰብር የሳተላይት ፕሮጀክት ከሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የታሪክ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ጥሪ እናቀርባለን።

• ለዲያስፖራው ማህበረሰብ፦ የትግሉ የጀርባ አጥንት በመሆን የካውንስሉን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና የፋይናንስ ዘላቂነት፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲኖረው በምትችሉት ሁሉ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ለፍትሕና ለህልውና የሚደረገውን ትግል በጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ታንጾ ለመዘገብና እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ለማድረስ ቆርጦ ተነስቷል። ይህ የመጀመሪያው እርምጃችን ሲሆን፣ በቀጣይ በዝርዝር የምናሳውቃቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች ታላቅ ተስፋ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠርም።

"የጋራ ድምፅ ለፍትሕና ለእውነት!"
የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC)
ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

28/04/2026

2 likes, 1 comment. "ምርጫ እና ብአዴን ማማ ሚዲያ Mamma media 28 04 2026"

24/04/2026

1 like. "ሰራዊቱ መክዳቱን ቀጥሏል!!! 23 04 2026"

Address

Chelsea

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mamma Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mamma Media:

Share